ሙሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ

ሙሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ

(Dr. Mark Durie)

ሙሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ ከመንፈሳዊ ዕይታ አኳያ እንደ ቀላል ነገር የሚታለፍ አይደለም፡፡ በእስላማዊ ትውፊት ዘገባ መሠረት አልዋቂዲ የተሰኘ ሰው እንዳስተላለፈው ከሆነ፤ ሙሐመድ ወደ ሰው ቤት ሲገባ የመስቀል ምስል ያለበትን ማንኛውንም ነገር  ካገኘ ማጥፋት ይቀናው ነበር[1]፡፡

ሙሐመድ ለመስቀል የነበረው ጥላቻ ሥር ከመስደዱ የተነሳ ክርስቶስ ወደ ምድር በሚመለስበት ጊዜ የሙስሊሞች ነብይ በመሆን መስቀልን ከምድረ ገፅ ያጠፋል፤ ክርስትናንም ያስወግዳል ብሏል፡፡

አቡ ሁራይራ እንደዘገበው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብሏል፦ “ነፍሴ በእጁ በተያዘችው ጌታ እምላለሁ፤ በእርግጥም የማርያም ልጅ በመካከላችሁ ይወርዳል፡፡ ለሰው ልጆችም በፍትህ ይፈርዳል፡፡ መስቀልን ይሰባብራል፤ አሳማንም ይገድላል፡፡ ጂዝያ [ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም የሚከፍሉትን ግብር] ያስቀራል፡፡ (ሳሂህ አልቡኻሪ፤ የነቢያቶች ታሪክ መጽሐፍ 4፡60፡3448)

በሌላ አባባል ኢየሱስ ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ “ሦስተኛው ምርጫ” ወይንም የጂዝያ ክፍያ ይቀራል፡፡ ይህም የሚሆነው ክርስቲያኖች በግድ እንዲሰልሙ ስለሚደረግ ነው፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን ይገደላሉ፡፡

