መላክ ያሕዌ – ክርስቶስ በዘመነ ብሉይ የተገለጠበት መንገድ [ክፍል 4]

መላክ ያሕዌ – ክርስቶስ በዘመነ ብሉይ የተገለጠበት መንገድ [ክፍል 4]

Isaiah 48 Apologetics


ከዚህ ቀደም እንደተነጋገርነው፥ ወልድ በአምሳለ መልአክ በዘመነ ብሉይ ይገለጥ ነበር። መልአክ ያስባለውም ከአባቱ ዘንድ በመላኩ እንጂ ፍጡር በመሆኑ እንዳይደለ አይተናል። መልአክ ማለት በዕብራይስጥ መልእክተኛ ማለት ነው። ይህም ተልዕኮ ተቀብሎ የሚንቀሳቀስን የትኛውንም አካል የሚጠቅስ ቃል ነው። በዚህ ጽሑፍ ጌታ ኢየሱስ እንዴት እስራኤላውያንን ከፊት ፊት እየሄደ ከባርነት እንዳዳናቸው እንመለከታለን።

ሙሴ በሚቃጠለው ቁጥቋጦ ፊት ሲቀርብ በእሳት የተያያዘ ቁጥቋጦ ብቻ ሳይሆን አንድ ልዩ የሆነ አካል እንደተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል፦

“የእግዚአብሔርም መልአክ በእሳት ነበልባል በእሾህ ቍጥቋጦ መካከል ታየው፤ እነሆም ቍጥቋጦው በእሳት ሲነድድ ቍጥቋጦውም ሳይቃጠል አየ።” (ዘጸአት 3:2)

እዚህ ጋር እንደምንመለከተው፥ በቁጥቋጦ መካከል የተገለጠለት ልዑክ አለ። ይህ መልአክ ፍጡር መልአክ ሳይሆን ራሱ ኢየሱስ በአምሳለ መልአክ ተገልጦ ነው። ይህንንም ቀጥሎ ከቀረበው ንግግር መረዳት እንችላለን። ምክንያቱም እግዚአብሔር ሙሴን ሲያናግረው፥ እሱ ራሱ እንደተገለጠለት ለእስራኤል ልጆች ይነግራቸው ዘንድ ያዘዋልና፦

ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ፦ እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ፦ መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፥ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤ ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ በላቸው።” (ዘጸአት 3:16-17)

አስተውሉ! ከላይ ተገለጠለት የተባለው መልአኩ ሲሆን እዚህ ጋር ደግሞ ተገለጠለት የተባለው እግዚአብሔር ነው። ይህ የዚህን መልአክ ማንነት በግልጽ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም እንደተነጋገርነው፥ የመለኮት አካላዊ መገለጦች በሙሉ የወልድ ናቸው። በዚህም ስፍራ እግዚአብሔር ለሙሴ በአካል ነው የተገለጠለት። ስለዚህ በቀጥታ እግዚአብሔር በመባልም ወይም፥ በአምሳለ መልአክ የመለኮት አካላዊ መገለጦች በሙሉ የወልድ ናቸው።


ከላይ የሚገኘውን ሐሳብ ከማጠናከር አንጻር እስኪ በክለሳ መልክ እንመልከት።

ከዚህ በፊት እንደተነጋገርነው፥ ወልድ በብሉይ ኪዳን በአምሳለ መልአክ በመገለጥ የእስራኤልን ሕዝብ ያድን እና ይታደግ ነበር። ለሙሴ በዚህ መልክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገለጠለት በዚህ በዘፅአት 3 ላይ ነው። በዚህ ስፍራ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሴ እግዚአብሔርን በአካል አየው።

በጠቅላላው ምዕራፍ እንደ አምላክ ሙሴን ያናግረው የነበረው ይህ መለኮታዊ ልዑክ ሲሆን፥ ይህንንም ከንግግሮቹ መረዳት ይቻላል፦

And the angel of the LORD appeared unto him in a flame of fire out of the midst of a bush: and he looked, and, behold, the bush burned with fire, and the bush [was] not consumed.” (Exodus 3:2)

