ሙሐመድ ለጥቁሮች የነበረው ንቀት – በእስልምና የሰው ልጆች እኩል ናቸው የሚለውን ተረት ውድቅ የሚያደርግ ማስረጃ

መሐመድ ለጥቁሮች የነበረው ንቀት

በእስልምና የሰው ልጆች እኩል ናቸው የሚለውን ተረት ውድቅ የሚያደርግ ማስረጃ

ሙስሊም ወገኖች ብዙ ጊዜ እስልምና የሰው ልጆችን እኩልነት የሚቀበል ሃይማኖት እንደሆነ ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው፡፡ በሐጅና በሰላት ወቅት አማኞች በእኩል ሁኔታ በፈጣሪያቸው ፊት እንደሚቆሙና ምንም ዓይነት አድልዎ በሃይማኖቱ ውስጥ እንደሌለ በልበ ሙሉነት ይናገራሉ፡፡ ከዚህም አልፈው አውሮፓውያን በባርያ ንግድና በቅኝ ግዛት ዘመናት በአፍሪካ ላይ የፈፀሙትን ግፍ ከክርስትና ጋር በማያያዝ እስልምና የጥቁሮች ሃይማኖት እንደሆነ በድፍረት ሲናገሩና ክርስትናን ሲያጣጥሉ ይደመጣሉ፡፡ ይህ የፕሮፓጋንዳ ስልት በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ውጤት ሊያስገኝላቸው ቢችልም ክርስትናን ከብዙ የአውሮፓ ሀገራት ቀድማ በተቀበለችውና ክርስትናዋን ይዛ የአውሮፓን ግፍ ስትታገል በኖረችው በኢትዮጵያ ውስጥ ቦታ የለውም፡፡ ታሪክን ያጠናን እንደሆን ጥቁር ባርያዎችን ከአፍሪካ በማጋዝ ለነጭ አውሮፓውያን ሲሸጡ የነበሩትና አፍሪካንም ከአውሮፓውያን ቀድመው የወረሩት አረብ ሙስሊሞች የመሆናቸው ሃቅ ሊካድ የማይችል ነው፡፡ ጥቁሮች በአረቦች ዘንድ እንዴት እንደሚታዩ ስለሚታወቅ በዚህ ረገድ መወሻሸት አንችልም፡፡ ለምሳሌ ያህል በአረብ ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ጥቁር ተወላጆች ምን ዓይነት ግፍና መገለል እንደሚደርስባቸው ከዚህ ዘጋቢ ፊልም ማየት ይቻላል፡፡ ይህንን ርዕስ በሌላ ጽሑፍ የምንመለስበት በመሆኑ ከዚህ በላይ አንልም፡፡ ነገር ግን በአረብ ሙስሊሞች ዘንድ በጥቁሮች ላይ ለሚንፀባረቀው ዘረኝነት መነሻ የሆነውን መሐመድ ለጥቁሮች የነበረውን ዝቅተኛ አመለካከት እንመለከታለን፡፡ እስልምና በሰው ልጆች እኩልነት ያምናል የሚለውን እስላማዊ ፕሮፓጋንዳ ሐሰትነትም እናጋልጣለን፡፡

መሐመድ ለጥቁሮች ከፍተኛ ንቀት እንደነበረውና የሰዎችን ሰብዓዊ ዋጋ በቆዳ ቀለም የሚለካ ሰው እንደነበር እስላማዊ መጻሕፍት ያሳያሉ፡፡ ለምሳሌ ያህል መሐመድ እንዲህ በማለት ሰይጣንና ጥቁር ሰውን አመሳስሏል፡-

“ነቢዩ እንዲህ አሉ፡- ‹‹ሰይጣንን ማየት የሚፈልግ ሰው ነብጣል ኢብን አል-ሐሪሥን ይመልከተው!›› ጥቁር ሰው ሲሆን የተንጨባረረ ረጅም ፀጉርና ጥቁር መንጋጋዎች አሉት፡፡” Ibn Ishaq, Sirat Rasulallah, translated as, The Life of Muhammad by A. Guillaume, page 243

