የሙሐመድ አሟሟት ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑን ያረጋግጣል

የሙሐመድ አሟሟት ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑን ያረጋግጣል

በቁርኣን ውስጥ በተጻፈው መሠረት ሙሐመድ በአላህ ላይ የሚዋሽ ከሆነ አላህ የልቡን ስር (ደም ቅዳ) በመቁረጥ ይገድለዋል፡፡ ቁርኣን በሱረት አል-ሐቃህ ላይ እንዲህ ይላል፡-

በኛ ላይም ከፊልን ቃላት (ያላልነውን) በቀጠፈ ኖሮ፤ በኅይል በያዝነው ነበር። ከዚያም ከርሱ የልቡን ስር (የተንጠለጠለበትን ጂማት) በቆረጥን ነበር። ከእናንተም ውስጥ ከርሱ ላይ ከልካዮች ምንም አይኖሩም። (69፡44-47)

And if Muhammad had made up about Us some [false] sayings, We would have seized him by the right hand; Then We would have cut from him the aorta.

የሙሐመድ አሟሟት እንዴት ነበር? በእስላማዊ ትውፊት ውስጥ በተጻፈው መሠረት ሙሐመድ በኸይበር አይሁድ ላይ ጦር አዝምቶ ወረራ በፈፀመበት ወቅት አንዲት አይሁዳዊት ሴት የተመረዘ ምግብ አብልታው ነበር፡፡ መርዙ አደገኛ ከመሆኑ የተነሳ ከምግቡ አብዝተው ከበሉት መካከል ቢሽር ኢብን አል በራ የተሰኘ ሰው ብዙም ሳይቆይ የሞተ ሲሆን ሙሐመድ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በመርዙ ከተሠቃየ በኋላ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ (Ibn Sa’ad’s Kitab Al-Tabaqat Al-Kabir, English translation by S. Moinul Haq, Volume 2, pp. 251-252; al-Tabari’s History, Volume 8, p. 124; Sunan Abu Dawud, Book 39, Number 4498; Sahih Muslim, Book 026, Number 5430; Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 59, Number 713)

የሚገርመው ነገር ሙሐመድ የመርዙን ውጤት በራሱና በጓደኞቹ ላይ ከተመለከተ በኋላ በምግቡ ውስጥ መርዝ መኖሩን በእጁ የነበረችው የፊየል ቅልጥም እንደነገረችው መናገሩ ነው፡፡ አንዳንድ ሙስሊሞችም ይህንን ማጭበርበርያ ለሙሐመድ ነቢይነት እንደ ማረጋገጫ ተዓምር ሲጠቅሱ ይታያሉ፡፡ መርዙን ቀምሶ አይቶ፣ ከጎኑ የነበሩት ሰዎች የፊታቸው መልክ ሲቀያየርና ከንፈራቸው ሲጨማደድ ተመልክቶ “በምግቡ ውስጥ መርዝ መኖሩን የፊየል ቅልጥም ነገረችኝ” ብሎ የተናገረን ሰው ማመን መሠረታዊ የማመዛዘን ችሎታን ከማጣትም የከፋ ነው፡፡

የሆነው ሆኖ የጉዳዩ አስኳል ይህ ነው፡- ሙሐመድ በኸይበር በበላው መርዝ ምክንያት ሲሠቃይ ከኖረ በኋላ ህልፈቱ ሲቃረብ የልቡ ስር እንደተቆረጠ እንደተሰማው ተናግሮ ነበር፡-

የአላህ መልዕክተኛ በሞቱበት ህመም ተይዘው ሳሉ የቢሽር እናት ልትጎበኛቸው መጣች፤ እሳቸውም እንዲህ አሉ፦ “የቢሽር እናት ሆይ፥ በኸይበር ከልጅሽ ጋር ከበላሁት ምግብ የተነሳ የልቤ ስር እንደተቆረጠ ይሰማኛል።” (የአልጠበሪ ታሪክ ቅፅ 8፥ ገፅ 124)

The messenger of God said during the illness from which he died – the mother of Bishr had come in to visit him – “Umm Bishr, at this very moment I feel my aorta being severed because of the food I ate with your son at Khaybay.” al-Tabari’s History, Volume 8, p. 124

