ሙሐመድ ቀይ የሴት ልብስ አለመስረቁን ለማሳወቅ አላህ በቁርአኑ ውስጥ መገለጥ አወረደ?

ሙሐመድ ቀይ የሴት ልብስ አለመስረቁን ለማሳወቅ አላህ በቁርአኑ ውስጥ መገለጥ አወረደ?

ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-

“ለነቢይም ሰለባን መደበቅ አይገባዉም ሰላባንም የሚደብቅ ሰዉ በትንሣኤ ቀን በደበቀዉ ነገር (ተሸክሞ) ይመጣል። ከዚያም ነፍስ ሁሉ የሥራዉን ዋጋ ትሞላለች እነርሱም አይበደሉም።” (ሱራ 3፡161)

ሱናን አቡ ዳውድ ይህ አያ የወረደበትን ምክንያት ሲያብራራ እንዲህ ይላል፡-

Narrated Abdullah ibn Abbas:

The verse “And no Prophet could (ever) be false to his trust” was revealed about a red velvet. When it was found missing on the day of Badr, some people said; Perhaps the Messenger of Allah (ﷺ) has taken it. So Allah, the Exalted, sent down “And no prophet could (ever) be false to his trust” to the end of the verse. (Sunan Abu Dawud, Book 31, Hadith 3960)

“አብዱላህ ኢብን አባስ እንዳስተላለፈው፡- ‹‹ለነቢይም ሰለባን መደበቅ አይገባዉም›› የሚለው ጥቅስ የወረደው ቀይ ከፋይ ልብስ [ብዙ ጊዜ ከሐር የሚሠራ ለስላሳ ጨርቅ] በማስመልከት ነበር፡፡ በበድር ዕለት በመጥፋቱ ምክንያት አንዳንድ ሰዎች ምናልባትም የአላህ መልእክተኛ ናቸው የወሰዱት አሉ፡፡ ስለዚህ ታላቅ የሆነው አላህ “ለነቢይም ሰለባን መደበቅ አይገባዉም” የሚለውን እስከ ጥቅሱ መጨረሻ አወረደ፡፡” (ሱናን አቡ ዳውዱ መጽሐፍ 31፣ ሐዲስ ቁጥር 3960)

—-

ሙሐመድ ቀይ የሴት ልብስ አለመስረቁን ለማሳወቅ አላህ ከዘላለም ዘመናት በፊት በመጽሐፉ ውስጥ የጻፈውን መገለጥ አወረደ ማለት ምን የሚሉት ስላቅ ነው? ቁርኣን የሙሐመድ ፈጠራ ነው!

 

ነቢዩ ሙሐመድ