የሙሐመድ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ?

የሙሐመድ ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ?

ሙስሊም ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስ እንደተበረዘና ሊታመን እንደማይችል በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን የነቢያቸውን እውነተኛነት ለማረጋገጥና ለነቢይነት ጥሪው ሕጋዊ መሠረት ለመስጠት “የተበረዘ” ወደሚሉት መጽሐፍ ዘወር ማለታቸው አስገራሚ ነው፡፡ እስልምናን በማስፋፋት ላይ የተሰማሩት ሙስሊም ዳዒዎች ለህሊናቸውም ሆነ ለምሑራዊ የጥናት ደንቦች ታማኞች ባለመሆናቸው ዕውቀት የሌላቸውን ብዙሃን የሚያሳምን ምንም ዓይነት የክርክር ነጥብ ለመጠቀም ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ግባቸው እውነትን በመናገር ሰዎችን ወደ ትክክለኛው መንገድ መምራት ሳይሆን የትኛውንም አማራጭ በመጠቀም እውቀት የሌላቸውን ወገኖች በማሳመን ኃይማኖታቸው ህልውናው የተረጋገጠ እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ ይህንን ግባቸውን ለመምታት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተተነበዩትን ትንቢቶች በመውሰድ ለሙሐመድ ከመስጠት ጀምሮ ሰይፍ፣ በረሃ፣ አረብ፣ ግመል፣ ወዘተ. የተጠቀሱባቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እየፈለጉ ስለ እስልምናና ስለ ሙሐመድ የተተነበዩ ትንቢቶች አስመስሎ እስከመናገር ድረስ ያሉትን አማራጮች ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡ ከዚህም አልፎ ዶ/ር ዛኪር ናይክን የመሳሰሉ ዘመንኛ ሙስሊም “ሊቃውንት” ሙሐመድ በገለፃ መልክ ብቻ ሳይሆን በስም ተጠርቶም ጭምር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተተንብዮዋል እስከማለት ድረስ ደፍረው ሄደዋል፡፡ ማስረጃውን ደግሞ ከመኃልየ መኃልይ 5፡16 ላይ ይጠቅሱልናል፡፡ በዚህ ጽሑፋችን ይህንን አቋም በእውነት ብርሃን እንመረምራለን፡፡

ዶ/ር ዛኪርን የመሳሰሉት ሙስሊም ሰባኪያን የነቢያቸው ስም እንደተጠቀሰበት የሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በእብራይስጥ እንዲህ ይነበባል፡-

ኺኮ መምተቂም ወኹ መኽመዲም ዘህ ዶዲዘህ ረዒይ በኖት የሩሻሊም

የዚህ ትርጉም በ1954 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ዕትም እንዲህ ይነበባል፡-

አፉ እጅግ ጣፋጭ ነው፥ እርሱም ፈጽሞ ያማረ ነው እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ ውዴ ይህ ነው፥ ባልንጀራዬም ይህ ነው።

በዚህ ጥቅስ ውስጥ “ፈጽሞ ያማረ” የሚለው በእብራይስጥ “መኽመዲም” ይላል፡፡ ዶ/ር ዛኪር ናይክና ሌሎች ሙስሊም ዳዒዎች “መኽመዲም” የሚለውን የእብራይስጥ ቅፅል “ሙሐመድ” ከሚለው ሥም ጋር እንዲመሳሰል “መሐመዲም” በማለት ያነቡታል፡፡

የመጀመርያው መታወቅ ያለበት ነገር “መኽመዲም” የሚለው የእብራይስጥ ቃል ቅፅል ስም (Adjective noun) እንጂ የተጸውዖ ስም (Proper Noun) አለመሆኑ ነው፡፡ “መኽመዲም” ማለት በእብራይስጥ ቋንቋ “የሚወደድ” “የሚፈቀር” “ያማረ” “አስደሳች” “መልካም የሆነ” “የዐይን አምሮት” ማለት ነው፡፡ የዘመናችን ዝነኛ ሙስሊም ሰባኪ ዶ/ር ዛኪርና ሌሎች ሙስሊም ሰባኪያን ግን እውነትን ደፍጥጠው  በዓለም ሕዝብ ፊት የቅጥፈት ዲስኩራቸውን ሲደሰኩሩ እፍረትም ሆነ ፍርሃት አይታይባቸውም፡፡

