ሰይጣን በሙስሊሞች አፍንጫ ውስጥ፤ እስልምና ሰው ሠራሽ ሃይማኖት መሆኑን የሚያረጋግጥ አስተምሕሮ

ሰይጣን በሙስሊሞች አፍንጫ ውስጥ

እስልምና ሰው ሠራሽ ሃይማኖት መሆኑን የሚያረጋግጥ አስተምሕሮ

እስልምና ሰው ሠራሽ መሆኑን የሚያረጋግጡ ብዙ  አስደንጋጭና አስቂኝ አስተምሕሮዎች አሉት፡፡ ከነዚህ መካከል አንዱ ሰይጣን ሌሊት በያንዳንዱ ሙስሊም አፍንጫ የላይኛው ክፍል ውስጥ ያድራል የሚለው ነው፡፡ ይህ ጉዳይ በመላው ሕዝበ ሙስሊም ዘንድ በፅኑ የሚታመን ሲሆን ተዓማኒነታቸው በተመሰከረላቸው የሱኒ እስልምና የሐዲስ መጻሕፍት ውስጥ በስፋት ተዘግቦ እናገኛለን፡፡ ከእነዚህ ዘገባዎች መካከል እስኪ ሁለቱን እንመልከት፡-

አቡ ሁራይራ እንዳስተላለፈው የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፡ “ከእናንተ መካከል ማንኛውም ሰው ጠዋት ተነስቶ ትጥበት ሲፈፅም አፍንጫውን ሦስት ጊዜ ማፅዳት አለበት፤ ምክንያቱም ሰይጣን ሌሊቱን በሙሉ በአፍንጫው የላይኛው ክፍል ውስጥ ያሳልፋልና፡፡” (ሳሂህ ሙስሊም መጽሐፍ 002፣ ቁጥር 0464)

አቡ ሁራይራ እንዳስተላለፈው የአላህ ነቢይ እንዲህ ብለዋል፡ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው ጠዋት ተነስቶ ትጥበት ሲፈፅም አፍንጫው ውስጥ ውኀ በመጨመር ሦስት ጊዜ መንፋት አለበት፤ ምክንያቱም ሰይጣን ሌሊቱን በሙሉ በአፍንጫው ውስጥ አሳልፏልና፡፡” (ሳሂህ አልቡኻሪ ቅፅ 4፣ መጽሐፍ 54፣ ቁጥር 516)

የዚህ ሐዲስ የእንግሊዘኛ ትርጉም የግርጌ ማስታወሻ እንዲህ ይላል፡-

“We should believe that Satan actually stays in the upper part of one’s nose, though we cannot perceive how…” (Dr. Muhammad Muhsin Khan, The Translation of the Meanings of Sahih Al-Bukhari, p. 312)

ትርጉም፡- “እንዴት እንደሆነ ባይገባንም ሰይጣን በትክክል በአንድ ሰው  አፍንጫ የላይኛው ክፍል ውስጥ እንደሚቀመጥ ማመን ይኖርብናል…”

በዚህ መሠረት ሰይጣን በአፍንጫ ውስጥ ማደሩ በሙስሊሞች ዘንድ ዘይቤያዊ ሳይሆን ቀጥተኛ ትርጉም ያለው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሙስሊሞች ጠዋት ጠዋት ሲታጠቡ ወይንም ለሰላት ከመቆማቸው በፊት አፍንጫቸው ውስጥ ውኀ በመጨመር ራሳቸውን ሲያስጨንቁ የሚታዩት፡፡ ይህ እምነት ሙሐመድ ስለ መንፈሳዊው ዓለም ምንም ዕውቀት እንዳልነበረው ከማሳየቱም በላይ ከባባድ ነገረ መለኮታዊና አመክንዮአዊ ጥያቄዎችን ያስነሳል፡፡ እስልምናም ለተከታዮቹ መለኮታዊ ጥበቃን ሊያረጋግጥ የማይችል ሰው ሠራሽ ሃይማኖት መሆኑን ያሳያል፡፡ ይህንን እውነታ ሊያስገነዝቡ የሚችሉ የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንደሚከተለው እናነሳለን፡-

