ሙሐመድ የሴት ልብስ ለባሹ!

ሙሐመድ የሴት ልብስ ለባሹ!

ወደ ዋሻ ገብቶ ከወጣ በኋላ ራሱን ነቢይ አድርጎ የሾመውን የሙሐመድን ታሪክ ስናጠና የሚያሳዝኑ፣ የሚያስቁ፣ የሚያስፀይፉ፣ የሚያስደነግጡ ብሎም የሚያስፈሩ ብዙ ታሪኮችን እናገኛለን፡፡ ሙሐመድ በባሕርዩ ብልጣብልጥ ስለነበረ አድማጮቹን በፈጣሪ ስም ማታለል ይችልበት ነበር፡፡ የሚፈፅማቸውን በርካታ ስህተቶችም አላህ እንደፈቀደለትና ለእርሱ ብቻ የተፈቀዱ እንደሆኑ ይናገር ነበር፡፡ ሙሐመድ የራሱን ስህተቶች ለመሸፈን አላህ ገለጠልኝ ካላቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡-

  • ሙሐመድ ትላንት የተናገረውን ረስቶ ዛሬ አዲስ ነገር ሲናገር ያዩ ጣዖት አምላኪያን “እዩት ይሄን ሰውዬ የሚናገረው ነገር ወጥነት የለውም” ብለው ሲሳለቁበት “አላህ ነው ያስረሳኝ፤ ሲያስረሳኝ ደግሞ ከእርሱ የተሻለውን ለማምጣት ነው” ብሎ ሰሚዎቹን አታልሏቸዋል፡፡ (ሱረቱ አል-በቀራህ – የላም ምዕራፍ 2፡106)
  • “ነቢይ ከሆንክ ምልክት አሳየን” ብለው በጠየቁት ጊዜ “አላህ ተዓምራት ቢያሳይም እናንተ ስለማታምኑ ተዓምራቱን አላሳይም ብሏል” በማለት አወናብዷል፡፡ (ሱረቱ አል-ዐንከቡት – የሸረሪት ምዕራፍ 29፡50)
  • በማደጎ ያሳደገውን የገዛ ልጁን ሚስት ቀምቶ ማግባት ሲፈልግ “አላህ ፈቅዶልኛል” ብሏል፡፡ (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33፡37)
  • “ማንኛዋንም ሴት አላህ ለእኔ ፈቅዶልኛል” ብሏል፡፡ (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33፡50)
  • “ሴቶች ሁሉ ለእኔ ተፈቅደዋል” በማለቱ ምክንያት ብዙ ውብ ያልሆኑ ሴቶች እየመጡ ሲያስቸግሩት ደግሞ ቃሉን አጥፎ “ከመጡት መካከል የፈለግካቸውን መርጠህ ማግባት ትችላለህ” ብሎኛል ብሏል፡፡ (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33፡51)
  • አንድ ሰሞን በር ላይ ቆመው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ሰዎች ሲጠሩት የተናደደው ሙሐመድ “የነቢዩ በር ላይ ቆማችሁ ለምን ትጠሩታላችሁ? እስኪወጣ አትጠብቁም?” በማለት አላህ መገለጥ አውርዷል ብሎም ነበር፡፡ አል-ሑጅራት (የስደት ምዕራፍ) 49፡4
  • በሰርጉ ቀን ምሽት ደግሞ ሰዎች ድግስ በልተው እየተጫወቱ ከቤቱ አንወጣ አሉ፡፡ ሙሐመድ ቢጠብቃቸው ቢጠብቃቸው ሰዎቹ የሚሄዱ አልነበሩም፡፡ ብልጣ ብልጡ ሙሐመድ ራሱ ወጥቶ የሚሄድ ቢያስመስልም ሰዎቹ ግን ፍንክች አንል አሉት፡፡ በዚህ ጊዜ ነው እንግዲህ የቁርጥ ቀን ደራሹ አላህ ከሰማይ ደርሶለት ከጭንቀቱ የገላገለው፡፡ እፍረተ ቢሱ ሙሐመድ “አላህ ምግብ ከበላችሁ በኋላ ወሬ እያወራችሁ ቤት ውስጥ አትቆዩ ቶሎ ሂዱ ብሏችኋል” ብሎ መገለጥ አወረደ፡፡ (ሱረቱ አል-አሕዛብ 33፡53)