ሁለተኛው መታወቅ ያለበት ነጥብ “መኽመዲም” በሚለው የእብራይስጥ ቃል መጨረሻ ላይ የሚገኘው “-ኢም” የሚለው ቅጥያ ብዛትን ወይም እምቅ አቅምን የሚያሳይ መሆኑ ነው፡፡ በአማርኛ እምብዛም ትርጉም ስለማይሰጥ በነጠላ ቢተረጎምም ነገር ግን ሙሽራይቱ “ውዴ” ብላ የጠራችውን የሰለሞንን ገፅታ ለማመልከት የተዘረዘሩትን ገለፃዎች ከማመልከቱ አኳያ በእብራይጥ ቋንቋ በዚህ አውድ ውስጥ ብዛትን አመላካች ነው፡፡ ስለዚህ መኽመዲም ነቢዩ ሙሐመድን እንደሚያመለክት ከተነገረ “ሙሐመድ” ሳይሆን “መሐመዶች” የሚል ግንዛቤን መያዝ ግድ ይላል፡፡ ሙስሊም ዳዒዎች ከዚህ እውነት ለመሸሽ “-ኢም” አክብሮትን እንደሚያሳይ ይነግሩናል፡፡ ዳሩ ግን እንደ አረብኛና እንደ ሌሎች ቋንቋዎች የአክብሮት ብዝሀነት በእብራይስጥ ቋንቋ ስለማይታወቅ ይህ “ምላሽ” ተቀባይነት የለውም፡፡ ስለዚህ ይህ ቃል ሙሐመድን ያመለክታል ከተባለ ስንት መሐመዶች አሉ? የሚለው ጥያቄ እንዲመለስልን እንፈልጋለን፡፡

“መኽመድ” ወይም “መኽመዲም” የሙሐመድ ስም ነው ከተባለ ቃሉ የተጠቀሰባቸው ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ለሙሐመድ የተነገሩ ትንቢቶች የማይሆኑበት ምክንያት የለም፡፡ ስለዚህ ሙስሊም ወገኖች የእንዲህ ዓይነቱን አካሄድ ትርጉም አልባነት መረዳት ይችሉ ዘንድ እስኪ ይህ ቃል በተጠቀሰባቸው ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ውስጥ በቃሉ ትርጉሞች ፋንታ ሙሐመድ የሚለውን ሥም ተክተን የሚሆነውን እንመልከት፡-

ሙሐመድ የነቢዩ ሕዝቅኤል ሚስት? የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ። የሰው ልጅ ሆይ፥ እነሆ፥ የዓይንህን አምሮት (መኽመድ) በመቅሠፍት እወስድብሃለሁ አንተም ወይ አትበል አታልቅስም እንባህንም አታፍስስእኔም በማለዳ ለሕዝቡ ተናገርሁ፥ ወደ ማታም ሚስቴ ሞተች በነጋውም እንደ ታዘዝሁ አደረግሁ።ሕዝቅኤል 2415-18

እቃ የሆነውን ሙሐመድን አጠፉ? የእግዚአብሔርንም ቤት አቃጠሉ፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር አፈረሱ፥ አዳራሾችዋንም በእሳት አቃጠሉ፥ መልካሙንም (መኽመድ) የሆነውንም ዕቃዋን ሁሉ አጠፉ።” 2ዜና 3619

ሙሐመድ ፈረሰ? አባቶቻችን አንተን ያመሰገኑበት የተቀደሰና የተዋበ ቤታችን በእሳት ተቃጥሎአል፥ ያማረውም (መኽመድ) የሆነውም ስፍራችን ሁሉ ፈርሶአል።ኢሳይያስ 6411

ሙሐመድ ተገደለ? ቀስቱን እንደ ጠላት ገተረ፥ እንደ አስጨናቂ ቀኝ እጁን አጸና፥ ለዓይንም የሚያምረውን (መኽመድ) ሁሉ ገደለ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን መዓቱን እንደ እሳት አፈሰሰ።ሰቆቃወ ኤርምያስ 24

ውድ ሙስሊም አንባቢ፤ እነዚህ የተባሉት ነገሮች ከነቢዩ ሙሐመድ ጋርይሄዳሉን?