ሙሐመድ ለመስቀል የነበረውን ጥላቻ የሚጋሩ እጅግ ብዙ ሙስሊሞችን በዚህ ዘመን ማየት ይቻላል፡፡

  • እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በ1998 ዓ.ም. የገና በአል ከመከበሩ ከሁለት ቀን በፊት በፓኪስታን ፌይሳላባድ በምትገኝ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የተንጠለጠለ መስቀል በሙስሊሞች መሪ እንዲወርድ ተደርጓል[2]፡፡
  • እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በወርሀ የካቲት 18/ 2004 ዓ.ም. በአልባንያ በምትገኝ የቅዱስ እንድርያስ ቤተክርስቲያን ተመሳሳይ ነገር ስለመፈፀሙ በፎቶግራፍ ተደግፎ የቀረበ ማስረጃ አለ፡፡ እንደ ፎቶግራፍ ማስረጃው ከሆነ በጣርያው ላይ የተንጠለጠለን መስቀል አውርደው ሰባብረዋል፡፡[3] በኮሶቮ ውስጥ በሚገኙ የክርስቲያኖች የመቀበርያ ስፍራዎች መስቀሎችን በመነቃቀል አመጽ እንዲነሳም ተደርጓል፡፡[4]
  • እንደ ጎርጎርጎርዮሳውያን አቆጣጠር በሚያዝያ 2007 ዓ.ም በባግዳድ ክርስቲያኖች  በሰፈሩበት አል-ዳዎራ  በሚባል ስፍራ የሙስሊም አማጽያን ክርስቲያኖችን በቤተክርስቲያናቸው ሕንጻ ላይ የተንጠለጠሉትን በዕይታ ውስጥ ያሉ መስቀሎችን እንዲያስወግዱ መመርያ ሰጥተዋል፡፡ ይህ ደግሞ ሊሆን የቻለው የሙስሊሞች ህግ (ፈትዋ) የክርስቲያኖችን የመስቀል ምልክት መጠቀም  በጥብቅ ስለሚከለክል ነው፡፡[5]
  • በ2007 ዓ.ም. ሀማስ ጋዛን በተቆጣጠረ ጊዜ መስቀልን የማጥፋት ዘመቻ አድርጓል፡፡ ጋዛ በሚገኝ የካቶሊኮች የሴቶች ገዳምና ትምህርት ቤት ጭንብል የለበሱ ወንዶች በመገኘት አካባቢውን በማመሰቃቀል፣ ዘረፋ ያካሄዱ ሲሆን ዋና ትኩረታቸውም መስቀልን ማጥፋት ነበር፡፡ በጋዛ የሚኖር የዐይን እማኝ የሆነ ክርስቲያን እንደዘገበው ከሆነ በጋዛ ውስጥ ተሰሚነት ካላቸው ሰዎች አንደኛው የስቅለት ስእል ያለበትን መስቀል ከአንገቱ ጀምሮ በመቆራረጥ “ይህ አልተፈቀደም” ሲል እኩይ የሆነውን ድርጊት ፈጽሟል፡፡[6]
  • በጥቅምት 29/ 2007 ዓ.ም. በዕለተ ሰኞ በማሌዥያውያን ፓርላማ ውስጥ የፓርላማ አባል የሆነ ጡሀን ሰይድ ሁድ ኢድሮስ የተባለ ሰው ሃይማኖታዊ የሆኑ በቤተክርስቲያኖች ትምህርት ቤቶች ፊትለፊት የሚሰቀሉ ምልክቶችን በተመለከተ “ለሃይማኖቴ፣ ለብሔሬ፣ እንዲሁም ለሀገሬ ሀላፊነት እንደሚሰማው ሰው … እነዚህ መስቀሎች ድምጥማጣቸው መጥፋት አለበት ብዬ አምናለሁ” ሲል ቁጭቱን በአደባባይ ተናግሯል፡፡[7]
  • በህዳር 2004 ዓ.ም እንግሊዝ ሀገር የሚገኝ ቤልማርሽ የተሰኘ ማረምያ ቤት በ6 ሚሊዮን ፓውንድ የጸሎት ቤት የማሠራት እቅድ እንዳለው ገልጿል፡፡ ተቋሙ የተለያዩ ቤተ እምነቶች የሚጠቀሙበትን ጸሎት ቤት አስገንብቶ ጥቅም ላይ እንዲውል እያደረገ የሚገኝ ሲሆን በሽብር ተከስሰው የታሠሩ ሙስሊሞች ተቃውሞን በማንሳታቸው ምክንያት እነዚህ አክራሪዎች በሚጸልዩበት ጊዜ በጸሎት ቤቱ ውስጥ የሚገኙ መስቀሎች እንዲሸፈኑ ተወስኗል[8]፡፡
  • በእንግሊዝ ሌላ መስቀልን የሚያጥላላ አንድ ድርጊት ተከስቶ ነበር፡፡ የለንደን ባቡር ተቆጣጣሪ የሆነው ሙሐመድ አዛዊ የእንግሊዝን ዘውድ በደንብ ልብሱ ላይ ማድረጉ በፍጹም እንዳልተስማማው በብሶትና በንዴት ተናግሯል፡፡ እንደ ምክንያት አድርጎ ያቀረበው ደግሞ አነስ ያለና አምስት ሚሊ ሜትር የሚሆን መስቀል ስላለበት ነው፡፡ የሠራተኞችን ጉዳይ ወደ ሚከታተለው የከተማው ልዩ ፍርድ ቤት በመቅረብ  በከተማው የፖሊስ ተቋም ላይ ያለውን ተቃውሞ አሰምቷል፡፡ እንደ አገላለጹ ከሆነ “ይህ የዘር መድልዎ ነው” ሲል ተደምጧል፡፡ ክሱ ተቀባይነት ባያገኝም ከሃይማኖት አንፃር ዘውዱን ለማድረግ ፈቃደኛ ያልሆኑ  ሰዎች  ያለማድረግ ፈቃድ እንዲሰጣቸው የፖሊስ ባለስልጣኑ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡
  • የቀድሞው የካንተርበሪ ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ጆርጅ ኬሪ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ1995 ዓ.ም በሳውዲ አረቢያ ባለስልጣናት ደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን መስቀል እንዲያስወግዱ በኃይል ተጠይቀዋል፡፡ ዴቪድ ስኪድሞር “ኤጲስቆጶስ” በተሰኘ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው ከሆነ፡-

