ረመዳን እንደተለመደው በሽብር ተጀመረ – በምድረ አፍጋኒስታን 18 ሰዎች በግፍ ተገድለዋል

ረመዳን እንደተለመደው በሽብር ተጀመረ – በምድረ አፍጋኒስታን 18 ሰዎች በግፍ ተገድለዋል

የሙስሊሞች ቅዱስ ወር የኾነው ረመዳን በተጀመረበት በዛሬው ዕለት ሙስሊም አሸባሪዎች በአፍጋኒስታን ውስጥ የ18 ሰዎችን ሕይወት በማጥፋት ቅዱሱን ወር ተቀብለውታል፡፡ ኾስት በተሰኘ የአፍጋኒስታን ግዛት ውስጥ በደረሰው በዚህ የአጥፍቶ መጥፋት ጥቃት ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 6 ሰዎች መቁሰላቸውም ተነግሯል፡፡ ሙስሊም ወገኖች “ሰይጣን የሚታሠርበት” እንደኾነ በሚናገሩለት በዚህ ወር ውስጥ ከየትኛውም ወር በበለጠ ሁኔታ አሸባሪዎች የንፁኀንን ደም ያፈስሳሉ፡፡ ባለፈው ዓመት የረመዳን ወር በዓለም ዙርያ በተለያዩ አገራት በደረሱት የሽብር ጥቃቶች ከ800 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ አይኤስ የተሰኘው አረመኔ እስላማዊ የሽብር ቡድን ሙስሊም ወገኖች በዚህ ወር ሙስሊም ባልሆኑት ላይ ሙሉ ጦርነት እንዲከፍቱ በዋዜማው ጥሪ አድርጓል፡፡ በዚህ ሳብያ ስጋት ያደረባቸው በሙስሊም አገራት የሚኖሩ ክርስቲያኖች የጸሎት ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡ እግዚአብሔር አምላክ የሞት ጥላ ያንዣበበባቸውን ንፁኀን ወገኖች ሁሉ ከዚህ ደም አፍሳሽ መንፈስ እንዲታደግ ቅዱሳን እንዲጸልዩ መልእክታችንን ለማስተላለፍ እንወዳለን፡