  1. ሰይጣን ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሁሉ የሙስሊሞችን አፍንጫ መምረጡ ለምንድነው? አፍንጫ ውስጥ መቀመጥ ከቻለ እንደ ጆሮ፣ ዐይን፣ አፍና ሌሎች ስማቸውን የማንጠራቸው የሰውነት ክፍሎች ውስጥ ስላለማደሩ ሙስሊሞች ምን ማረጋገጫ አላቸው? በአፍንጫ ውስጥ ላለው ሰይጣን ፍቱን መድኃኒቱ ውኀ በመጨመር ሦስት ጊዜ መንፋት ከሆነ ሰይጣን ብልጠትን የተካነ ፍጥረት በመሆኑ ውኀ በመጨመር ሦስት ጊዜ መንፋት በማያስችሉ እንደ ጆሮ፣ ዐይንና ሌሎች ስማቸውን የማንጠራቸው የአካል ክፍሎች ውስጥ ለማደር ቢመርጥ ተዝናንቶ ይቀመጣል ማለት ነው፡፡
  2. ሰይጣን በዓለም ዙርያ በሚገኙ ሙስሊሞች ሁሉ አፍንጫ ውስጥ በአንድ ጊዜ ለማደር በሁሉም ቦታ የመገኘት ችሎታ ሊኖረው ይገባል፡፡ ነገር ግን የሁሉ ጌታ ከሆነው አምላክ በስተቀር በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ የመገኘት ችሎታ ያለው ማንም የለም፡፡ ሙሐመድ ይህንን ችሎታ ለሰይጣን መስጠቱ እንዴት ይታያል? በሙሐመድ እምነት መሠረት ሰይጣን ከአምላክ ባሕርያት መካከል አንዱን በመጋራት የአምላክ ሸሪክ ሆኗል፤ ስለዚህ ሙሐመድ ሰይጣንን ከፈጣሪ ጋር በማሻረክ በእስልምና እጅግ የከፋውን የሺርክ ኃጢአት ፈፅሟል፡፡ ሙስሊሞችም ሙሐመድ የተናገረውን በማመን የዚህ ወንጀል ተካፋዮች ሆነዋል፡፡ ይህ እጅግ አደገኛ ነገር ነው፡፡
  3. ሰይጣን በሙስሊሞች አፍንጫ ውስጥ የሚያድረው እንዲሁ ማደርያ ፍለጋ ወይንስ አንዳች ዓይነት እኩይ ተልዕኮ አለው? የሆነው ሆኖ አላህ ለምን ሰይጣን የእርሱ ባርያዎች በሆኑት በሙስሊሞች አፍንጫ ውስጥ ገብቶ እንዲቀመጥ ይፈቅዳል?
  4. ሙስሊሞች ሰይጣን አፍንጫቸው ውስጥ ገብቶ ሲቀመጥ ይታወቃቸዋል ወይንስ አይታወቃቸውም? የሚታወቃቸው ከሆነ ልምዳቸውን ቢያካፍሉን፡፡
  5. ውኀ አፍንጫ ውስጥ በመጨመር ሦስት ጊዜ መንፋት ሰይጣንን ሊያስወጣ ከቻለ ሰይጣን በውኀ ታጥቦ የሚወጣው ቁስ አካል ነው ማለት ነው? በሙሐመድ እምነት መሠረት ሰይጣን ልክ እንደ ሰው ይመገባል (Sahih al-Bukhari, Volume 5, Book 58, Number 200)፤ ይሸናል (Sahih al-Bukhari, Volume 2, Book 21, Number 245)፤ በመቀመጫው በኩል ጋስ ያስወጣል (Sahih al-Bukhari, Volume 1, Book 11, Number 582)፡፡ ሰይጣን ይህንን ሁሉ ማድረግ ከቻለ የማይዳሰስ መንፈስ ሳይሆን ቁስ አካል ነው ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ሐሰት ነው፡፡
  6. ሦስት ጊዜ መንፋት ያስፈልጋል ተብሎ በቁጥር የተወሰነው ለምንድነው? አራት ጊዜ ወይንም ሁለት ጊዜ ቢሆንስ ሰይጣኑ አይወጣም ማለት ነው? ሦስት የሚለው ፎርሙላ መሰጠቱስ ለምን ይሆን?

በእስላማዊ ሐዲሳት መሠረት ሙሐመድን ጨምሮ ሙስሊሞች ሁሉ በሰይጣን ቁጥጥር ስር ናቸው፡-

“የአላህ መልእክተኛ ሲናገሩ እንዲህ አሉ፡- ከእናንተ መካከል ሰይጣን ያልተመደበበት የለም፡፡ ሱሃባዎቹም የአላህ መልእክተኛ ሆይ በእርሰዎም ላይ ሰይጣን ተመድቦበዎታልን? ብለው ጠየቁ ሲመልሱ አዎን! ተመድቦብኛል ነገር ግን አላህ በእርሱ ላይ እረዳኝና ተቃወምኩት ከሃይሉ እኔ ነጻ ነኝ አሁን የሚያዘኝ ወደ መጥፎ ስራ ሳይሆን ወደ መልካም ስራ ነው፡፡ አብዱላህ ኢብን መሱድ የዘገበው ሐዲስ ነው፡፡” (ሳሂህ ሙስሊም 39 ፡ 6757)

ሙሐመድ እራሱ በድግምት ቁጥጥር ስር ወድቆ ሲሠቃይ እንደነበር ተዓማኒ የተባለው እስላማዊ ሐዲስ እንዲህ ይናገራል፡-

“አይሻ ስትናገር፡- የአላህ መልእክተኛ ላይ ድግምቱ ሰርቶባቸው፣ ከሚስቶቻቸው ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት ሲፈጽሙ እንደሚያደርጉት እንዲሁ ብቻቸውን ያደርጉ ጀመር፡፡ እርሳቸው ከሚስታቸው ጋር እየፈጸሙ ይመስላቸዋል፣ ግን አልነበረም፡፡ ሌላዋ ሚስታቸው ሳፍያም እንዲህ ዓይነት ተግባር የሚያስተጽመው በጣም አደገኛው የድግምት አይነት ነው አለች፡፡” (ሳሂህ አል-ቡኻሪ 71 ፡ 660 ቅጽ 7)

ውድ ሙስሊሞች፤ የሰይጣን ማደርያ እንድትሆኑ የሚፈቅደውን “አምላክ” በመተው ለምን በሰይጣን ኃይል ላይ ሥልጣንን ወደሚሰጣችሁ የነፍሳችሁ ቤዛ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አትመጡም? በስሙ የሚያምኑ ሰዎች ሰይጣንን በሥልጣን በማዘዝ ያስወጣሉ እንጂ የሰይጣን ማደርያ አይሆኑም፡፡ ቅዱስ ቃሉ እንዲህ ይላል፡-

“ሰብዓውም በደስታ ተመልሰው፦ ጌታ ሆይ፥ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት። እንዲህም አላቸው ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ።” (ሉቃስ 19፡17-20)

ጌታ እግዚአብሔር የልብ ዐይኖቻችሁን በመክፈት በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘውን አርነት እንድትጎናጸፉ ይረዳችሁ ዘንድ የዘወትር ጸሎታችን ነው፡፡

 

ነቢዩ ሙሐመድ