ኬሪ ከግብጽ ተነስተው ወደ ሱዳን እየበረሩ ሳለ ሳውዲ አረቢያ እንዲያርፉ አስገዳጅ ሁኔታ አጋጥሟቸው ነበር፡፡ የቀይባህር ጠረፋማ ከተማ በሆነችው ጅዳ ሲቃረቡ ኬሪ ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ምልክቶች ማለትም አንገታቸው ላይ ያጠለቁትን ጳጳስ መሆናቸውን የሚያሳየውን ዘለበትና በደረታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን መስቀል እንዲያስወግዱ ተነግሯቸዋል[9]፡፡

የቱንም ያህል መስቀል በሙስሊሞች ዘንድ የተወገዘም ቢሆን  በክርስቲያኖች ዘንድ ግን ነፃ የመውጣታችን ምልክት ሆኖ ይታያል፡፡

መስቀል፣ ተቀባይነትን ማጣትና እርቅ

በክርስቲያኖች መረዳት መሠረት የሰው ልጆች ትልቁ ችግር ኃጢኣት ነው፡፡ ኃጢኣት ደግሞ የሰው ልጆች በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጡና  እርስበርሳቸው እንዳይቀባበሉ አድርጓቸዋል፡፡  ይህ ባይተዋርነት ውጤቱ መገለልን አስከትሏል፡፡ አዳምና ሔዋን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ በመተላለፋቸው ከኤደን ገነት ተባረዋል፡፡ ስለሆነም ከእግዚአብሔር መገኘት የተገለሉ እንዲሆኑ ሆኗል፡፡ በውደቀታቸው ሳብያ ደግሞ የተረገሙ ሆነዋል፡፡

የእስራኤልን ታሪክ በምንመለከትበት ጊዜ እግዚአብሔር በሙሴ በኩል ከእርሱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲኖራቸው  ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ግን ይህንን ሐሳብ አልተቀበሉም፡፡ ይልቁኑ በራሳቸው መንገድ ተጉዘው ፍርድን በራሳቸው ላይ አምጥተዋል፡፡

በሰው ላይ የመጣውን ፍርድና በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ማጣትን ሊያሸንፍ የቻለው ቁልፍ  ነገር መስቀል ነው፡፡ ኢየሱስ ተቀባይነትን እስከማጣት ደርሶ ራሱን ዝቅ ቢያደርግም የመስቀሉ ኃይል በሰውና በእግዚአብሔር መካከል የነበረውን ግድግዳም ጭምር ማሸነፍ ችሏል፡፡ ኢየሱስ  ለዓለም ኃጢኣት ሲል ሰዎች የጎዱትን ጉዳት ከምንም ሳይቆጥር ነፍሱን አሳልፎ በመስጠት ለሁላችንም መስዋዕት ሆኗል፡፡ በዚህ ምክንያት የሰው ልጆች ጥለኞች እንዲሆኑ ያደረገው ኃይል መስዋዕት በተከፈለበት ፍቅር ተሸናፊ ሆኗል፡፡ ጌታችን ኢየሱስ በመስቀል ላይ ያሳየው ፍቅር ማንም ሰው ሊያደርገው የማይችልና እግዚአብሔር ለዓለም ሁሉ የሰጠው ስጦታ ነው፡፡

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡ (ዮሐ 3፡16)

የሰው ልጆች እግዚአብሔርን በመበደላቸው ምክንያት ኢየሱስ በመስቀል ላይ በመሞት ሊቀበሉት  የተገባቸውን ቅጣት እርሱ እንዲቀበለው ሆኗል፡፡ ይህ የሰው ልጆች ሁሉ የተገባቸው ቅጣት ደግሞ ዘላለማዊ ሞት ነው፡፡ ስለሆነም በእርሱ የሚያምኑ ሁሉ የኃጢአትን ይቅርታ ያገኛሉ፤ እንደዚሁም የዘላለም ሕይወት ወራሽ ይሆናሉ፡፡ በዚህም መንገድ ኢየሱስ በተቀጣው ቅጣት የሰው ልጆችን የቅጣት ዕዳ በመክፈል እግዚእብሔርን በማስደሰት ተቀባይነት ማጣትን ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሙሴ መጻሕፍት የመስዋዕትን ምሳሌ በምንመለከትበት ጊዜ የሚፈሰው ደም ኃጢአትን ያስተሰርይ ነበር፡፡ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ሐሳብ የሚተረግሙት የኢየሱስ ክርስቶስን በመስቀል ላይ መሞት አስፈላጊነት በሚያመለክት መንገድ ነው፡፡  በነብዩ ኢሳይያስ የባርያውን ሥቃይን አስመልክቶ የተነገረው ቃል ሐሳቡን ግልጽ ያደርገዋል፡-

የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም። በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው። እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን። እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ። ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ? ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ፤ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገኘበትም ነበር። እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል። ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሸከማል። ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ። (ኢሳይያስ 53፡3-12)

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የሮሜ መልእክቱ የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረውን ተቀባይነት ማጣት በእርቅ እንዴት እንደለወጠው ይናገራል፡-

ገና ደካሞች ሳለን ክርስቶስ ዘመኑ ሲደርስ ስለ ኃጢአተኞች ሞቶአልና፡፡ ስለ ጻድቅ የሚሞት በጭንቅ ይገኛልና፤ ስለ ቸር ሰው ግን ሊሞት እንኳ የሚደፍር ምናልባት ይገኝ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቷልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል፡፡ ይልቁንስ እንግዲህ አሁን በደሙ ከጸደቅን በእርሱ ከቁጣው እንድናለን፤ ይህም ብቻ አይደለም ፣ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን፡፡ (ሮሜ 5፡6-11)

ይህኛው የማስታረቅ ሥራ በሦስተኛ አካል የሚነሳ ማንኛውንም ክስ ያሸነፈ ነው፡፡

እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል? ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው ያው ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን  ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም? እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው? ከፍታም ቢሆን ዝቅታም ቢሆን ልዩ ፍጥረትም ቢሆንም በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ፡፡ (ሮሜ 8፡31-33፣ 39)

ምን ይሄ ብቻ! ክርስቲያኖች የማስታረቅን አገልግሎት እንዲያገለግሉ አደራ ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህም ሌሎችን ማስታረቅና በመስቀሉ የተሠራውን ሥራ በማወጅ ተቀባይነት ማጣትን ማስወገድ ነው፡፡

ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር   ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ ፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልዕክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን (ሮሜ 2ቆሮ 5፡18-20)

————————————–

[1]  W.Muir, The life of Muhammad. Volume3, p.61, note 47

[2]  Annual Report on International Relegious Freedom for 1999. US State  Department <http//www.thepersecution.net/used/us99irf.html>

[3]  ERP-KLM Info Service. Newsletter 17/3/ 2005. <http://www.Kosovo.net/news/archive/2005/ March_17/1.Html>

[4]  Jared Israel, “ Eradication of an ancient culture… The destruction of the Churches of Kosovo’.<http://emperorsclothes.com_list.htm>.

[5]  Extremists threaten Church in Baghdad’. Zenit News Service. 19 April 2007. <http://www.zenit.net/article/19414?I=english>

[6]  Fears in PA : Gaza May  turn into Taliban-style Emirate. MEMRI Special Dispatch Series 1633, Palestinian Authority / Jihad & Terriorism Studies Project, June 26, 2007. <http:// memri.net/ bin/articles.cgi? page= archives& Area=sd&ID= SP 163307> This is cited from  AL-Quds AL- Arabi (London), June 20, 2007.

[7]  The Hansard record of the Third Meething of the fourth Session of Eleventh Parliament (Dewan Rakyat) of Malasia, on Monday, 29 October 2007, PP. 143-44http://www.parlimen.gov.my/hidex/pdf/DR-29102007.pdf.

[8]  Reported by Justin Penrose,  writhing in the Sunday  Mirror  of November  7.2004. Daniel Pipes  offered  a critique  of this dission in his ‘ Londonistan  Follies’ blog http://www.danielpipes.net/blog /298.

[9]  David Skidmore . ‘Heart speaks to heart during Archbishop of Canterbury ‘s visit to Chicago.’ http://www.wfn. net /1996/06/msg 00144.htm.

ነቢዩ ሙሐመድ