በእርዳታ ስም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕፃናትን የማስለም ተግባር በጎዴ

በእርዳታ ስም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕፃናትን የማስለም ተግባር በጎዴ

ይህ አሳሳቢ ሪፖርት በተነባቢነቱ ሁለተኛ ደረጃ ላይ በተቀመጠው ኤልሙንዶ በተሰኘው የስፔን ጋዜጣ ከወጣ ሰንብቷል። መረጃው ብዙ ስፓኛውያን ክርስቲያን አንባቢያንን ያስደነገጠ ቢሆንም የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ያገኘ አይመስልም፡፡

“የተዋሕዶ ሕፃናትን በመስረቅ ከእግዚአብሔር እየነጠቋቸው ነው!” በማለት ሁለት የኦርቶዶክስ ቀሳውስት የድርጊቱን አሳሳቢነት በምሬት ገልጸዋል። “ይህ ጉዳይ በተልይም የወንጀሉን ተባባሪዎች አውሮፓውያኑንና ኢትዮጵያውያኑን ጨምሮ ሁላችንንም በጥብቅ ሊያሳስበን ይገባል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ተጠያቂዎች ያደርገናል” በማለት ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

ይህ ሁሉ ጉድ የሚፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙት ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የእጓለ ሙታን መንደሮች ውስጥ ነው። በዚህ የማስለም መርሃ ግብር፡-

  • ሠላሳ የሚሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕፃናት ወደ እስልምና እንዲቀይሩ ተገድደዋል፡፡
  • የክርስቲያን አገር እንደሆነች የሚነገርላት ኦስትርያ በአንድ መንደር ውስጥ አንድ መስጊድ ገንብታለች፡፡ የመንደሩ አስተዳዳሪ ጣልያናዊ ሲሆን ገንዘብ ለጋሾቹ አውሮፓውያን ናቸው፡፡

እነዚህ ሕፃናት ወደ ማሳደጊያዎቹ ሲገቡ በአክራሪነት አስተሳሰብ እንዲጠመቁ እየተደረጉ ናቸው። 

ሠላሳ የሚሆኑ ክርስቲያን ሕፃናት እስልምናን እንዲቀበሉና በቀን እስከ አምስት ሰዓት ድረስ በመንደሩ መስጊድ ውስጥ እንዲጸልዩ ይገደዳሉ።

ዜናው ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣው እ.ኤ.አ በ 2014 ነበር። አባ ፍሬው የተሰኙ የአካባቢው ካህን ክርስቲያን ልጆችን፣ ወጣቶችንና ጎልማሶችን እስላም ለማድረግ ሤራ መጠንሰሱን ለኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የበላይ አለቆቻቸው አስቀድመው ማስጠንቀቂያ ልከው እንደ ነበር ተናግረዋል።

አደጋው ያንዣበበው በሶማሌ ክልል በጎዴ ከተማ በአስራ ሁለት የአልዲያስ ኢንፋንቲል ድርጅት መጠለያዎች ውስጥ ተከፋፍለው በሚገኙ መቶ ሃያ ህፃናት ላይ ነው። ተንከባካቢና አሳዳጊና የእንጀራ እናት ሆነው ልጆቹን የሚነከባከቡት ሶማሊያውያን አክራሪ ሙስሊሞች ናቸው።

አስገራሚው ነገር አንድ የኦስትሪያ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሕፃናቱን ለማስለም የታለመ መስጊድ መገንባቱ ነው። በተጨማሪም መስጊዱ እንደ ቁርኣን ትምሕርት ቤት ወይም መድረሳ ሆኖ ያገለግላል። በዚህ መስጊድ ክርስቲያን ሕፃናቱ በቀን አምስት ጊዜ እንዲሰግዱ ብሎም የቁርኣን ሱራዎችንና ተጨማሪ ጥቅሶችን እስኪደክማቸው ድረስ እንዲያነበንቡና በቃላቸው እንዲሸመድዱ ይገደዳሉ። የሕጻናቱ መንደር በሚገኝበት ቦታ ያሉ ባለስልጣናት መስጊድ የሚለውን ስም በይሉኝታ በማለሳለስ “የጸሎት ቤት“ ብለው ሊጠሩት መርጠዋል።