አይሻ እንዳወራችው፡- ነቢዩ በሞቱበት ህመም ሲታመሙ ሳሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ ነበር፤ “አይሻ ሆይ! በኸይበር ከበላሁት ምግብ የተነሳ እስከ አሁን ህመም ይሰማኛል፣ በዚህ ሰዓት ግን ከመርዙ የተነሳ የልቤ ስር እንደተቆረጠ እየተሰማኝ ነው፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ ቅፅ 5፣ መጽሐፍ 59፣ ቁጥር 713)

Narrated ‘Aisha: The Prophet in his ailment in which he died, used to say, “O ‘Aisha! I still feel the pain caused by the food I ate at Khaibar, and at this time, I feel as if my aorta is being cut from that poison.” (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 59, Number 713)

በእስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ የሰፈረውን የሙሐመድን የህልፈት ታሪክና በቁርኣን ውስጥ አላህ ተናገረ የተባለውን በማስተያየት የምንደርስበት ድምዳሜ የሚከተለውን ይመስላል፦

  1. አላህ በቁርአኑ እንደገለፀው ሙሐመድ ሐሰተኛ ሆኖ ከተገኘ የልቡን ስር በመቁረጥ ይገድለዋል።
  2. ሙሐመድ ለሞት ሲቃረብ የልቡ ስር እንደተቆረጠ ተሰምቶት ነበር።
  3. ስለዚህ በቁርኣን መስፈርት መሠረት ሙሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ ነው።

ውድ ሙስሊም ወገኖቻችን፤ ከላይ የሰፈረውን አመክንዮአዊ ድምዳሜ ያሳየናችሁ ሃይማኖታችሁን ለማብጠልጠል ወይንም ደግሞ እናንተ ነቢይ ብላችሁ የምታከብሩትን ሰው ለማንኳሰስ አይደለም። በገዛ መጻሕፍታችሁ ውስጥ የሌሉ የግል ሐሳቦቻችንን ስላልጨመርን ሃይማኖታችሁ እንደተነቀፈ ሊሰማችሁ አይገባም። ነገር ግን የሙሐመድን ነቢይነት ለማረጋገጥ በተጻፉት መጻሕፍት ውስጥ እንዲህ ያሉ አስደንጋጭ ነገሮች ስለምን ተገኙ? በማለት ትጠይቁ ዘንድ እናበረታታችኋለን። ሙስሊም ሊቃውንት እነዚህ ትውፊቶች የሙሐመድን ሐሰተኛ ነቢይነት የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ቢያስተውሉ ኖሮ በሌሎች የሙሐመድ የታሪክ ድርሳናት ላይ በፈፀሙት ሁኔታ ቆርጠው ባወጧቸው ነበር፡፡ ለምሳሌ ያህል ኢብን ሒሻም የተባለው ሙስሊም ሊቅ በኢብን ኢስሐቅ ከተጻፈው የሙሐመድ ግለ ታሪክ ውስጥ የሙሐመድን ሐሰተኛ ነቢይነት የሚያረጋግጡ ታሪኮችን ቆርጦ ማውጣቱን እንዲህ ሲል ይናዘዛል፡-

“ለመነጋገር አሳፋሪ የሆኑ ነገሮች፣ አንዳንድ ሰዎችን ሊያስጨንቁ የሚችሉ ጉዳዮችና በአል-ባካኢ [የኢብን ሒሻም መምህር] ተዓማኒ ተደርገው እንደማይቆጠሩ የተነገሩኝ ጉዳዮች እንዲወገዱ አድርጌያለሁ፡፡” (Alfred Guillaume. The Life of Muhammad, A Translation of Ibn Ishaq’s Sirat Rasul Allah; 1955, p. 691)

ውድ ሙስሊሞች፤ የሙሐመድን ሐሰተኝነት የምታውቁበትን ግልፅ ማስረጃ እግዚአብሔር አምላክ በሉኣላዊው ሥልጣኑ  ከእስልምና የሃይማኖት ሊቃውንት የቅጥፈት መቀስ ሰውሮ አቆይቶላችኋልና ንቁ!


ሙስሊሞች ለሰጡት ማስተባበያ የተሰጠውን ምላሽ ለማንበብ እዚህ ጋ ይንኩ፡፡ ዩ ቲዩብ ላይ ለማድመጥ እዚህ ጋ ይንኩ፡፡

 

ነቢዩ ሙሐመድ