የቁርኣን መበረዝ – በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት

የቁርአን መበረዝ

በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት

“በክፍለ ዘመናት መካከል ከ114 ሱራዎች መካከል አንድም ቃል አልተለወጠም፡፡ ስለዚህ ቁርአን ከአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለሙሐመድ የተገለጠ በሁሉም ረገድ ልዩና ተዓምራዊ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡”

እንዲህ ያሉ ቃላት ለዘመናት ከሙስሊሞች ዘንድ ሲደመጡ ኖረዋል፡፡ ሙስሊሞች ቁርአን እንከን በሌለው መንገድ ተጠብቆ ለዘመናችን እንደበቃ በፍፁም መተማመን ይናገራሉ፡፡ ቁርአን ከሰማይ የወረደ ዘላለማዊ የአላህ ቃል መሆኑን ከማመናቸው አንፃር በቁርአን ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች መካከል የአንድ ፊደል ልዩነት እንኳ ሊኖር መቻሉን አለማመናቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ታድያ ይህ እምነት ማስረጃ ይኖረው ይሆን?

ዶ/ር ዳንኤል ብሩቤከር የተሰኙ የቁርአን ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ሊቅ በቅርቡ ባሳተሙት “Corrections in Early Qurʾān Manuscripts: Twenty Examples” በተሰኘው መጽሐፋቸው ውስጥ እውነቱ ሙስሊሞች ከሚናገሩት በተጻራሪ እንደሆነ በማስረጃ አረጋግጠዋል፡፡ ይህ መጽሐፍ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሜይ 21/ 2019 የተለቀቀ ሲሆን እስከ ዛሬ ድረስ ሙስሊም ሊቃውንት ከሕዝባቸው የሰወሯቸውን አስደንጋጭ ግኝቶች በውስጡ ይዟል፡፡

እኚህ የቁርአን ሊቅ ምርምሩን ያደረጉት ከ7ው እስከ 10ው ክፍለ ዘመን በተገለበጡት የቁርአን ጽሑፎች ላይ ነው፡፡ ግኝታቸውን በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፈዋል፡-

“በጥናት ወረቀቴ ውስጥ 800 የሚሆኑ ተጨባጭ እርማቶችን የመዘገብኩ ብሆንም በአሁኑ ወቅት ግን በሺህዎች የሚቆጠሩትን አግኝቻለሁ፤ ይህ ጉዳይ ማለቂያ ያለውም አይመስልም፡፡”

በማስከተል በፒ ዲ ኤፍ ባዘጋጀነው ጽሑፍ ውስጥ የሚገኘው ከብዙ በጥቂቱ የቀረበ ነው፡፡ ጽሑፉን በማውረድ ለማንበብ ከታች በሰማያዊ ቀለም የተጻፈውን ርዕስ ጠቅ ያድርጉ፡-

የቁርአን መበረዝ በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ላይ የተደረገ አዲስ ጥናት