እንግዲህ ከላይ ያየናቸው የሙሐመድ ፈጠራዎች ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አሁን ደግሞ ሙሐመድ አንድ ችግር ገጥሞታል፡፡ ከሚስቶቹ መካከል አይሻን አብልጦ ይወድዳት ስለነበር ከሌሎች ሚስቶቹ ዘንድ ቅሬታና ተቃውሞ ተነሳበት፡፡ ይህንንም ተቃውሞ እንዴት ማርገብ እንዳለበት መላ የጠፋው ሙሐመድ ለበርካታ ጊዜያት የሚስቶቹን አቤቱታ ችላ በማለት ባልሰማና ባላየ ለማለፍ ቢሞክርም ሚስቶቹ እንዲሁ በዋዛ የሚተዉት አልነበሩምና ለአቤቱታቸው መልስ መስጠት ግዴታ ሆነበት፡፡ ይሄኔ ነው እንግዲህ የማያልቅበት ሙሐመድ እንደተለመደው ተከታዮቹ ላይ ያላገጠው፡፡ ሐዲሱን እናንብብ፡-

ዑርዋ ከአይሻ እንደዘገበው:-

የአላህ መልእክተኛ ሚስቶች በሁለት ጎራ ተከፈሉ፡፡ አንደኛው ጎራ አይሻን፣ ሐፍሳን፣ ሳፊያንና ሳውዳን ያቀፈ ሲሆን ሁለተኛው ጎራ ደግሞ ኡም ሰላማንና ሌሎች የነቢዩን ሚስቶች ያቀፈ ነበር፡፡ የአላህ መልእክተኛ አይሻን ከሁሉም ይበልጥ ይወድዳት እንደነበር ሙስሊሞቹ ያውቁ ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ከመካከላቸው ማንኛቸውም ለአላህ መልእክተኛ ስጦታ ሊሰጡ ቢፈልጉ ነቢዩ ወደ አይሻ ቤት እስኪመጣ ድረስ ያቆዩት ነበር፡፡ እርሱም በአይሻ ቤት ሲሆን ስጦታቸውን ይልኩለት ነበር፡፡ በኡም ሰላማ ጎራ ያሉ የነቢዩ ሚስቶች በጉዳዩ ላይ ተነጋገሩና ኡም ሰላማ ወደ ነቢዩ ሄዳ ሰዎች እርሱ ባለበት በየትኛውም የሚስቶቹ ቤት ሰዎች ስጦታቸውን እንዲልኩ እንዲያደርግ እንድትነግረው ተስማሙ፡፡ ኡም ሰላማም ለአላህ መልእክተኛ ስለተወያዩት ነገር ነገረችው፡፡ እርሱም አንዳች አልመለሰላትም፡፡ ከዚያ ሌሎቹ ሚስቶቹ ስለነገሩ ጠየቋት እርሷም አንዳች አልመለሰልኝም አለች፡፡ እነርሱም በድጋሚ እንድታናግረው ጠየቋት፡፡ እርሷም በራሷ ቀን በድጋሚ ጠየቀችው፡፡ እርሱ ግን አንዳች አልመለሰላትም፡፡ እነርሱም በድጋሚ ሲጠይቋት ምንም እንዳልመለሰላት ነገረቻቸው፡፡ እነርሱም እስኪመልስልሽ ድረስ ጠይቂው አሏት፡፡ እርሷም ቀኗ በደረሰ ጊዜ ጠየቀችው፡፡ እርሱም እንዲህ አላት፡- በአይሻ ጉዳይ አታስቀይሙኝ ከአይሻ ውጭ በማንኛዋም ሴት ልብስ  ውስጥ ስሆን (ፊ ተውብ ኢምረዓህ) መለኮታዊው መገለጥ አይመጣልኝምና፡፡  ከዚያም ኡም ሰላማ አንተን በማስቀየሜ ለአላህ ንስሃ እገባለሁ አለች … (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 3 መጽሐፍ 47 ሐዲስ 755)

