ጥቃቱ የደረሰው የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኝ አሪያና ግራንዴ የሙዚቃ ድግሷን በማገባደድ ሕዝቡ አካባቢውን ለቆ ለመውጣት እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ሰዓት ላይ ነበር፡፡ ፖሊስ የአጥፍቶ መጥፋት የቦምብ ጥቃት እንደሆነ በገለጸው በዚህ ጥቃት ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ 19 ሰዎች ሞተው 60 ቆስለዋል፡፡ ጥቃቱ ሲፈፀም 20,000 የሚሆኑ ሰዎች በቦታው ተሰብስበው እንደነበር የተገለጸ ሲሆን በ 7/ 2005 (እ.ኤ.አ) በለንደን ከተማ ላይ ከተፈጸመውና ለ52 ሰዎች ሕይወት መቀጠፍ ምክንያት ከሆነው ጥቃት ከጥሎ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡ የአውሮፓ አገራት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለእስላማዊ ሽብር ጥቃቶች በከፍተኛ ሁኔታ እየተጋለጡ መምጣታቸው ይታወቃል፡፡ ዘገባው የሲኤንኤን እና የፎክስ ኒውስ ነው፡፡
እስላማዊ የሽብር ጥቃቶች በንጹኀን ላይ ለምን እንደሚፈጸሙ ማወቅ ይፈልጋሉን? ይህችን ቡክሌት አውርደው ያንብቡ፡፡ ለማውረድ እዚህች ጋር ጠቅ ያድርጉ፡፡