14. ሙሐመድ አስጠንቃቂነቱ ለአማንያን ብቻ? ወይንስ ለካሃዲያንም ጭምር?
ማሳሰብያ፡- በሰማያዊ የተጻፈው የኛ ሲሆን በጥቁር የተጻፈው የእርሱ ነው፡፡
ለአማንያን
36:10 የምታስጠነቅቀው ግሣጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው ፤
ለካሃዲያን
19:97 በምላሥህም ቁርኣንን ያገራነው፣ በርሱ ጥንቁቆቹን ልታበስርበት በርሱም ተከራካሪዎችን ሕዝቦች ልታስጠነቅቅበት ነው።
ለሁሉም
6፥19 ይህም ቁርኣን እናንተንና የደረሰውን ሰው ሁሉ በእርሱ ላስጠነቅቅበት ወደኔ ተወረደ፡፡ ከአላህ ጋር ሌሎች አማልክት መኖራቸውን እናንተ ትመሰክራላችሁን» በላቸው፡፡
ኦሪጅናል ጥያቄያችን እንዲህ የሚል ነው፡-
ሙሐመድ የሚያስጠነቅቀው ያመኑ ሰዎችን ብቻ ወይንስ ያላመኑ ሰዎችንም ጭምር?
ያመኑትን ብቻ:- 35:18 “[…]የምታስጠነቅቀው፣ እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሦላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፤ የተጥራራም ሰው፣ የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው፤ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው።”
36:11 “የምታስጠነቅቀው ግሣጼን የተከተለንና አልረሕማንን በሩቅየፈራን ሰው ብቻ ነው ፤ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው።”
ያላመኑ ሰዎችንም ጭምር:- 41:13 “(ከእምነት) እንቢ ቢሉም እንደ ዓድና ሠሙድ መቅሠፍት ብጤ የሆነን መቅሠፍት አስጠነቅቃችኋለሁ፣ በላቸው።”
34:46 “የምገሥጻችሁ ባንዲት ነገር ብቻ ነው፤ (እርሷም) ሁለት ሁለት፣ አንድ አንድም፣ ኾናችሁ ለአላህ እንድትነሱ፣ ከዚያም በጓደኛችሁ(በሙሐመድ) ምንም ዕብደት የሌለበት መሆኑን መርምራችሁ እንድትረዱ ነው፤ እርሱ ለናንተ ከብርቱ ቅጣት በስተፊት አስጠንቃቂ ነው እንጂ ሌላ አይደለም፣ በላቸው።”
በፊተኞቹ ጥቅሶች ውስጥ እንደተመለከተው ሙሐመድ የሚያስጠነቅቀው ያመኑትን ሰዎች ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን ከነርሱ ቀጥለው በሚገኙ ጥቅሶች መሠረት ሙሐመድ ላላመኑ ሰውችም ጭምር አስጠንቃቂ እንደሆነና ሲያስጠነቅቃቸውም እናነባለን፡፡ ታድያ የቱ ነው ትክክል?
መልስ
የቁርኣን ማስጠንቀቂ በሁለት ከፍለን ማለየት አለብን፥ አንዱ “ሙጅመል” مجمل ማለትም “ጥቅላዊ ማስጠንቀቂያ” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሙፈሰል” مُفَصَّل ማለትም “ተናጥሏዊወደ ማስጠንቀቂያ” ነው። ቁርኣን ለሁሉም መገሰጫ ይሆን ዘንድ መውረዱ ሙጅመል ነው፦
6፥19 «በምስክርነት ከነገሩ ሁሉ ይበልጥ ታላቅ ማነው» በላቸው፡፡ ሌላ መልስ የለምና «አላህ ነው»፡፡ በእኔ እና በእናንተ መካከል መስካሪ ነው፡፡ በል፦ “ይህም ቁርኣን እናንተን እና የደረሰውን ሰው ሁሉ በእርሱ ላስጠነቅቅበት እኔ ተወረደ”፡፡
22፥49 «እናንተ ሰዎች ሆይ! እኔ ለእናንተ ግልጽ አስጠንቃቂ ብቻ ነኝ» በላቸው፡፡
25፥1 ያ ፉርቃንን በባሪያው ላይ “ለዓለማት ማስጠንቀቂያ” ይኾን ዘንድ ያወረደው አምላክ ክብርና ጥራት ተገባው፡፡
68፥52 ግን “እርሱ ቁርኣን ለዓለማት መገሰጫ እንጂ ሌላ አይደለም”፡፡
“ለዓለማት ማስጠንቀቂያ” የሚለው ቃል “ለዓለማት መገሰጫ” በሚል ተለዋዋጭ ቃል”inter-change” መምጣቱ በራሱ ቁርኣን ለሰዎች ሁሉ በመልካም ለማዘዝ ከመጥፎ ለመከልከል የተወረደ መልእክት እንደሆነ አስረግጦና ረግጦ ያሳያል።
ሁለተኛ በተናጥል ለአማንያን የሚሰጠው ግሳጼ አላህን በሩቅ ለሚፈሩትየፈራን ማግኘት እንዳለ ነው፤ ይህ ሙፈሰል ነው፦
21፥49 “ለእነዚያ ጌታቸውን በሩቅ ለሚፈሩት እነርሱም ከሰዓቲቱ ተጨናቂዎች ለኾኑ መገሰጫን ሰጠን”፡፡
36፥11 “የምታስጠነቅቀው ግሳጼን የተከተለን እና አልረሕማንን በሩቅ የፈራን ሰው ብቻ ነው”፡፡ በምሕረትና በመልካም ምንዳም አብስረው፡፡
35፥18 “የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ የተጥራራም ሰው የሚጥራራው ለራሱ ብቻ ነው”፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ብቻ ነው፡፡
“ብቻ” ብሎ የገባው ገላጭ ቅጽል “ኢነማ” إِنَّمَا ሲሆን ብዙ ቦታ በአንጻራዊት ደረጃ የሚገባበት ጊዜ አለ፥ ለምሳሌ፦
