ቁርኣንና ኖስቲሳውያን – የቁርኣን ደራሲ የኩረጃ ጉድ ሲጋለጥ

ቁርኣንና ኖስቲሳውያን

የቁርኣን ደራሲ የኩረጃ ጉድ ሲጋለጥ

ኖስቲሲዝም (Gnosticism) በሁለተኛውና በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ተከታዮችን አፍርቶ የነበረ የኑፋቄ ቡድን ሲሆን አጀማመሩንና የተጀመረበትን ዘመን በተመለከተ በሊቃውንት መካከል ስምምነት የለም፡፡ አንዳንዶቹ ከአይሁድ ኑፋቄያዊ ቡድኖች የተገኘ እንደሆነ ሲናገሩ ሌሎች ደግሞ ክርስቲያናዊ አውድ ይሰጡታል፡፡ ሙሉ በሙሉ አረማዊ ስረ መሠረት እንዳለው የሚናገሩ ሊቃውንትም አሉ፡፡[1] ኖስቲክ (Gnostic) የሚለውን ቃል ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀመው ሄንሪ ሞር የተሰኘ በ17ው ክ.ዘ. የኖረ ሰው ሲሆን “ዕውቀት” የሚል ትርጉም ካለው ኖሲስ (Gnosis) ከሚለው የግሪክ ቃል የተዋቀረ ነው፡፡[2] ኖስቲሲዝም በተሰኘው እምነት ስር የሚመደቡ ብዙ ቡድኖች የሚገኙ ሲሆን ከክርስትና የሚለዩዋቸው ዋና ዋና ትምህርቶቻቸው የሚከተሉት ናቸው፡-

  • የብሉይ ኪዳን አምላክ ከአዲስ ኪዳን አምላክ የተለየ ነው፡፡ የብሉይ ኪዳን አምላክ ክፉና ውሱን ሲሆን የአዲስ ኪዳን አምላክ ሁሉን ቻይ ነው፡፡
  • ፍጥረት የተፈጠረው በሶፍያ (ጥበብ) ውድቀት ምክንያት ነው፡፡
  • ቁስ የተባለ ሁሉ ክፉ ነው፡፡
  • ኢየሱስ በስጋ አልመጣም፣ በመስቀል ላይ አልሞተም፣ ትክክለኛው ኢየሱስ መንፈስ ነው፡፡
  • የመንፈስ ትንሣኤ እንጂ የሥጋ ትንሣኤ የለም፡፡[3]

ስለ ኖስቲሳውያን ከጥንት ቤተ ክርስቲያን አበው ጽሑፎች ብዙ መረጃዎችን የምናገኝ ሲሆን በ1945 ዓ.ም. ነጅ ሐማዲ በተባለ ቦታ የኖስቲሳውያን እምነቶች የተንጸባረቁባቸው ብዙ መጻሕፍት በመገኘታቸው ምክንያት ስለ እነርሱ ያለን መረጃ ከፍ ብሏል፡፡ ከነዚህ መጻሕፍት መካከል “የቶማስ ወንጌል” የተሰኘው መጽሐፍ ይገኝበታል፡፡[4] በቁርኣን ውስጥ የሚገኘው ኢየሱስ በህፃንነቱ ከጭቃ ወፍ ሠርቶ ስለማብረሩ የሚናገረው ታሪክ ከዚህ ወንጌል ላይ የተቀዳ መሆኑ በሊቃውንት ተረጋግጧል፡፡[5]

ቁርኣን ከቶማስ ወንጌል ብቻ ሳይሆን የኖስቲሲዝም ንክኪ ካላቸው ከሐዋርያት ዘመን በኋላ ከተጻፉ ሌሎች መስመ ወንጌላት (Pseudo Gospels) ላይ የተቀዱ በርካታ ታሪኮችን በውስጡ አጭቋል፡፡ ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል፡-