አባ ፍሬውና አጋራቸው ሕይወታቸው ለአደጋ የተጋለጥች ብትሆንም ስለ ሕጻናቱ አሳዛኝ ሁኔታ ለሚመለከታቸው የበላዮቻቸው ከማስታወቅ ወደ ኋላ አላሉም። እንደርሳቸው ከሆነ እስከ ሠላሳ የሚሆኑ ሕጻናት በመስጊዱ ግፊት ወደ እስልምና እንዲገቡ ተገድደዋል። በጎዴ የ ኤስ.ኦ.ኤስ. የህፃናት መንደሮች ውስጥ ምን ዓይነት ጉድ እየተካሄደ እንዳለ ለሦስት ዓመታት ያህል ድምጻቸውን ከማሰማት ወደ ኋላ አላሉም። “ስለተሰረቁት በጎቼ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ ልጆቼ ተሠርቀዋል፣ ለእምነታቸው በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂው እኔ ነኝ!” በማለት አባ ፍሬው እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። “ሙስሊሞቹ አደጋ ሊጥሉብኝ እንደሚችሉ ቢሰማኝም ለጠፉት በጎቼ ጥብቅና ለመቆም ደሜን ለማፍሰስ ፈቃደኛ ነኝ። ልጆቼን ለመከላከል ዝግጁ ካልሆንኩ በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ እኔ ነኝ ለነፍሳቸው ተጠያቂ የምሆነው።

ነገር ግን የድኽነት ስሜት ይሰማኛል፣ ጥንካሬም ጎድሎኛል፣ ማንም ሊሰማኝ ፈቃደኛ አይደለም፣ ወደ ህፃናቱ መንደር ውስጥ እንድገባና ከተዋሕዶ ልጆቼ ጋር እንድነጋገር እንኳን አይፈቅዱልኝም።” ብለዋል አባ ፍሬው።

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያን ሆነው ወደ ህፃናት መንደ መጡትና ወደ “እስልምና” እንዲቀየሩ ተገደዱት ወላጅ አልባ ልጆ ስም መካከል በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

  • ንዋሜ ደጀኔ
  • ጃፈር አቢቹ
  • ኒሞሆ አቢቹ
  • ሰላም ያዬ
  • ቤዛዊት
  • ሊዲያ
  • መስከረም
  • ብሩክ
  • ብርቱካን
  • ሃይማኖት
  • ሃሊዩ
  • ነፃነት
  • ዮርዳኖስ
  • ናርዶስ

አሁን ግን የሙስሊም ስሞች ተሰጥቷቸዋል፣ ዘራቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል፤ ከሌሎቹ ቤተሰቦቻቸው ጋር፦ ከአያቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸው እና ከሌሎች ዘመዶቻቸው ጋር ግኑኝነት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ዘመዶቻቸው አልፎ አልፎ ለመጠየቅ ሲመጡ ሙስሊሞቹ “ሞግዚቶቻቸው” አይነጠሏቸውም፤ ምክኒያቱም ከክርስቲያን ዘመዶቻቸው ጋር ለብቻቸው እንዲሆኑ አይፈቅዱላቸውምና ነው።

አባ ፍሬው እንዲህ ብለዋል፦ “እርግጠኛ ነኝ ለ ኤስ.ኦ.ኤስ. (SOS) የሕፃናት መንደሮች ገንዘብ የሚሰጡ የውጭ ሰዎች በአብዛኛው ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን የእነርሱን ድጋፍ የሚቀበሉ ወገኖች ልጆቻቸውን ለአክራሪ እስልምና አሳልፈው እየሰጧቸው እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም።”

በእነዚህ መንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች (NGO) አማካኝነት በተቋቋሙት የሕፃናት መንደሮች ምን ዓይነት ጉድ እየተሠራ እንድሆነ ለማጣራት የስፔይን ኤስ ኦ ኤስ መንደሮች መርማሪ ቡድን በቦታው ተግኝቶ ነበር። ከገንዘብ ለጋሾቹ መካከል፦ ስፔይን፣ አውስትርያ እና ጣልያን ይገኙበታል። የጎዴን የህፃናት መንደር የሚያስተዳድረው ጣልያናዊው ክላውዲዮ ክሮቼ ይሰኛል።

ምንጭ: El Mundo