የመጀመርያው ፍጡር ወይንስ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ? – የኡስታዝ ወሒድ ቅጥፈት ሲጋለጥ

የመጀመርያው ፍጡር ወይንስ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ?

ይህንን ርዕሰ ጉዳይ ከዚህ ቀደም ሰፊ ማብራርያ የሰጠንበት ቢሆንም ወሒድ የተሰኘ አንድ አብዱል እንደ ልማዱ ጥቅስ ከጥቅስ እያማታ የጻፈውን ጽሑፍ ስለተመለከትን ሙስሊም ሰባኪያን በዚህ ሙግት ላይ እስከ ወዲያኛው ተስፋ እንዲቆርጡ ማድረግ አስፈላጊ መስሎ ታይቶናል፡፡

ወሒድ የመጽሐፍ ቅዱስን የመጀመርያ ቋንቋዎች በአቦ ሰጡኝ እየጠቃቀሰ አንባቢን ለማሳሳት ጥረት አድርጓል፡፡ ይህ ሰው ግሪኩን ደጋግሞ በመጥቀስ ምሑር የመምሰል ልማድ ያለው ከመሆኑ አንፃር ምንም ዓይነት የግሪክ ቋንቋ ዕውቀት እንደሌለው የሚያሳዩ ስህተቶቹን በመጠቆም እንጀምራለን፡፡ በግሪክ ቋንቋ ትምሕርት ውስጥ ቀዳሚው ጉዳይ ፊደላቱን መለየትና ማንበብ መቻል ነው፡፡ ወሒድ ግን በእንግሊዝኛ የተጻፉ አነባበቦችን ቢጠቀምም ፊደላቱን ለይቶ አያውቃቸውም፡፡ ለዚህ ማሳያው በዚህም ሆነ በሌሎች ጽሑፎቹ ውስጥ እንደሚታየው የግሪክ ቃላትን ከጠቀሰ በኋላ አነባበቦቹን በአማርኛ ሲያስቀምጥ ከሞላ ጎደል በሁሉም አጋጣሚዎች ስህተት መሥራቱ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኙትን እንመልከት፡-

  • ἔκτισέν (ኤክቲሴን) የሚለውን “ኪትዞ” ብሎታል፡፡
  • πρωτότοκος (ፕሮቶቶኮስ) የሚለውን “ፕሮቶኮስ” ብሎታል፡፡
  • πάσης (ፓሴስ) የሚለውን “ፓሰስ” ብሎታል፡፡
  • κτίσεως (ክቲሴዎስ) የሚለውን “ክቲሶስ” ብሎታል፡፡

ፊደላቱን ለይቶ ባላወቀበትና በላቲን ፊደላት የተጻፈውን ትራንስሊትሬሺን (አነባበብ) እንኳ በትክክል ማንበብ ባልቻለበት ሁኔታ የነቃ የበቃ ሊቅ መስሎ ለመታየት መሞከሩ አስቂኝ ነው፡፡ ቀላል በሆነው ጉዳይ እንዲህ ለስህተት ከተዳረገ በዋናው ጉዳይ ምን ያህል ሊሳሳት እንደሚችል አስቡት፡፡ ለማንኛውም ወደ ሙግቱ እንግባ፡፡ የክርስቶስን ልደት በተመለከተ የተረቶች መጽሐፍ ከሆነው ከቁርአን አንድ ጥቅስ ከጠቀሰ በኋላ እንዲህ ሲል ሙግቱን ያቀርባል፡-

ወሒድ

325 ድህረልደት በኒቂያ ጉባኤ በአትናቴዎስ እና በአርዮስ መካከል ውይይት ከተደረገ በኃላ የአርዮስ ተከታዮች ከዐበይት የሥላሴያውያን መሪዎች ግዝት እና ግዞት ደርሶባቸዋል፤ የአርዮስ እሳቤ ባዕዳና እንግዳ ኢያም ያረጀና ያፈጀ እሳቤ ሳይሆን ጳውሎሳዊ እሳቤ ነው፤ በግሪክ ኮይኔፕሮቶኮስ” πρωτότοκος ማለትበኵር” “ቀዳማይ” “መጀመሪያማለት ነው፦

