ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን የከበበው በኢዮአቄም ስንተኛ የንግሥና ዓመት ነው?

ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን የከበበው በኢዮአቄም ስንተኛ የንግሥና ዓመት ነው?

ሰሞኑን የተወሰኑ ሙስሊሞች “የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭት” ብለው በማሕበራዊ ሚድያዎች ላይ እየተቀባበሉት ለሚገኙት አንድ ሙግት ምላሽ እንሰጣለን፡፡ ሙግቱ እንዲህ የሚል ነው፡-

መቼም ዳንኤልና ኤርሚያስ በቁርኣን ባይጠቀሱም የእስራኤል ነቢያት ሆነው የተናገሩት ትንቢት እንደተፈፀመ እናያለን፤ ነገር ግን የዳንኤና የኤርሚያስ መፅሃፍ ታሪክ የገባበት መፅሃፍ መሆኑን ቅቡል ነው፤ ከዚህ ጭማሬ ጋር ተያይዞ እርስ በእርሱ ይጋጫል፤ ይህም ግጭት፦

    1. አንዱ ናቡከደነፆር ኢየሩሳሌምን የከበባት ኢዮአቄም በነገሰ በሶስተኛው አመት ነው ሲለን፦

ዳን1:1 የይሁዳ ንጉሥኢዮአቄምበነገሠበሦስተኛው ዓመትየባቢሎን ንጉሥናቡከደነፆርወደኢየሩሳሌም መጥቶ ከበባት

    1. ሌላው ደግሞ የኢያቄም ንግስና አራተኛው አመት ላይ የናቡከደነጾር የመጀመሪያው አመት ነው ይለናል፤በዚህ ጊዜ ገና ኢየሩሳሌም እንደሚከብ ትንቢት ተነገረ፦

ኤር.25:1 በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅበኢዮአቄም በአራተኛው ዓመት በባቢሎን ንጉሥበናቡከደነፆር በመጀመሪያው ዓመት ስለ ይሁዳ ሕዝብ ሁሉ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።

ኤር 25:9 ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ ባሪያዬንም የባቢሎንን ንጉሥ ናብከደነዖርን እወስዳለሁ፥በዚህችም ምድር በሚቀመጡባትም ሰዎች በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፥ ለመደነቂያና ለማፍዋጫም ለዘላለምም ባድማ አደርጋቸዋለሁ።

የቱ ነው ትክክል? ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌም የከበበው በኢያቄም ንግስና በሶስተኛ አመት ወይስ ከኢያቄም ንግስና አራተኛው አመት በኃላ?

መልስ

ሁለቱም ትክክል ናቸው፡፡

በባቢሎናውያን አቆጣጠር መሠረት አንድ ንጉሥ ከነገሠ በኋላ የመጀመርያው የንግሥና ዓመት የማይቆጠር ሲሆን አዲስ ዓመት ከገባ በኋላ አንድ ተብሎ ይጀመራል፡፡ ነገር ግን በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት ንጉሡ ዙፋን ላይ የወጣበት ዓመት የመጀመርያው ዓመት ተብሎ ይቆጠርለታል፡፡ ስለዚህ በባቢሎን ምድር ይኖር የነበረው ነቢዩ ዳንኤል የባቢሎናውያንን የንግሥና ዘመን አቆጣጠር በመጠቀም ስለቆጠረ የናቡ ከደነፆር ወረራ ኢዮአቄም በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እንደሆነ የጻፈ ሲሆን ነቢዩ ኤርምያስ ግን በይሁዳ ምድር ስለነበረ በአይሁድ አቆጣጠር መሠረት የመጀመርያውን የንግሥና ዓመት ጨምሮ በመቁጠር ኢዮአቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት ናቡ ከደነፆር በነገሠ በመጀመርያው ዓመት እንደሆነ ጽፏል፡፡ ንጉሥ ኢዮአቄም የነገሠው በ668 ዓ.ዓ. ስለነበር ነቢዩ ኤርምያስ በተጠቀመው የአይሁድ አቆጣጠር መሠረት አራተኛው የንግሥና ዓመቱ 665 ዓ.ዓ. ነው፡፡ ዳንኤል በተጠቀመው የባቢሎናውያን አቆጣጠር መሠረት የመጀመርያው የንግሥና ዓመቱ 667 ዓ.ዓ ሲሆን ሦስተኛው የንግሥና ዓመቱ በተመሳሳይ 665 ዓ.ዓ. ነው፡፡ ስለዚህ በሁለቱ መካከል ግጭት የለም፡፡ (ለበለጠ መረጃ አ.መ.ት. ማጥኛ ገፅ 1297 እንዲሁም Gleason L. Archer; Encyclopedia of Bible Difficulties, p. 288)


የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች?

ቁርኣን ግጭቶች