የሙሐመድ የሐሰት ትንቢት

የሙሐመድ የሐሰት ትንቢት

የደጃልን (የክርስቶስ ተቃሚ) መምጣት በተመለከተ የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ተከታዩን ትንቢት መናገሩ ሱናን አቡ ዳውድ በተሰኘው የሐዲስ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል፡-

ሙአዝ ኢብን ጀበል እንደተረከው፡-
ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢየሩሳሌም የምታብበው ያሥሪብ ስትፈራርስ ነው፣ የያሥሪብ መፈራረስ ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ነው፣ ታላቁ ጦርነት የሚነሳው ኮንስታንትኖፕል ተሸንፋ ስትያዝ ነው፣ የኮንስታንትኖፕል መያዝ ደግሞ ደጃል (የክርስቶስ ተቃዋሚ) ሲመጣ ነው፡፡” ነቢዩ ባቱን ወይም ደረቱን በመምታት እንዲህ አለ፡ “ይህ አንተ (ሙአዝ ኢብን ጀበል) እዚህ የተቀመጥከውን ያህል እውነት ነው፡፡” ሱናን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 37፣ ሐዲስ ቁጥር 4281

ሙአዝ ኢብን ጀበል እንደተረከው፡-
ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ታላቁ ጦርነት፣ የኮንስታንትኖፕል መያዝና የደጃል መምጣት በሰባት ወር ውስጥ ይፈፀማል፡፡” ሱናን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 37፣ ሐዲስ ቁጥር 4282

ኮንስታንትኖፕል (ቁስጥንጢንያ) በቱርክ ጂሃዳውያን ተወርራ ከተያዘች ይኸው ድፍን 500 ዓመታት አለፉ፤ ሙሐመድ የተናገረው ደጃል ግን አልመጣም፡፡ ስለዚህ ትንቢቱ ሐሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ ላለመሆኑ ይህ ግልፅ ማስረጃ አይደለምን?

ሐዲሳቱን ኦንላይን ማንበብ ከፈለጉ እዚህ ጋ ጠቅ ያድርጉ።

ነቢዩ ሙሐመድ