የጥንት ሙስሊሞች መሐመድ ጥቁር መሆኑን የሚናገር ሰው ይገድሉ ነበር፡-

“የሰህኑን ወዳጅ የነበረው አሕመድ ኢብን አቢ ሱለይመን እንዲህ አለ፡- ‹‹ማንኛውም ነቢዩ ጥቁር እንደሆኑ የሚናገር ሰው ይገደላል፡፡ ነቢዩ ጥቁር አልነበሩም››፡፡” Qadi ‘Iyad Musa al-Yahsubi, Muhammad Messenger of Allah (Ash-Shifa of Qadi ‘Iyad), translated by Aisha Abdarrahman Bewley [Madinah Press, Inverness, Scotland, U.K. 1991; third reprint, paperback], p. 375 & 387

መሐመድ ነጮች ለገነት እንደተፈጠሩና ጥቁሮች ደግሞ ለገሃነም እንደተፈጠሩ ተናግሯል፡-

“አቡ ደርዳ እንዳወራው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህ አዳምን በፈጠረ ጊዜ የቀኝ ትከሻውን መታና እንደ ምስጥ የነጡ ነጫጭ ዘሮች ወጡ፡፡ የግራ ትከሻውን ሲመታ ደግሞ እንደ ከሰል የጠቆሩ ጥቁር ዘሮች ወጡ፡፡ ከዚያም ከቀኝ ትከሻው የወጡትን ‹ገነት ትገባላችሁ ምንም ግድ የለኝም› አላቸው፡፡ ከግራ ትከሻ የወጡትን ደግሞ ‹እነዚህ ለገሃነም የተዘጋጁ ናቸው ምንም ግድ የለኝም› አለ፡፡ ይህ ሐዲስ በአሕመድ የተላለፈ ነው፡፡” (Al-Tirmidhi Hadith, Number 38; ALIM CD ROM Version) እንዲሁም  (Mishkat Al Masabih, English translation with explanatory notes by Dr. James Robson [Sh. Muhammad Ahsraf Publishers, Booksellers & Exporters, Lahore-Pakistan, Reprint 1990], Volume I, Chapter IV, Book I.- Faith, pp. 31-32)

ይህንን ሐዲስ ሙስሊም ሊቃውንት በሕትመት ላይ ካለው የአል-ትርሚዚ ሐዲስ እንዲሰረዝ ቢያደርጉም በኤሌክትሮኒክስ ሚድያ በታተመው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛል፡፡ ዕውቅ የቁርአን ሙፈሲርና የሐዲስ ሊቅ በነበረው አል-ባግሃዊ ተጽፎ በአል-ተብሪዚ በተከለሰው ሚሽካት አል-መሳቢህ በተሰኘው የሐዲስ ስብስብ ውስጥ መካተቱ ለሐዲሱ ተዓማኒነት ጥሩ ማሳያ ነው፡፡

መሐመድ ጥቁር ባርያዎች እንደነበሩት በብዙ እስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ በተደጋጋሚ ተዘግቧል፡፡ Sahih Bukhari, Volume 9, Book 91, Number 368 ጥቁር ባርያዎችንም በስጦታ ይቀበል እንደነበር ተነግሯል፡፡ Malik’s Muwatta, Book 21, Number 21.13.25

በአንድ ወቅት አንድ አረብ ባርያ በሁለት ጥቁር ባርያዎች እንደለወጠ እስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ ተጽፏል፡-

“ጃቢር ኢብን አብዱላህ እንዳስተላለፈው፡- አንድ ባርያ ወደ አላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) በመምጣት ቃል ኪዳን ያዘ፡፡ ነቢዩም ባርያ መሆኑን አላወቁም ነበር፡፡ አሳዳሪው በመምጣት ባርያው እንዲመለስለት በጠየቀ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ‹‹ሽጥልኝ›› አሉት? በሁለት ጥቁር ባርያዎችም ገዙት፡፡” Sahih Muslim, Book 10, Number 3901

ሙስሊም ወገኖች ብዙ ጊዜ እንደ መሐመድ የቅርብ ሰው የሚጠቅሱት ኢትዮጵያዊው ቢላል ኢብን ረባህ በሌላ ጥቁር ባርያ ልዋጭ በአቡበከር አማካይነት ነፃ እንደወጣ ቢነገርም (Ibn Ishaq, Sirat Rasulallah, p. 144) በተግባር ግን ነፃ ሰው ሆኖ አልኖረም፡፡ በመጨረሻም በዑመርና በአቡበከር ከመዲና ስለተባረረ ወደ ሦርያ ለመሸሽ ተገድዷል፡፡

