ከኛ ጋር ያገልግሉ

ከኛ ጋር ያገልግሉ

ውድ የገጻችን ተከታታዮች “የእውነት ለሁሉ” የአገልግሎት ቡድን ይህንን መልካም ሥራ በጥሩ ሁኔታ ለማስኬድ የናንተን እገዛና ድጋፍ ይሻል። በሚከተሉት መንገዶች በአገልግሎቱ ውስጥ መሳተፍ ትችላላችሁ፦

  1. ጽሑፎችን በማዘጋጀት፦ የድረ ገጻችንን ደረጃ የሚመጥኑ የክርስቲያን-ሙስሊም ውይይትን የተመለከቱ ጽሑፎችን በአማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ትግርኛና እንግሊዘኛ በማዘጋጅት መሳተፍ ትችላላችሁ። ጽሑፎቹ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦
  • ጽሑፎቹ ከዚህ ቀደም በሌሎች ድረገፆች ላይ የታተሙ መሆን የለባቸውም።
  • በሌላ ግለስብ ወይንም ድርጅት በቅጂ መብት የተጠበቁ ጽሑፎች አይስተናገዱም።
  • ጽሑፎቹ ትርጉም ከሆኑ ምንጭ ሊጠቀስላቸው ይገባል።
  • የጽሑፎቹ ደራሲያን የቅጂ መብታቸው የተጠበቀ ቢሆንም በድረገጹ ላይ የታተሙ ጽሑፎችን ለሌላ ድረገጽ መስጠት አይቻልም።
  • በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን በጽሑፎቹ ላይ ለሚሰነዘሩት ሒሶች ደራሲያኑ መልስ የመስጠት ዝግጁነት ሊኖራቸው ይገባል።
  1. በአርትዖትና ጽሑፎችን በማሔስ፦ ጽሑፎቻችን ከመታተማቸው በፊት ሥነ ጽሑፋዊ ገፅታቸውንና ነገረ መለኮታዊ ትክክለኛነታቸውን በመገምገም እንዲሁም የፊደል ግድፈቶችን በማረም ድጋፍ የሚያደርጉ ወገኖች በእጅጉ ያስፈልጉናል።
  2. በአማርኛ የሚታተሙ ጽሑፎችን ወደ አፋን ኦሮሞና ወደ ትግርኛ በመተርጎም።
  3. ድረገጻችንን በተለያዩ ሚድያዎችና መድረኮች ለሕዝብ በማስተዋወቅ።
  4. በጸሎት።

ከላይ ከተጠቀሱት በማንኛውም መንገድ በአገልግሎቱ ውስጥ መሳተፍ የምትሹ ወገኖች በተከታዩ የኢሜል አድራሻችን ትጽፉልን ዘንድ እናበረታታችኋለን፦

ewnet4hulu@gmail.com

እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ።

ማንነታችን