የይሁዳ አሟሟት እንዴት ነበር?

የይሁዳ አሟሟት እንዴት ነበር?

ማቴዎስ 26፡5 ታንቆ እንደሞተ ሲናገር የሐዋርያት ሥራ 1፡18 በግንባሩ ተደፍቶ ከመካከሉም ተሰንጥቆ አንጀቱ ተዘርግፎ እንደሞተ ይናገራል፡፡

ልስ – የሐዋርያት ሥራ 1፡18 ላይ ያለውን ቃል እስኪ እናንብብ፡-

ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው፡፡”

ይህ ጥቅስ አሟሟቱን ሳይሆን ከሞተ በኋላ የሆነውን የሚናገር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ላይ ሞተ የሚል ቃል አልተጠቀሰም፡፡ ነገር ግን በኢየሩሳሌም ይኖሩ ለነበሩት የታወቀውን ነገር፣ መለትም ይሁዳ በግምባሩ ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰንጥቆ አንጀቱ መዘርገፉን የሚናገር ነው፡፡ ለዚህ ምክንያታዊ ትንታኔ ሊሆን የሚችለው በትውፊት ሲነገር እንደ ኖረው ይሁዳ ገደላማ በሆነው በሄኖም ሸለቆ ላይ ራሱን በሚሰቅልበት ሰዓት ገመዱ ተበጥሶ ወድቆ ሊሆን ይችላል፤ ወይንም ደግሞ ሬሳው ሳይታይ ለረጅም ጊዜ ስለቆየ ገመዱ ተበጥሶ በመውደቅ ፈራርሶ ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ስፍራ ሞተ የሚል ቃል ስለሌለ እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች ይጋጫሉ ብለን ለመደምደም ከመፍጠናችን በፊት ያሉትን ምክንያታዊ ትንታኔዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልገናል፡፡

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ግጭቶች?

ቁርኣን ግጭቶች