“እውነት ለሁሉ” ድረ-ገፅ ክርስትናንና እስልምናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ ለሙስሊሞች ጥያቄዎችም መልስ ይሰጣል፡፡
የዚህ መጽሐፍ ዓላማ ለሙስሊም ወዳጃችሁ ወንጌልን ስታካፍሉና ክርስቲያናዊ አስተምሕሮዎችን ስታብራሩ ከትክክለኛው ነጥብ መጀመር ትችሉ ዘንድ መርዳት ነው። እስልምናን ይበልጥ እንድታውቁ እንደሚያግዛችሁና ይልቁኑ የክርስትናን አስተምሕሮዎች ጥልቀት እንዲሁም የነቢያትን መልእክት መሰናሰልና በክርስቶስ ፍፃሜን ማግኘት በማሳየት እምነታችሁ በጠንካራ መሠረት ላይ የቆመ መሆኑን እንድትገነዘቡ እንደሚረዳችሁ እተማመናለሁ። ክርስትና እውነት መሆኑን አጥርታችሁ እንድታዩና ለሙስሊም ወዳጃችሁ ወንጌልን ለማካፈል ይበልጥ እንድትበረታቱ እንደሚያግዛችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።
ለሙስሊሞች ወንጌልን ማካፈል ለማንኛውም ሰው እንደማካፈል ነው፤ ልምድ በማዳበር እየተሻሻላችሁ ትሄዳላችሁ። እንድትናገሩ እግዚአብሔር የሚሰጣችሁን ዕድል ሁሉ ተጠቀሙ።
ሳሙኤል ግሪን
ወቅታዊ ጽሑፎች
በመላው ዓለም የሚገኙት ሙስሊሞች በየዓመቱ የአል-አድሃን በኣል ያከብራሉ፡፡ ይህ በኣል በሙስሊሞች የጨረቃ አቆጣጠር መሠረት ዙል ሒጃ በመባል በሚታወቀው ወር 10ኛ ቀን ላይ ይውላል፡፡ አድሃ የሚለው ቃል ዳሂያ ወይንም መሥዋዕት ከሚለው የአረብኛ ሥረወ ቃል የተገኘ ነው፡፡ የአል-አድሃ በኣል የመሥዋት በኣል ወይንም ታላቁ በኣል፣ ዒድ አል ከቢር በመባል ይታወቃል፡፡ በአል-አድሃ በኣል ዕለት ሙስሊሞች ፈጣሪ የአብርሃምን ልጅ የዋጀበትን ክስተት ለማስታወስ በግ ይሠዋሉ፡፡ ይህ ክስተት የክርስቶስን ቤዛዊ መሥዋዕትነት ከሚያመለክቱ የተውራት ተምሳሌታዊ ትንቢቶች መካከል አንዱ ነው። በወንድም ፉአድ መስሪ የተጻፈውን ይህንን ግሩም ቡክሌት ያንብቡ…
ኢንጂል ተበርዟልን? በሚል ርዕስ በፉአድ መስሪ የተጻፈው ቡክሌት የኢንጂልን ተዓማኒነት በተመለከተ ብዙ ማስረጃዎችን በውስጡ የያዘ ነው። ወንድም ፉአድ የእስልምና እምነቱን በመልቀቅ ክርስትናን ከመቀበሉ በፊት የኢንጂልን ተዓማኒነት በተመለከተ ሰፊ ጥናት አድርጓል። የጥናቱ ውጤትም ብዙ ሙስሊሞች ከሚናገሩት በተጻራሪ ኢንጂል በትክክል ተጠብቆ ለዚህ ዘመን መብቃቱን በማረጋገጥ ክርስቶስን ለመከተል እንዲወስን አድርጎታል። ይህንን ቡክሌት ያንብቡ…
ሙስሊሞች ፈጣሪን በጣም የሚፈሩና መልካም ነገሮችን ለሌሎች በማድረግ የሚያምኑ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ልክ እንደ ክርስቲያኖች በፈጣሪ አንድነት፣ በነቢያት፣ በቅዱሳት መጻሕፍት፣ በመላእክት መኖር፣ በሙታን ትንሣኤና በመጨረሻው ፍርድ ያምናሉ፡፡ በፍቅርና በአክብሮት በመቅረብ በእነዚህ ርዕሶች ዙርያ ከነርሱ ጋር ለመወያየት የሚፈልጉትንም ክርስቲያኖች ለመስማት ፍቃደኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ ከሙስሊሞች ጋር ያለን ግንኙነት በፍርሃት ወይም በጥርጣሬ ላይ የተመሠረተ ሳይሆን በፍቅርና በአክብሮት ላይ የተመሠረተ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ቡክሌት ለሙስሊሞች የክርስቶስን ወንጌል ለማካፈል የሚረዱ መሠረታዊ መረጃዎችን ይሰጣል። ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…
በሙስሊሞች እምነት መሠረት ቁርኣን ፍፁም የሰው እጅ ያልገባበት ከአላህ ዘንድ በቀጥታ የወረደ መገለጥ ነው፡፡ ይህንንም መገለጥ ‹‹ተንዚል›› በማለት ይጠሩታል፡፡ በ23 ዓመታት ውስጥ ለመሐመድ በጅብሪል አማካይነት የወረዱላቸው የአላህ ቀጥተኛ ንግግሮች ስብስብ እንደሆነም ያምናሉ፡፡ “ኡም አል-ኪታብ” (የመጽሐፉ እናት) በመባል የሚታወቅ ያልተፈጠረ ነገር ግን አላህ በነበረበት ጊዜ ሁሉ ከርሱ ጋር የነበረ ጽሑፍ እንዳለና ቁርኣንም የዚያ ግልባጭ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ የቁርአንን ታሪክ ስናጠና ግን እውነታው ከዚህ የተለየ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ሙስሊም ወገኖች እንደ ቅዱስ መጽሐፍ አድርገው የተቀበሉት ቁርአን እነርሱ ከሚያምኑት በተጻራሪ የሰው እጅ ገብቶበታል፡፡ ይህንን ደግሞ ጥንታውያን የሆኑት እስላማዊ ጽሑፎች ያረጋግጣሉ፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…
ቁርአን ስለመሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተተነበየ ይናገራል (ሱራ 7፡157-158፤37፡6)፡፡ ሙስሊም አቃቤ እምነታውያን እነዚህን ትንቢቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳገኙ በርግጠኝነት እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ክርስቲያኖችና አይሁዶችም ሆነ ብለው ትንቢቶቹን እንደሚደብቁ በማስመሰል ወቀሳ ሲሰነዝሩ እያደመጥን ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ስለመሐመድ የተነገሩ ትንቢቶች ናቸው በማለት የሚያቀርቧቸውን ጥቅሶች በትክክል ብንመረምራቸው የመሐመድን ነቢይነት በመጽሐፍ ቅዱስ ለማረጋገጥ መሞከራቸው “ላም ባልዋለበት…” እንደሚባለው ምሳሌ ዓይነት ከንቱ ምኞት መሆኑን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…