[የሙስሊም ሰባኪያንን ስህተት ለማጋለጥና ጥቅሱ ሙሐመድን እንደማያመለክት ለማስረዳት ከላይ የተጠቀሱት ምላሾች በቂ ናቸው፡፡ ነገር ግን ሙስሊም ወገኖቻችን እንዲህ ያለውን አካሄድ ዳግመኛ እንዳያስቡት ከማድረግ አኳያ ተጨማሪ ሐሳቦችን ማከል አስፈላጊ ይመስለኛል፡፡]

የሙስሊም ሰባኪያን የሥነ ልሳን ተፋልሶ (Phonetic Fallacy)

መጽሐፍ ቅዱስ በመጽሐፈ ምሳሌ 26፡4-5 ላይ እንዲህ ይላል፡-

አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት። ለራሱ ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሰነፍ እንደ ስንፍናው መልስለት።

ይህ ቃል እንዲሁ ሲታይ የሚጣረስ ይመስላል፡፡ ነገር ግን ተቃርኖ ሳይሆን ቅርቃር (Dilemma) ነው፡፡ ለሰነፍ እንደ ስንፍናው መመለስም ሆነ አለመመለስ መዘዝ አላቸው፡፡ ለሰነፍ እንደ ስንፍናው ብንመልስለት እኛም እንደ እርሱ ሰነፎች መምሰላችን ነው፡፡ እንደ ስንፍናው ሳንመልስለት ብንቀር ደግሞ ጠቢብ የሆነ እንዲመስለው እናደርጋለን፡፡ ጠቢቡ ሰለሞን የሁለቱንም ምርጫዎች መዘዞች አስቀምጦልን ከሁለቱ አንዱን እንድንመርጥ ውሳኔውን ትቶልናል፡፡ ይህንን ጽሑፍ ሳዘጋጅ እኔም እንዲህ ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቼ ነበር፡፡ ለነዚህ ሙስሊም ሰባኪያን አስተሳሰባቸው ምን ያህል ገለባ እንደሆነ ለማሰየት ተመጣጣኝ የሆነ የመከራከርያ ሐሳብ ለማቅረብ ሳወጣና ሳወርድ “አንተ ደግሞ እርሱን እንዳትመስል ለሰነፍ እንደ ስንፍናው አትመልስለት” የሚለውን ቃል አስታወስኩኝ፡፡ የሙስሊም ሰባኪያን ክርክር ትክክል አለመሆኑን ከቃሉ ትርጉምና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጥቅም ላይ ከዋለበት ሁኔታ አንፃር ብቻ አስረድቼ ለማብቃት ሳስብ ደግሞ “ጠቢብ የሆነ እንዳይመስለው ለሰነፍ እንደ ስንፍናው መልስለት” የሚለው ቃል ሞገተኝ፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሙስሊም ሰባኪያን ክርክራቸው አይረቤ መሆኑን መረዳት ይችሉ ዘንድ የመጀመርያውን መዘዝ በመምረጥ ልጽፍ ወስኛለሁኝ፡፡ ተከታዩን ክፍል ስታነቡ በዚሁ መረዳት ይሁን፡፡

እስኪ የዶ/ር ዛኪርና የመሰሎቻቸውን “አመክንዮ” ወስደን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተጠቀሱት በሌሎች ቃላት ላይ በመተግበር የሚሆነውን እንመልከት፡፡ በእብራይስጥ ብሉይ ኪዳን ውስጥ በአነባበብ ከአረብኛ ቃላት ጋር የሚመሳሰሉ ነገር ግን የተለየ ትርጉም ያላቸው የተወሰኑ ቃላት አሉ፡፡ ከእነዚህ መካከል “አላህ” እና “አክበር” የሚሉት ከሙስሊሞች አፍ የማይጠፉ ቃላት ይገኙበታል፡፡ የትኛውንም የእብራይስጥ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ብንመለከት በእብራይስጥ “አላህ” (Allah) ማለት “ዛፍ” ማለት ሲሆን “አክበር” (Akbar) ማለት ደግሞ “አይጥ” ማለት መሆኑን እናያለን፡፡ እነዚህ ሁለቱ ቃላት ደግሞ በእብራይስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሰው እናገኛቸዋለን፡፡ ከ Strong’s Concordance የእብራይስጥ መስገበ ቃላት የተወሰደው የሁለቱ ቃላት ትርጉም እነሆ፡- 