ቆላስይስ 115 እርሱም የማይታይ አምላክ መልክ እና *”የፍጥረት ሁሉ በኵር ነው”* who is the image of the invisible God, the firstborn of all creation; (English Revised Version)

ግሪክ፦ πρωτότοκος πάσης κτίσεως

ፓሰስ” πάσης ማለትሁሉማለት ነው፤የፍጥረት ሁሉ በኵርየሚለው ሃይለቃል ይሰመርት፤ክቲሶስ” κτίσεως ማለትፍጥረትማለት ነው።ፍጡርበነጠላፍጥረትበብዜት ነው፤ የፍጥረት ሁሉ በኵር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው።

መልስ

ብኩርና በመጽሐፍ ቅዱስ በጊዜ ቀዳሚነትን ብቻ ሳይሆን የበላይነትን፣ ገዢነትን፣ ተወዳጅነትን፣ ወዘተ. የሚያመለክት በመሆኑ የቃሉ ትርጉም መታየት ያለበት እንደየ አውዱ እንጂ በጥሬ ትርጉሙ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ያህል ከታናናሽ ነገዶች መካከል አንዱ የሆነው ኤፍሬም “በኩር” ተብሏል (ትንቢተ ኤርምያስ 31:9)፡፡ ዳዊትም ከቤቱ የሁሉ ታናሽና የእስራኤል ሁለተኛው ንጉሥ ቢሆንም “በኩር” ተብሏል (መዝ. 89፡20፣ 27)፡፡ ስለዚህ  ቆላስይስ 1፡15 ላይ ክርስቶስ “በኩር” የተባለበትን ምክንያት ለመረዳት በጥቅሱ አውድ ውስጥ ቃሉ ጥቅም ላይ የዋለበትን ሁኔታ ማጤን አስፈላጊ ነው፡፡ ጥቅሱ ባጠቃላይ ስለ ክርስቶስ ፈጣሪነት ይናገራል፡-

“እርሱም የማይታይ አምላክ ምሳሌ ነው። የሚታዩትና የማይታዩትም፥ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ጌትነት ወይም አለቅነት ወይም ሥልጣናት፥ በሰማይና በምድር ያሉት ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኵር ነው። ሁሉ በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።” (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:15-16)

በጥቅሱ ውስጥ “ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋልና” ἐν αὐτῷ ἐκτίσθη τὰ πάντα (ኤን አውቶ ኤክቲስቴ ታ ፓንታ) ተብሏል፡፡ ሁሉም (πάντα ፓንታ) የተፈጠሩት በእሱ ከሆነ፣ ኢየሱስ ፍጥረት ውስጥ የለም ማለት ነው።  “ሁሉንም ፈጠረ” ተብሎ እራሱ ፍጡር ነው ከተባለ  እራሱንም ፈጥሯል እያልን ነው ማለት ይሆናል። ይህ ደግሞ ኢ-አመክንዮአዊ ነው፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ በኩር የተባለው የበላይና ወራሽ መሆኑን ለማመልከት እንጂ የመጀመርያው ፍጡር መሆኑን ለማመልከት አይደለም (ሮሜ 8፡17፣ 29፣ ዕብራውያን 1፡1-3፣ ማርቆስ 12፡6-8)፡፡ ትክክለኛው ፍቺ ኢየሱስ በፍጥረታት ሁሉ ላይ ሥልጣን ያለው የሁሉ የበላይ ነው የሚል ነው። ለበለጠ ማብራርያ ቀደም ሲል በርዕሱ ላይ የጻፍነውን መጣጥፍ በድረ ገጻችን ላይ ማንበብ ይቻላል፡፡