እዚህ ጋር ለሙሴ በሚታይ መልኩ የተገለጠው መልአኩ መሆኑን እናያለን። የተገለጠውም በቁጥቋጦው መካከል ነው።

ቀጥሎ ግን ምን ይላል፥ ከቁጥቋጦው መካከል እግዚአብሔር ጠራው ይላል። ከላይ በቁጥቋጦው መካከል የተገለጠው መልአኩ/ልዑኩ ሲል ከታች ደግሞ እግዚአብሔር ነው ይላል። ይህ የዚህን መልአክ ማንነት ይገልጽልናል

“And when the LORD saw that he turned aside to see, God called unto him out of the midst of the bush, and said, Moses, Moses. And he said, Here [am] I.” (Exodus 3:4)

ከዚህ የምንረዳው፥ ለሙሴ በመላው ምዕራፍ እንደ አዳኙ አምላክ የታየው ይህ መልአክ መሆኑን ነው። ይህንንም ቀጥሎ ባለው ጥቅስ እናረጋግጣለን

” ደግሞም። እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ የያዕቆብም አምላክ ነኝ አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ያይ ዘንድ ፈርቶአልና ፊቱን ሸፈነ። ” (ኦሪት ዘጸአት 3:6)

እዚህ ጋር ሙሴ እግዚአብሔርን ለማየት ፈርቶ ፊቱን እንደሸፈነ እናነባለን። እንግዲህ እግዚአብሔር በሚታይ መልኩ ባይገለጥ ኖሮ ሙሴ ለማየት ባልፈራ ነበር። ነገር ግን እግዚአብሔር በሚታይ መልኩ ስለተገለጠ ሙሴ ፈራ። አስተውሉ! ከላይ ተገለጠ፥ ታየ የተባለው ይህ መልአክ ብቻ ቢሆንም፥ ሙሴ ለማየት የፈራው እግዚአብሔርን ነው ይላል። የዚህም ምክንያት ይህ መልአክ በአምሳለ መልእክተኛ የተገለጠው ወልድ ስለነበር ነው።

ቀጥሎም ይህ መልአክ በራሱ ንግግር አምላክነቱን ይናገራል።

“ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ሰብስብ። እግዚአብሔር የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም የይስሐቅም የያዕቆብም አምላክ። መጐብኘትን ጐበኘኋችሁ፥ በግብፅም የሚደረግባችሁን አየሁ፤ ከግብፅም መከራ ወደ ከነዓናውያን ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ያቡሳውያንም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስስ አገር አወጣችኋለሁ አልሁ ብሎ ተገለጠልኝ በላቸው።” (ዘጸአት 3፡16-17)

እዚህ ጋር መልአኩ ለሙሴ ነጻ አወጣችኋለሁ ብሎ እግዚአብሔር ተገለጠለኝ ብለህ ለእስራኤል ሽማግሌዎች ተናገር ይለዋል። አስተውሉ! ቁ.3 ላይ ለሙሴ ተገለጠለት የተባለው መልአኩ ቢሆንም፥ እዚህ ጋር ተገለጠለት የተባለው እግዚአብሔር ነው። ይህ ተናጋሪው መልአክ ፍጡር መንፈስ ሳይሆን ራሱ ኢየሱስ መሆኑ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው።

ከቁ.16-17 የምንረዳው ነገር ቢኖር በመላው ምዕራፍ እንደ አምላክ ያናገረው ይህ መልአክ መሆኑን ነው። “ያለ የነበረ ነኝ” ያለውም ይህ መልአክ ነው። ምክንያቱም ከቁ.4 እስከ ቁ.17 ድረስ ያለው ንግግር፥ አንድ ወጥ የሆነ ንግግር ስለሆነ። ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ ላይ ለሙሴ የተገለጠለት መልአክ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እናረጋግጣለን። መቼም ቢሆን አብን ያለው የለም፥ ስለዚህ ልጁ ከጥንት ጀምሮ ይተርከዋል (ዮሐ፥1-18)።

 



መሲሁ ኢየሱስ