ኢየሱስ አጥምቋል ወይንስ አላጠመቀም?

ኢየሱስ አጥምቋል ወይንስ አላጠመቀም?

በዮሐንስ 3፡22 መሠረት አጥምቋል:-

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ይሁዳ አገር መጣ፥ በዚያም ከእነርሱ ጋር ተቀምጦ ያጠምቅ ነበር።”

ነገር ግን በዮሐንስ 4፡1-4 መሠረት አላጠመቀም:-

እንግዲህ ኢየሱስ ከዮሐንስ ይልቅ ደቀ መዛሙርት ያደርጋል ያጠምቅማል ማለትን ፈሪሳውያን እንደ ሰሙ ጌታ ባወቀ ጊዜ፥ ይሁዳን ትቶ ወደ ገሊላ ደግሞ ሄደ፤ ዳሩ ግን ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አላጠመቀም።”

ልስ – ይህ በመጀመርያ ዕይታ ግልፅ ግጭት ቢመስልም ነገር ግን ጸሐፊው ለማለት የፈለገውን ነገር ለመረዳት ብንሞክር መልሱ በጣም ቀላል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ “አቶ አበበ ቤት ሠራ” ብንል የቤቱ ባለቤት እርሱ መሆኑን ለማመልከት እንጂ ምሰሶና ማገሩን የሠራው ሙያተኛ እርሱ ነው ለማለት ተፈልጎ ላይሆን ይችላል፡፡ ስለዚህ የቤቱ ባለቤት በመሆኑ ምክንያት አቶ አበበ ቤቱን ሠርቷል እንላለን ነገር ግን ምሰሶና ማገሩን ከመምታት አንፃር ከሆነ ቤቱን የሠራው አናፂው እንጂ አቶ አበበ አይደለም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በመጀመርያው ጥቅስ ውስጥ ኢየሱስ አጠመቀ የተባለበት ምክንያት የጥምቀቱ ባለቤት እርሱ ስለ ሆነና ሐዋርያት ደግሞ አገልጋዮች ብቻ በመሆናቸው ምክንት ሲሆን በሁለተኛው ጥቅስ ውስጥ ያጠመቁት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ እርሱ አለመሆኑ የተነገረበት ምክንያት ደግሞ የጥምቀቱን ሂደት፣ ማለትም ሰዎችን በውሃ ውስጥ የማጥመቁን ተግባር የፈፀሙት ደቀ መዛሙርቱ እንጂ ኢየሱስ ራሱ አለመሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ስለዚህ በነዚህ ጥቅሶች መካከል ግጭት የለም፡፡

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች?

ቁርኣን ግጭቶች