በማስከተል ወሒድ የማይገናኙ ጥቅሶችን በማገናኘት እንዲህ ሲል ጽፏል፡-

ወሒድ

ይህንን ናሙና ለመረዳት አንድ ተመሳሳይ ሰዋስው እንይ፦

ራእይ 15 ከታመነውም ምስክር *”የሙታንም በኵር”* and from Jesus Christ, who is the faithful witness, the firstborn of the dead, (English Revised Version)

ግሪክ፦ πρωτότοκος τῶν νεκρῶν

ኔክሮን” νεκρῶν ማለትሙታንማለት ነው።ሙትበነጠላሙታንበብዜት ነው፤ የሙታን በኵር ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኩር ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ካልሆነ ምን ማለት ነው? እንቀጥል፦

1 ቆሮንቶስ 1520 አሁን ግን *”ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል”*

ግሪክ፦ Νυνὶ δὲ Χριστὸς ἐγήγερται ἐκ νεκρῶν, ἀπαρχὴ τῶν κεκοιμημένων.

በኵርየሚለው የግሪኩ ቃልአፕአርኬ” ἀπαρχὴ ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤አፓ” ἀπό ማለትምእናአርኬ” ἀρχή ማለትምመጀመሪያነው፤ ላንቀላፉት ሙታንመጀመሪያነው ማለት መጀመሪያ የተነሳ ማለት ከሆነ የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ ማለት መጀመሪያ የተፈጠረ ማለት ነው፦

መልስ

የጥቅሶቹ አውድ ለየቅል በመሆኑ ድምዳሜው በእጅጉ የተሳሳተ ነው፡፡ ቆላስይስ ላይ የሚገኘው ጥቅስ ክርስቶስ ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪ መሆኑን ከገለጸ በኋላ የፍጥረት የበላይና ገዢ መሆኑን ለማመልከት “በኩር” አለው፡፡ እርሱ የጠቀሳቸው ጥቅሶች ደግሞ በመጨረሻው ዘመን ለብሰን በምንነሳው የትንሣኤ አካል ከሙታን አስቀድሞ የተነሳ በመሆኑ “ከሙታን በኩር” አሉት፡፡ የመጀመርያው ጥቅስ የበላይነትን የሚያሳይ ሲሆን ሁለቱ ጥቅሶች ደግሞ የጊዜ ቀዳሚነትን የሚያሳዩ ናቸው፡፡ ስለዚህ ሙግቱ ገለባ ነው፡፡

ወሒድ

ራእይ 314 አሜን የሆነው፥ የታመነውና እውነተኛው ምስክር፥ *”የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያ”* የነበረው እንዲህ ይላል፦ the beginning of the creation of God. (English Revised Version)

ግሪኩ፦ ἡ ἀρχὴ τῆς κτίσεως τοῦ θεοῦ:

የእግዚአብሔር ፍጥረት መጀመሪያየሚለው ሃይለቃል ይሰመርበት፤መጀመሪያለሚለው የገባው ቃል ልክ እንደ የሙታን መጀመሪያአርኬ” ἀρχή መሆኑ አንባቢ ልብ ይለዋል።