መሐመድ ለኢትዮጵያውያን ያለውን ንቀትና ዘረኛ አመለካከት እንዲህ በማለት ገልጧል፡-

“የእናንተ መሪ ዘቢብ (የደረቀ የወይን ፍሬ) የመሰለ ጭንቅላት ያለው ኢትዮጵያዊ ቢሆን እንኳ ታዘዙት፡፡” Sahih al-Bukhari Book Number 89 Hadith Number 256

እንዲህ ያለ የዘረኝነት አመለካከት የነበረው ሰው እውነተኛ የእግዚአብሔር ነቢይ ሊሆን አይችልም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ግን እንዲህ በማለት የሰው ልጆች በሙሉ በእግዚአብሔር ፊት እኩል ዋጋ እንዳላቸው ይናገራል፡-

“አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።” (ገላቲያ 3፡28)

በእርግጥ በክርስትና የሰው ልጆች ዋጋ መሠረቱ በአምሳለ እግዚአብሔር መፈጠራቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ ሰው ይህንን የከበረ ምስል ስለተሸከመ ወንድ፣ ሴት፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ የተማረ፣ ያልተማረ፣ አካል ጉዳተኛ፣ የተሟላ አካል ያለው፣ ኃብታም፣ ድኻ፣ ወዘተ. ሳይል እኩል ዋጋ አለው፡፡

“እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” (ዘፍጥረት 1፡27)

እስልምና የሰው ልጆች በአምሳለ እግዚአብሔር እንደተፈጠሩ ስለማያምን ለሰው ልጆች ዋጋ የልኬት መሠረት የለውም፡፡ ቋሚ የሆነ የልኬት መሠረት የሌለው ነገር ደግሞ መሠረቱ ስለሚዋዥቅ በግለሰቦች አመለካከትና በሁኔታዎች ላይ ተመሥርቶ ይለዋወጣል፡፡ ለዚህ ነው በእስልምና የሰው ልጆች እኩል የማይታዩት፡፡ በእስልምና መሠረት ሙስሊሞች እንደ ሰው ያላቸው ዋጋ ሙስሊም ካልሆኑት ይበልጣል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ በሸሪኣ ሕግ የሙስሊም ደምና ሙስሊም ያልሆነ ሰው ደም እኩል አለመሆኑ ነው፡፡ እስላማዊት ሀገር ሳዑዲ አረብያ የሁሉንም ዓይነት ሰው ዘር ደም ዋጋ የሚያሳይ ዝርዝር አላት፤ “ዲያ” በመባል በሚታወቀው በዚህ ሕግ መሠረት ሙስሊም ወንድ ከሁሉ የላቀ ዋጋ አለው፣ ከዚያ ሙስሊም ሴት፣ ክርስቲያን ወንድ፣ ክርስቲያን ሴት፣ አይሁድ ወንድ፣ አይሁድ ሴት፣ ሒንዱ ወንድ፣ ሒንዱ ሴት እያለ የደረጃ ምድብ ዝርዝሩ ይቀጥላል፡፡

እንደ እስልምና አስተምሕሮ ወንዶች ከሴቶች ይበልጣሉ፡፡ ሰዎች ባርያና ጨዋ ተብለው ተከፍለዋል፡፡ “አል-ቂሳስ” ተብሎ በሚታወቀው የእስልምና የፍትህ ሥርኣት መሠረት በተመሳሳይ ፆታና ደረጃ ላይ የሌሉ ሰዎች ቢገዳደሉ ቅጣቱ እኩል አይደለም፡፡ ቁርአን እንዲህ ይላል፡-

“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በተገደሉ ሰዎች ማመሳሰል በናንተ ላይ ተጻፈ፡፡ ነጻ በነጻ ባሪያም በባሪያ ሴትም በሴት (ይገደላሉ)፡፡” (አል-በቀራ/የላሚቱ ምዕራፍ 2፡178)

እስልምና በሰው ልጆች እኩልነት ያምናል የሚለው ብሒል በመሐመድ የማይታወቅና በቁርአንም ድጋፍ የሌለው ነው፡፡

ነቢዩ መሐመድ