ከላይ ያለው ታሪክ በዚህ አያበቃም፡፡ በደል የተፈፀመባቸው ሚስቶቹ ኡም ሰላማ ምንም ለውጥ እንዳላመጣች ሲያውቁ ወደ ሙሐመድ ሴት ልጅ ወደ ፋጢማ በመሄድ ተመሳሳይ ክስ አቀረቡ፡፡ ፋጢማም ክሳቸውን ለሙሐመድ ባቀረበች ጊዜ “እኔ የምወደውን አትወጂምን?” ብሎ መለሰላት፡፡ ፋጢማም ምንም ለውጥ ሳታመጣ ቀረች፡፡ ከዚህ በኋላ የሙሐመድ የማደጎ ልጅ የዘይድ የቀድሞ ሚስቱ ዘይነብ ወደ ነቢዩ ተላከች፡፡ እርሷም እጅግ በመቆጣት ከፍ ባለ ድምፅ አይሻን እያንኳሰሰች ተናገረች፡፡ በዚህ ጊዜ ነቢዩ ትመልስላት እንደሆነ አይሻን በጎሪጥ ሲመለከታት አይሻ ዘይነብን ፀጥ እስክታሰኝ ድረስ ጮኸችባት፡፡ በዚህች ታሪክ ብቻ ሙሐመድ የፈጣሪ ነቢይ ሊሆን ቀርቶ መልካም ሥነ-ምግባር የሌለው ሰው መሆኑን ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዋና ዓላማ ግን ይህ ባለመሆኑ ለሌላ ጊዜ እናቆየው፡፡

ወደ ርዕሱ ስንመለስ ሙሐመድ አይሻን አብልጦ የሚወድዳት ለምን እንደሆነ ተናግሯል፡፡ የእርሷን ቀሚስ ሲለብስ ቁርኣን ስለሚወርድለት ነው፡፡ እስኪ ጉዳዩን በሰከነ መንፈስ እንደ ባለ አእምሮ እንመልከት፡፡ ይህ ምን የሚሉት ቀልድ ነው? የፈጣሪ መገለጥና የአይሻ ቀሚስ እንዴት ይገናኛሉ? መገለጡ የአይሻን ቀሚስ የመረጠበትስ ምክንያት ምንድነው? አስባችሁታል አዛውንቱ ሙሐመድ የታዳጊዋን ልጅ ቀሚስ ለብሶ መገለጥ ሲወርድለት?

ኡስታዞች በአረብኛ ቋንቋ ውስጥ ለመደበቅ ይሞክራሉ

እስልምና የሙሐመድን ታሪክ በሚያጠኑ ክርስቲያኖች ወሰን የሌላቸው ትችቶች ያስተናግዳል፡፡ ሙስሊም ሰባኪያን ለእነዚህ ክሶች ያላቸው ማምለጫ በዓረብኛው ማሳበብ ነው፡፡ በዚህ ታሪክ ውስጥ ልብስ የሚለው ቃል በዓረብኛ ተውብ (ثَوْبِ) ነው፡፡ የቃሉ ቀጥተኛ ፍች ቀሚስን የመሳሰሉ የሚለበሱ ልብሶችን (clothing) የሚያመለክት ቢሆንም ጉዳየን ለማድበስበስ የሚፈልጉት ሙስሊም ሰባኪያን ግነ ይህንኑ ቃል ደስ ሲላቸው “ቤት” ደስ ሲላቸው “አልጋ” ሲያሻቸው “ብርድልብስ” እያሉ ይተረጉሙታል፡፡ ይህ ሁሉ ግን ስህተት ነው፡፡  