መልስ

አዲስ ኪዳንን ስንመለከት ἀρχή (አርኬ) የሚለው ቃል የጊዜ መቅደምን ብቻ ሳይሆን ገዢነትን ወይንም ሥልጣንንም ያመለክታል፡፡ ለምሳሌ ያህል ሉቃስ 20፡20 ላይ “ሲጠባበቁም ወደ ገዢ ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት …” በሚለው ቃል ውስጥ “ሥልጣን” የሚለው “አርኬ” ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ 1ቆሮንቶስ 15፡24 ላይ “ሥልጣን” ተብሏል፡፡ ሮሜ 8፡38 ላይ ይኸው ቃል “ግዛት” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ ኤፌሶን 1፡21 ላይ “አለቅነት” ተብሏል፡፡ እዚያው ኤፌሶን 3፡10 እና 6፡12 ላይ “አለቆች” ተብሎ ተተርጉሟል፡፡ ቲቶ 3፡1 ላይ “ገዦች” ተብሏል፡፡ ለዚህ ነው ራዕይ 3፡14 ላይ የሚገኘውን ቃል የአዲሱ መደበኛ ትርጉም አዘጋጆች “የእግዚአብሔርም ፍጥረት ገዢ የሆነው” በማለት የተረጎሙት፡፡ ስለዚህ ይህ ጥቅስ የክርስቶስን አምላክነት ለማስተባበል ሊጠቀስ የሚችል አይደለም፡፡ በማስከተል አሁንም የማይገናኙ ጥቅሶችን በመጥቀስ ሐሰተኛ ምስስሎሽ (false analogy) አመክንዮአዊ ተፋልሶ ፈጽሟል፡፡

ወሒድ

ሌላው የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ነው፦

ዘሌዋውያን 2726 ለእግዚአብሔር ግን የሚቀርበውን *”የእንስሳ በኵር”* ማንም ይቀድሰው ዘንድ አይቻለውም፤ በሬ ቢሆን ወይም በግ ለእግዚአብሔር ነው።

የእንስሳ በኵር ማለት ከእንስሳ የመጀመሪያው እንስሳ ማለት ከሆነ የፍጥረት በኵር ማለት ከፍጥረት የመጀመሪያው ፍጡር ማለት ነው፤

መልስ

የቃሉን ትርጉም የሚወስነው አውዱ እንደሆነ ከላይ በማስረጃ ስላረጋገጥን የተሟጋቹ ሙግት ውኀ የሚያነሳ አይደለም፡፡

ወሒድ

ፍጥረት የሚለው አዲስ ፍጥረትን ነው የሚያመለክተው ብንል ኢየሱስ የአዲስ ፍጥረት በኩር ነው፦

ሮሜ 829 *ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ* አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤

2 ቆሮንቶስ 517 ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን *”አዲስ ፍጥረት ነው”* አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

 “ሁሉም አዲስ ሆኗልየሚለዉ ይሰመርበት፤ሁሉአንጻራዊ ከሆነየፍጥረትሁሉመጀመሪያማለት የአዲስ ፍጥረት ሁሉ መጀመሪያ ማለት ነው፤

መልስ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር በመምጣቱ ምክንያት በሰብዓዊ ባሕርዩ ከኛ ጋር ተቆጥሯል፡፡ ነገር ግን እርሱ መለኮት የሆነ የእግዚአብሔር አንድያ ልጅ ነው (ዮሐንስ 3፡16)፡፡ ስለዚህ ሮሜ 8፡29 ላይ የሚገኘውን ቃል በዚህ መንገድ መረዳት ያስፈልጋል፡፡ ነገረ ክርስቶስ (ክርስቶሎጂ) እጅግ ሰፊ ጥናት በመሆኑ ጥቅሶችን እያቀጣጠሉ ወደ ጠባብ ድምዳሜ ማምራት የተሟጋቹን ዕውቀት አጠርነት ያሳያል፡፡

ወሒድ

ግን ፍጥረት የሚለው አጠቃላይ ፍጥረትን ያመለክታል ከተባለ የፍጥረት በኵር ማለት ከሁሉ አስቀድሞ የተፈጠረ ማለት ነው፦

ምሳሌ 822 *እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ* (1980 አዲስ ትርጉም)

ግዕዝ፦

ምሳሌ 822 “ፈጠረኒ እግዚእ መቅድመ ተግባሩ

ኢንግሊሽ፦

Proverbs 822 “The LORD made me as he began his planning, (International Standard Version)

ዕብራይስጥ፦

ምሳሌ 822 יְהוָה–קָנָנִי, רֵאשִׁית דַּרְכּוֹ: קֶדֶם מִפְעָלָיו מֵאָז.

