ከቁርኣን ውስጥ የጠፉ 213 አንቀጾች!

ከቁርኣን ውስጥ የጠፉ 213 አንቀጾች!


ሙስሊም ኡስታዞች ቁርኣን አልተጨመረበትም ከላዩ ላይም አልተቀነሰም በማለት ሲጓደዱ መስማት የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን የመጀመርያዎቹ ሙስሊሞች በርካታ የቁርኣን ክፍሎች ጠፍተው መቅረታቸውን መስክረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በኡበይ ቢን ካዕብ ምስክርነት መሠረት ሱረት አል-አሕዛብ መጀመርያ “ሲወርድ” ርዝመቱ የሱረት አል-በቀራ ያህል እንደነበርና ገሚሱ ጠፍቆ አሁን ያለው ብቻ ሊተርፍ ችሏል፡-

تفسير سورة الأحزاب [ وهي ] مدنية . قال [ عبد الله بن ] الإمام أحمد : حدثنا خلف بن هشام ، حدثنا حماد بن زيد ، عن عاصم بن بهدلة ، عن زر قال : قال لي أبي بن كعب : كأين تقرأ سورة الأحزاب ؟ أو كأين تعدها ؟ قال : قلت : ثلاثا وسبعين آية : فقال : قط! لقد رأيتها وإنها لتعادل ” سورة البقرة ” ، ولقد قرأنا فيها : الشيخ والشيخة إذا زنيا فارجموهما البتة نكالا من الله والله عليم حكيم ” .

Narrated ‘Aasim ibn Bahdalah, from Zirr, who said:

Ubayy ibn Ka‘b said to me: How long is Soorat al-Ahzaab when you read it? Or how many verses do you think it is? I said to him: Seventy-three verses. He said: Only? There was a time when it was as long as Soorat al-Baqarah, and we read in it: “The old man and the old woman, if they commit zina, then stone them both, a punishment from Allah, and Allah is Almighty, Most Wise.”

ዓሲም ኢብን ባህደላህ ከአዚር ሰምቶ እንደተናገረው፡-

ኡበይ ኢብን ካዕብ እንዲህ አለኝ፡- አንተ ስታነበው ሱረት አል-አሕዛብ ምን ያህል ይረዝማል? ወይም ምን ያህል አንቀጽ ነው ብለህ ታስባለህ? ሰባሦስት አንቀጽ ነው ብዬ መለስኩለት፡፡ እርሱም ይህ ብቻ ነው? በማለት መለሰልኝ፡፡ የሱረት አል-በቀራ ያህል የሚረዝምበት ጊዜ ነበር፡፡ በውስጡም እንዲህ የሚል ነበር፡- “ጎልማሳ ወንድና ሴት ዝሙት ከፈፀሙ ሁለቱንም ውገሯቸው፤ ይህም ከአላህ ዘንድ የሆነ ቅጣት ነው፤ አላህ ሁሉን ቻይ ጥበበኛም ነው፡፡” (ሙስናድ አሕመድ ሐዲስ ቁጥር 21245)

ለአረብኛው ሐዲስ እዚህ ጋ ጠቅ ያደርጉ፡፡

ኢብን ሐዝም የተባለ ሊቅ ይህ ሐዲስ ሳሂህ መሆኑ የቀን ፀሐይ ያህል ግልፅ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ኢብን ከሢር ደግሞ ኢስናዱ የሐሰን ደረጃ እንዳለው ተናግሯል፡፡ ታላላቅ ሙስሊም ሊቃውንት ይህ ሐዲስ እውነት መሆኑን ይስማሙበታል፡፡ ሱረት አል-በቀራ (የላሚቷ ምዕራፍ) 286 አንቀፆች ያሉት ሲሆን ሱረት አል-አሕዛብ ደግሞ 73 አንቀፆች ብቻ ናቸው ያሉት ስለዚህ 213 ያህል አንቀፆች ከአላህ መጽሐፍ ውስጥ ጠፍተዋል ማለት ነው፡፡

ሙስሊም ወገኖቻችን ቁርኣን በትክክል ተጠብቋል ሲሉን ምን ማለታቸው ይሆን?

ቅዱስ ቁርኣን