በዚህ አውድ የተጠቀሰው ልብስ የሴት ልብስ ወይም ቀሚስ እንጂ የወንድ ልብስ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሙሐመድ በግልፅ “ከአይሻ ውጭ በማንኛዋም ሴት ልብስ  ውስጥ ስሆን” ብሏልና፡፡ ማናችንም ብንሆን የአብዱልፈታ ልብስ ከተባለ የወንድ ልብስ ነው ወደ አእምሯችን የሚመጣው፡፡ የዘይነብ ልብስ ከተባለ ደግሞ ቀሚስ ወደ አእምሯችን መምጣቱ ግልፅ ነው፡፡ ሙሐመድ ደግሞ ልብሱ የአይሻ መሆኑን ብቻ ሳይሆን የሴት ልብስ መሆኑንም በግልፅ መናገሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ ምንም ያህል ዓረብኛውን ቢያገላብጡት ለውጥ የለውም፡፡ ሙሐመድ የሴት ቀሚስ ለባሽ ነበር!

የተቃራኒ ፆታ ልበስ መልበስ በመጽሐፍ ቅዱስ የተከለከለ ነው

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይህንን ተግባር አጥብቆ ይከለክላል፡-

“ሴት የወንድ ልብስ አትልበስ፥ ወንድም የሴት ልብስ አይልበስ፤ ይህን የሚያደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና።” (ዘዳግም 22፡5)

የተቃራኒ ፆታ ልብስ መልበስ (Cross Dressing) በብዙ ባሕሎች ውስጥ ከስነ ምግባር ጉድለት የሚቆጠር ፀያፍ ድርጊት ነው፡፡ ተባዕታይና አንስታይ ፆታዎች ተለይተው የሚታወቁት አንድም በአለባበሳቸው በመሆኑ የአንድን ማሕበረሰብ ጤናማ መስተጋብር ለመጠበቅ የአለባበስ ስርዓትን ማክበር አስፈላጊ ነው፡፡

ነቢይ የተባለው ሙሐመድ ይህንን ወሳኝ ግብረ ገባዊ ስርዓት ካለማክበሩም በላይ መለኮታዊ መገለጥ የሚመጣለት በሚስቱ ቀሚስ ውስጥ መሆኑን በመናገር መለኮታዊ ልዕልናን የሚያንኳስስ ስህተት ፈፅሟል፡፡ እንደዚያ እንዲናገር ያደረገው ደግሞ በዕድሜ አነስተኛ ከሆነችው ከሚስቱ ከአይሻ ጋር መጫወት መፈለጉ እንጂ እውነት መለኮታዊ መገለጥ ቤትና ልብስ መርጦ ስለሚመጣለት እንዳልነበረ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ የግል ፍላጎቱን ለማርካት ሲል በፈጣሪ ላይ ከመሳለቁም በተጨማሪ ነቢይነቱን ተገን በማድረግ በሚስቶቹ ላይም በደል ፈፅሟል፡፡

ውድ ሙስሊሞች! እንዲህ ያለ ሰው እውነተኛ የአምላክ ነቢይ ሊሆን ይችላልን? ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ ከተባለ ሐሰተኛ ነቢይ ምን ዓይነት ሊሆን ነው? ውድ ሙስሊም


ወገኖቼ፤ ተታላችኋል! ሰባኪዎቻችሁ ስለ ሙሐመድ ማንነት እውነተኛውን ነገር እየነገሯችሁ አይደለም! እንዲህ ያለ የስነ ምግባር ጉድለትና ራስ ወዳድነት የማታገኙበትን አንድ አዳኝ ልጠቁማችሁ፡፡ እርሱም የናንተና የሙሐመድ ፈጣሪና ጌታ የሆነው የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ስለ እርሱ ለማወቅ ቅዱስ ቃሉ የሆነውን መጽሐፍ ቅዱስን ታነቡ ዘንድ አበረታታችኋለሁ፡፡ መዳኛችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው!

“መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” (የሐዋርያት ሥራ 4፡12)



ሙሐመድ ቀይ የሴት ልብስ አለመስረቁን ለማሳወቅ አላህ በቁርአኑ ውስጥ መገለጥ አወረደ? 

ነቢዩ ሙሐመድ