የአላህ ትርጉም በእብራይስጥ

allah: an oak

Original Word: אַלָּה

Part of Speech: Noun Masculine

Transliteration: allah

Phonetic Spelling: (al-law’)

Short Definition: oak

ምንጩን ለማየት እዚህ ጋር ጠቅ ያድርጉ፡፡

የአክበር ትርጉም በእብራይስጥ

akbar: a mouse

Original Word: עַכְבָּר

Part of Speech: Noun Masculine

Transliteration: akbar

Phonetic Spelling: (ak-bawr’)

Short Definition: mice

ምንጩን ለማየት እዚህ ጋር  ጠቅ ያድርጉ፡፡

ስለዚህ የዶ/ር ዛኪርና የመሰሎቻቸውን አመክንዮ የተከተልን እንደሆን ሙስሊሞች “አላሁ አክበር!” በማለት ሲጮኹ “አላህ አይጥ ነው!” ወይንም “ዛፍ ትልቅ ነው!” እያሉ ነው የሚጮኹት ማለት ነው? በትርጉምም ሆነ በአነባበብ ሙሐመድ ከሚለው ሥም ጋር የማይገጥመው “መኽመዲም” የሚለው የእብራይስጥ ቃል ለሙሐመድ የተነገረ ትንቢት ነው ከተባለ ይህንኑ አመክንዮ በመውሰድ ሙስሊሞች “አላሁ አክበር!” በማለት ሲጮኹ በእብራይስጥ ቋንቋ አላህን እየተሳደቡ ነው ቢባል አያስኬድም ትላላችሁ? ሙስሊም ሰባኪያ ከእንዲህ ዓይነት እፍረት ለመዳን ይህንን አይረቤ ክርክር ማቆም ያስፈልጋቸዋል፡፡

ማጠቃለያ

የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ የፍቅር መዝሙር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚወደውን በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል ሊኖር የሚገባውን ከእጮኝነት ጀምሮ እስከ ጋብቻ ድረስ ያለውን የተቀደሰ ፍቅር የሚያሳይ መጽሐፍ ነው፡፡ በሌሎች የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ያሕዌ እግዚአብሔር በእርሱና በሕዝበ በእስራኤል መካከል ያለውን ቃልኪዳን በጋብቻ ስለመሰለው የጥንት አይሁዶች ይህንን መዝሙር ከዚህ መረዳት በመነሳት መንፈሳዊ ትርጉም ይሰጡታል፡፡ ክርስቲያኖችም ደግሞ በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው ቃልኪዳን በአዲስ ኪዳን ውስጥ በጋብቻ ስለተመሰለ ከዚሁ መረዳት በመነሳት መንፈሳዊ ትርጉም ይሰጡታል፡፡  ሙስሊም ወገኖች ግን ይህ መጽሐፍ ከሚጠቀማቸው ቃላት የተነሳ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ሊጠራ እንደማይገባው ይናገራሉ፡፡ አንዳንድ እውቀት የጎደላቸው ሙስሊም ሰባኪያንም “የብልግና መጽሐፍ ነው” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ (ሙስሊም ወንዶች በገነት ውስጥ ከብዙ ጡተ ጉቻማ ሴቶች ጋር ዝሙት እንደሚፈጽሙ የሚናገረውን ቁርአናቸውን ምን ሊሉት ይሆን? ሱራ 78፡30-33፣ ሱራ 44፡51-54፣ ሱራ 56፡34-36) ነገር ግን በዚሁ “የብልግና መጽሐፍ” በማለት በሚጠሩት መጽሐፍ ውስጥ ሙሽራይቱ የፍቅረኛዋን አፍ ጣፋጭነት በምታሞግስበት ክፍል ውስጥ ነቢያቸው እንደተጠቀሰ ሲናገሩ ማየት በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡ እነርሱ እንደሚሉት መጽሐፉ “የብልግና” መጽሐፍ ከሆነ ነቢያቸው የመጽሐፉ ማዕከል መሆኑ የባለጌዎች ቁንጮ ነው አያስብለውምን?

ሌላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንዲያስቡበት የምንፈልገው ጉዳይ ቢኖር ሙሐመድ በቁርኣን ውስጥ ስለ እርሱ እንደተተነበየ የተናገረው በቶራና በወንጌል ውስጥ መሆኑን ነው፡፡ ነገር ግን የመኃልየ መኃልይ መጽሐፍ ቶራም ወንጌልም አይደለም፡፡ ታድያ ምን እግር ጥሎት ነው እርሱ በማያውቀው መጽሐፍ ውስጥ ተጠቅሶ የተገኘው? በዚህ ግኝት ሙሐመድና አላህ ራሳቸው ሳይደነቁ አይቀሩም! ለነገሩ ሙስሊም ሰባኪያን ስለ ነቢያቸው የተተነበዩ ትንቢቶችን በሒንዱ መጻሕፍት ውስጥ እንኳ እንዳገኙ እየነገሩን ነው፡፡ ለሙስሊም ዳዒዎች ምን የሚል መጠርያ ብንሰጣቸው ይሆን ይህንን ባሕርያቸውን በትክክል የሚገልፀው? የቅጥፈታቸውን ግዝፈት በማየት ሰይጣን እንኳ ሳይታዝባቸው አይቀርም!

የእስልምናው ነቢይ ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደተተነበየ ለመናገር ብቸኛው ሰው አይደለም፡፡ ማኒ፣ ጆሴፍ እስሚዝና በሀኡላን የመሳሰሉ ሀሰተኛ ነቢያትም ተመሳሳይ ነገሮችን ተናግረዋል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡ በሙስጣቸው ግን ነጣቂ ተኩላዎች ከሆኑ ሀሰተኛ ነቢያት እንድንጠነቀቅ አዞናል፡፡ ሀሰተኞች መሆናቸውን ደግሞ በፍሬያቸው እንደምንለይ ነግሮናል (ማቴዎስ 7፡15-20)፡፡ ሙሐመድ ላለፉት 1400 ዓመታት በመራራና ገዳይ ፍሬው ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘውን እስልምና የተባለውን “ሃይማኖት” በመፍጠር በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሕዝቦች የሰቆቃ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሙሐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ መስፈርት መሠረት እውነተኛ ነቢይ የመሆን ምንም ዓይነት እድል የለውም፡፡ ከነቢይነት መስፈርቶች መካከል ሊያሟላ የሚችለው ብቸኛው መስፈርት ቢኖር ምናልባትም ሰው መሆኑ ብቻ ነው፡፡

ሙስሊም ወገኖች ሆይ፣ ለገንዘብና ለዝና በሚዋሹ አጭበርባሪዎች  እስከመቼ ድረስ ትታለላላችሁ? በእውነት የሰማይና የምድር ንጉሥ የሆነው አምላክ በእንዲህ ዓይነት ውሸት የሚከብር ይመስላችኋልን? ይህንን ጽሑፍ በእንዲህ ያለ ጠንካራ ቋንቋ ያዘጋጀሁበት ምክንያት የናንተን ስሜት ለመጉዳት ሳይሆን ሰባኪዎቻችሁ የሚመግቧችሁ ትምህርት ምን ያህል ገለባና አሳፋሪ እንደሆነ አውቃችሁ እንድትመለሱ ነው፡፡ እባካችሁን ንቁ! ጌታ እግአብሔር የልብ ዓይኖቻችሁን በመክፈት ወደ እውነት መንገድ ይመራችሁ ዘንድ የዘወትር ጸሎቴ ነው፡፡