41፥6 በላቸው «እኔ መሰላችሁ “ሰው ብቻ ነኝ”፡፡ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ወደ እርሱም ቀጥ በሉ ምሕረትንም ለምኑት ማለት ወደ እኔ ይወረድልኛል፡፡ ለአጋሪዎቹም ወዮላቸው፡፡
ነቢያችን “ሰው ብቻ” ናቸው ማለት መልአክ ወይም አምላክ አይደሉም ማለት እንጂ ከሰው ሁሉ የበለጠ ደረጃ ነቢይ ወይም መልእክተኛ አይደሉም ማለት እንዳልሆነ ሁሉ ቁርኣን ለአማንያን ብቻ ማስጠንቀቂያ የተባለበት አላህ ፊት ሚዛን የሚቆምላቸው አማንያን ብቻ ስለሆነ በተናጥል የቀረበ ማስጠንቀቂያ ማለት እንጂ ለሰዎች ሁሉ የመገናኛው ቀን ማስጠንቀቂያ አይደለም ማለት አይደለም፦
18፥105 “እነዚያ እነርሱ በጌታቸው ማስረጃዎች እና በመገናኘቱ የካዱት ናቸው፡፡ ሥራዎቻቸውም ተበላሹ፡፡ ለእነሱም በትንሣኤ ቀን ሚዛንን አናቆምላቸውም”፡፡
ስለዚህ ሥራቸው በሚዛን እንደሚመዘን ማስጠንቀቂያው ለአማንያን ብቻ ነው። ጥሩ ሥራዎቹ በሚዛን የከበዱለት ሰው በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል፥ በተቃራኒው ጥሩ ሥራዎቹ በሚዛን የቀለሉበት ሰው ቅጣቱ በሃዊያህ ናት፦
101፥6 ሚዛኖቹ የከበዱለት ሰውማ”፤
101፥7 “እርሱ በምትወደድ ኑሮ ውስጥ ይኾናል”፡፡
101፥8 “ሚዛኖቹም የቀለሉበት ሰውማ”፤
101፥9 “መኖሪያው ሃዊያህ ናት”
ቁርኣን ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን መልካም ሥራ በተመለከተ እርስ በርሱ የተምታታ ነገር ነው የሚናገረው፡፡ በአንዱ ቦታ ላይ አላህ የማንንም መልካም ሥራ ከንቱ እንደማያደርግ ይናገራል፡-
“በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው፣ (ከመቆሚያ ሥፍራ) ይመለሳሉ። የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል። የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል።” (ሱራ 99፡96-98)
So whoever does an atom’s weight of good will see it.
በሙሽሪክነት የተፈረጁት ክርስቲያኖችና ሌሎች ሕዝቦች ሳይቀሩ (ሱራ 9:28-33) መልካም ሥራቸው በመጨረሻው ዘመን ከንቱ እንደማይሆንና በአላህ ዘንድ እንደሚታሰብላቸው ይናገራል፡-
“እነዚያ ያመኑና እነዚያም ይሁዳውያን የኾኑ፣ ሳቢያኖችም ክርስቲያኖችም፣ (ከነርሱ) በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነና መልካምን ሥራ የሠራ ሰው፣ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም።” (ሱራ 5:69)
“እነዚያ ያመኑ እነዚያም ይሁዳውያን የኾኑ፣ ክርስቲያኖችም፣ ሳቢያኖችም (ከእነርሱ) በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካምንም ሥራ የሠራ ለነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው፡፡ በነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡” (ሱራ 2:62)
በሌሎች ቦታዎች ግን ከሙስሊሞች ውጪ የሚገኙት ሕዝቦች ሥራ እንደማይታሰብላቸውና ከንቱ እንደሚሆን ይናገራል (9:17፣ 9:69፣ 2:217፣ 18፡105)፡፡ ስለዚህ በመጨረሻው ቀን ሥራቸው የሚታሰብላቸው ወይም የሚመዘንላቸው ሙስሊሞች ብቻ ወይንስ ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም ጭምር? ለሚለው ጥያቄ ቁርኣን እርስ በርሱ የሚጣረስ ምላሽ ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ጉዳዩ እንደርሱ ከሆነ ደግሞ መልስህ ውድቅ ሊሆን ነው፡፡ አንተ የሙሐመድን አስጠንቃቂነት ለሁለት የከፈልክ ሲሆን አጠቃላይ በሆነ ሁኔታ ሰዎችን ሁሉ እንደሚያስጠነቅቅና ስለ መልካም ሥራ ግን ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎች ሥራ ስለማይታሰብላቸው ሙስሊሞችን ብቻ እንደሚያስጠነቅቅ ነግረኸናል፡፡ ነገር ግን ሙስሊም ላልሆኑት ሰዎች መልካም ሥራቸው ይታሰባል ወይንስ አይታሰብም? ለሚለው ቁርኣን እርስ በርሱ የሚጣረስ ምላሽ ስለሚሰጠን የሙሐመድን አስጠንቃቂነት በመልካም ሥራ ላይ ተመሥርተህ ሁለት መልክ መስጠትህ ስህተት ይሆናል፤ ግጭቱንም አያስታርቅም፡፡