መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙሐመድ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙሐመድ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ብዙ ክርስቲያኖች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እስልምናና ስለ ሙሐመድ ምን እንደሚል ቢጠየቁ የሚሰጡት ምላሽ ምናልባት “ምንም!” የሚል ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ይህ ምላሽ መጽሐፍ ቅዱስን ላጠና ሰው ስህተት መሆኑ  በቀላሉ ይገባዋል፡፡ ለዚህም ምክንያቱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በተከታዮቹ የተነገሩ ትንቢቶችና ማስጠንቀቂያዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በብዛት መገኘታቸው ነው፡፡ በርግጥ ስለ እስልምናና ስለ ሙሐመድ በቀጥታ ተጠቅሶ ማስጠንቀቂያ የተሰጠበት ቦታ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መኖሩ አከራካሪ ቢሆንም አጠቃላይ በሆነ መንገድ የተጠቀሱባቸውና ማስጠንቀቂያ የተሰጠባቸው ክፍሎች አያሌ ናቸው፡፡

ጌታ ኢየሱስ እንዲህ አለ፡-

የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” (ማቴዎስ 7፡15-20)

በሌላ ቦታ ላይ ጌታ ኢየሱስ ስለ ዓለም ፍፃሜ ምልክቶች በተናገረበት ክፍል እንዲህ ብሏል፡-

“ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ”     (ማቴዎስ 24፡11)

የክርስቶስን መስቀል በማስካድ ብዙዎችን እንደ ማሳቱ መጠን ከሙሐመድ በተሻለ ሁኔታ ከላይ የተጠቀሱት ትንቢቶች እውነት መሆናቸውን ሊያረጋግጥ የሚችል ነቢይ ነኝ ባይ ያለ አይመስለኝም፡፡ እስልምና በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንፁሃንን ደም በማፍሰስና ዓለምን በሽብር በማስጨነቅ የሐሰተኛ ነቢይ አስተምሕሮ ፍሬ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ ሙሐመድ የአንድን አምላክ ስም እየጠራ መምጣቱና ለእነርሱ የመጣውን መገለጥ እየተቃወመ ነገር ግነ በሙሴና በሌሎች ቅዱሳን ነቢያት አምላክና መንፈስ እንደተላከ መናገሩ በጎችን ለማወናበድ የተጠቀመበት ለምድ እንጂ እውነት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት፡፡

“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።” (2ቆሮ. 11፡14-15)

እስልምና የእውነተኛ ነቢያት መመዘኛ የለውም፡፡ ሙስሊሞች የሙሐመድን እውነተኛ ነቢይነት ለማረጋገጥ ለሚደረግ ምርመራ ትዕግስት የላቸውም፡፡ ከሙሐመድ በኋላ ብዙ ነቢያት ነን ባዮች የተነሱ ቢሆንም እነዚህን ወገኖች ላለመቀበል ብቸኛው መመዘኛቸው ሙሐመድ የመጨረሻው ነቢይ እንደሆነ ማመናቸው ብቻ ነው፡፡

በቁርኣን ውስጥ ነቢያትን ማመንና መቀበል እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚና በአፅንዖት ተነግሯል (4:150-151፣ 2:285፣ 3:161፣ ወዘተ.)፡፡ ነገር ግን ሁሉንም ነቢያት ማመንና መቀበል እንደሚገባ አሰልቺ በሆነ ድግግሞሽና በማስፈራርያዎች በታጀበ ሁኔታ የተነገረ ቢሆንም ስለ ሐሰተኛ ነቢያት የተሰጠ የረባ ማስጠንቀቂያ አለመኖሩ አስገራሚ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እውነተኛ ነቢያትን ማመንና መቀበል እንደሚገባ የተነገረውን ያህል ከሐሰተኞች ነቢያትም መጠንቀቅ እንደሚያስፈልግ በተደጋጋሚና በአፅንዖት ተነግሯል ዘዳ. 13, 18:20-22፣ ኤር. 5:31፣ 14:14፣ ኤር. 23:9-40፣ ኤር. 28፣ ሕዝ. 13፣ ማቴ. 24:11፣ 1ቆሮ. 14:29፣ 2ጢሞ 4:3፣ 2ጴጥ. 2:1፣ ራዕይ 2:20፣ 16:13፣ ወዘተ.)፡፡

ይህ ማስጠንቀቂያ በቀደሙት መገለጦች ውስጥ በተደጋጋሚ የተነገረ ሆኖ ሳለ የቁርኣን ደራሲ በዚህ ጉዳይ ላይ ዝምታን መምረጡ ጥርጣሬን ያጭራል፡፡ ከቀደሙት ቅዱሳት መጻሕፍት ጋር እምብዛም ትውውቅ ያልነበራቸው ተከታዮቹ ስለ ሐሰተኞች ነቢያት መኖር ማወቃቸው የእርሱን ሁኔታ በንቃት መከታተልና መመዘን እንዲጀምሩ እንደሚያደርግ ሙሐመድ አስተውሏል፡፡ የሐሰተኞች ነቢያት መኖርን ከስሌቱ ውጪ በማድረግ በሁሉም ነቢያት የማመንን አስፈላጊነት በተደጋጋሚ በመናገር በእርሱ ነቢይነት ማመን ግዴታ እንደሆነ በማስመሰል ተከታዮቹ አዙረው እንዳያስቡ አድርጓቸዋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ራሱ ንግግር ነው፡፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት በተጻራሪ ሙሐመድ ስለ ሐሰተኞች ነቢያት ዝምታን መምረጡ የሚያስተላልፈው ግልፅ መልእክት አለ፤ ሙሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ አይደለም!

 

ነቢዩ ሙሐመድ