ግሪክ ሰፕቱአጀንት፦

Proverbs 822 κύριος ἔκτισέν με ἀρχὴν ὁδῶν αὐτοῦ εἰς ἔργα αὐτοῦ

በተለይ በግሪኩ ሰፕቱአጀንት”LXX” ላይኪትዞ” ἔκτισέν ማለትፈጠረኝማለት ነው፤ በተመሳሳይ ዕብራይስጡቃናኒ” קָ֭נָנִי ማለትአስገኘኝማለት ነው።

መልስ

በዚህ ምዕራፍ ትርጓሜ ዙርያ ክርስቲያን ሊቃውንት አንድ ዓይነት አቋም እንደሌላቸው ይታወቃል። ጥቅሱ ለክርስቶስ ነው ብለህ የምትሟገት ከሆነ የእብራይስጡ ቃል ትርጉም አስቀድሞ የነበረን ነገር ማግኘትን ወይንም ገንዘብ ማድረግን በሚያመለክት መንገድ መተርጎም የመቻሉን እውነታ መለወጥ አትችልም፡፡ የእብራይስጥ መዝገበ ቃላት በተከታዩ መንገድ ተርጉሞታል፡-

1) to get, acquire, create, buy, possess

  1. a)(Qal)

1) to get, acquire, obtain

  1. a)of God originating, creating, redeeming His people

1) possessor

  1. b)of Eve acquiring
    c)of acquiring knowledge, wisdom

2) to buy

  1. b)(Niphal) to be bought
    c)(Hiphil) to cause to possess 

ምንጭ፡- https://www.blueletterbible.org/cgi-bin/words.pl?word=07069

ከዚህ ትርጉም እንደምንገነዘበው ማግኘት፣ መግዛት፣ ገንዘብ ማድረግ፣ የራስ ማድረግ፣ ወዘተ. በሚሉ መንገዶች መተርጎም ይቻላል፡፡ ይህም ጥበብ አስቀድሞ የነበረ እንጂ የተፈጠረ አለመሆኑን አመላካች ነው፡፡ በዚሁ በመጽሐፈ ምሳሌ ውስጥ “ቀናህ” የሚለው ቃል የጥበብን አስቀድሞ መኖር በሚያሳይ ሁኔታ ጥቅም ላይ ውሎ እናገኛለን፡፡ ለምሳሌ ያህል፡-

“ጥበብን የሚያገኝ (ቆኔህ) ነፍሱን ይወድዳል፥ ማስተዋልንም የሚጠብቅ መልካም ነገርን ያገኛል።” (ምሳሌ 19፡8)

አንተ የሚመችህን ትርጉም ስለመረጥክ እንጂ አብዛኞቹ የእንግሊዘኛ ትርጉሞች መፈጠርን በማያመለክት መንገድ ተርጉመውታል፡፡

New International Version

The LORD brought me forth as the first of his works, before his deeds of old;

English Standard Version

The LORD possessed me at the beginning of his work, the first of his acts of old.

New American Standard Bible

The LORD possessed me at the beginning of His way, Before His works of old.

New King James Version

The LORD possessed me at the beginning of His way, Before His works of old.

King James Bible

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

Christian Standard Bible

The LORD acquired me at the beginning of his creation, before his works of long ago.

Contemporary English Version

From the beginning, I was with the LORD. I was there before he began

GOD’S WORD® Translation

The LORD already possessed me long ago, when his way began, before any of his works.

New American Standard 1977

The LORD possessed me at the beginning of His way, Before His works of old.

Jubilee Bible 2000

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

King James 2000 Bible

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

American King James Version

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

American Standard Version

Jehovah possessed me in the beginning of his way, Before his works of old.

Douay-Rheims Bible

The Lord possessed me in the beginning of his ways, before he made any thing from the beginning.

Darby Bible Translation

Jehovah possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

English Revised Version

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

Webster’s Bible Translation

The LORD possessed me in the beginning of his way, before his works of old.

World English Bible

Yahweh possessed me in the beginning of his work, before his deeds of old.

Young’s Literal Translation

Jehovah possessed me — the beginning of His way, Before His works since then.

ከላይ በማስረጃ እንዳረጋገጥነው “ቀናህ” የሚለው ቃል አስቀድሞ የነበረን አካል ለመግለፅ ጥቅም ላይ መዋል የሚችል ከሆነ የእግዚአብሔር ጥበብ ፍጡር አይደለም ማለት ነው፡፡ በርግጥ የእግዚአብሔር ጥበብ ከባሕርየ መለኮታት (Divine Attributes)  መካከል አንዱ በመሆኑና የእግዚአብሔር ባሕርይ ደግሞ የማንነቱ አካል እንጂ ፍጡር ባለመሆኑ ምሳሌ 8፡22ን “ፈጠረኝ” ብሎ መተርጎም ትክክል አይደለም፡፡ የእግዚአብሔር ባሕርያት የማንነቱ መገለጫዎች በመሆናቸው ፍጡራን አለመሆናቸውን እስልምናም የሚስማማበት እውነታ ነው፡፡

ማጠቃለያ

“ኢየሱስ የመጀመርያው ፍጡር ነው” የሚለው የአርዮሳውያን አስተምሕሮ ከቅዱሳት መጻሕፍት ብቻ ሳይሆን ከአመክንዮም የማይስማማ ስሁት አስተምሕሮ ነው፡፡ አንድ አካል ከፍጥረት ሁሉ በፊት እንደተፈጠረ ከተናገርን ጊዜና ስፍራ (time and space) ከመፈጠራቸው በፊት ተፈጥሯል ማለት ይሆናል፡፡ ለመኖር ጊዜና ስፍራ የማያስፈልጉት አንዱ እግዚአብሔር ብቻ በመሆኑ እንዲህ ያለው እሳቤ በጊዜና በቦታ ያለመገደብን ለፍጡር በማጎናፀፍ ኢ-አመክንዮአዊና ኑፋቄያዊ ድምዳሜ ላይ ይጥለናል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት እግዚአብሔር በመጀመርያ የፈጠረው ሰማይና ምድርን እንጂ ኢየሱስን አይደለም፡- “በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍጥረት 1፡1)፡፡ ኢየሱስ ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ፈጣሪ እንጂ ፍጡር አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ “የመጀመርያ ፍጡር” እንደሆነ ሊነግረን ቢፈልግ ኖሮ “ፕሮቶክቲሲስ” የሚል የግሪክ ቃል በተጠቀመ ነበር፡፡ ነገር ግን አንድም ጊዜ ኢየሱስ በዚህ ቃል አልተጠቀሰም፡፡ ይልቁንስ ቅዱስ ቃሉ “ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” በማለት ዘግቶታል (ዮሐንስ 1፡3)፡፡ ስለዚህ ከተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ያለ እርሱ የተፈጠረ አንዳች ስንኳ ከሌለ እርሱ ፍጡር አይደለም ማለት ነው፡፡ አለበለዚያ ራሱንም ፈጥሯ ወደሚል ትርጉም አልባ ድምዳሜ እንደርሳለን፡፡ በሌላ ቦታ ደግሞ “አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ እስከ ዘላለም ድረስ ይኖራል … ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው…” ተብሎለታል (ዕብራውያን 1፡8-10)፡፡ ስለዚህ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍጥረት ሁሉ ፈጣሪ፣ የበላይና ገዢ እንጂ ፍጡር አይደለም!


ለተጨማሪ ንባብ

“የይሖዋ ምስክሮች”ና ትምህርተ ሥላሴ (ሌላ ድረገጽ)

ጌታችን ኢየሱስ “የፍጥረት በኩር” ተብሎ መጠራቱ የሚያሳየው ፈጣሪነቱን ወይንስ ፍጡርነቱን?

መሲሁ ኢየሱስ