  • ሱራ 3፡44 ላይ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡- “ይኸ ወደ አንተ የምናወርደው የኾነ ከሩቅ ወሬዎች ነው፡፡ መርየምንም ማን እንደሚያሳድግ ብርኦቻቸውን (ለዕጣ) በጣሉ ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡ በሚከራከሩም ጊዜ እነሱ ዘንድ አልነበርክም፡፡”

ማርያምን ለማሳደግ እጣ ስለመጣሉ የያዕቆብ ወንጌል ወይም የማርያም ልደት የተሰኘው መጽሐፍ አስቀድሞ ተርኳል፡፡ እንዲህ ይላል፡-

And Joseph, throwing away his axe, went out to meet them; and when they had assembled, they went away to the high priest, taking with them their rods. And he, taking the rods of all of them, entered into the temple, and prayed; and having ended his prayer, he took the rods and came out, and gave them to them: but there was no sign in them, and Joseph took his rod last; and, behold, a dove came out of the rod, and flew upon Joseph’s head. And the priest said to Joseph, Thou hast been chosen by lot to take into thy keeping the virgin of the Lord. But Joseph refused, saying: I have children, and I am an old man, and she is a young girl. I am afraid lest I become a laughing-stock to the sons of Israel. And the priest said to Joseph: Fear the Lord thy God, and remember what the Lord did to Dathan, and Abiram, and Korah; how the earth opened, and they were swallowed up on account of their contradiction. And now fear, O Joseph, lest the same things happen in thy house. And Joseph was afraid, and took her into his keeping.

ዮሴፍም መጥረቢያውን ጥሎ ሊቀበላቸው ወጣ። ተሰብስበውም በትራቸውን ይዘው ወደ ሊቀ ካህናቱ ሄዱ። የሁሉንም በትር ይዞ ወደ መቅደስ ገባና ጸለየ። ጸሎቱንም ከፈጸመ በኋላ በትሮቹን [ዕጣ ለማውጣት የሚያገለግሉ] ይዞ ወጥቶ ሰጣቸው፤ ነገር ግን ምልክት አልነበረባቸውም ዮሴፍም በመጨረሻ በትሩን ወሰደ። እነሆም፥ ርግብ ከበትሩ ወጥታ በዮሴፍ ራስ ላይ በረረች። ካህኑም ዮሴፍን፦ የጌታን ድንግል ትጠብቅህ ዘንድ በዕጣ ተመርጠሃል አለው። ዮሴፍ ግን፣ ልጆች አሉኝ፣ እናም እኔ ሽማግሌ ነኝ፣ እርስዋም ትንሽ ልጅ ነች ብሎ እምቢ አለ። ለእስራኤል ልጆች መሳቂያ እንዳልሆን እፈራለሁ። ካህኑም ዮሴፍን፦ አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፥ እግዚአብሔርም በዳታን፥ በአቤሮንም፥ በቆሬም ላይ ያደረገውን አስብ። ምድር እንዴት እንደ ተከፈተች እነርሱም በመቃወማቸው ምክንያት ተዋጡ። አሁንም ዮሴፍ ሆይ ይህ ነገር በቤትህ እንዳይሆን ፍራ። ዮሴፍም ፈራ፥ ጠባቂዋም ሊሆን ወሰዳት።[6]

ቁርኣን በዚህ የተረት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘውን ታሪክ በመውሰድ መለኮታዊ መገለጥ አስመስሎ አቅርቧል፡፡ በተጨማሪም ሱራ 3፡37 ላይ የጌታ እናት ማርያም በቤተ መቅደስ ስለማደጓና መላእክት ይመግቧት እንደነበር የሚናገረው ታሪክ ከዚሁ የያዕቆብ ወንጌል ወይም የማርያም ልደት በመባል ከሚታወቀው የአፖክሪፋ መጽሐፍ የተወሰደ ነው፡፡[7]

ሱራ 19፡23-26 እንዲህ ይላል፡-

“ምጡም ወደ ዘንባባይቱ ግንድ አስጠጋት፡፡ «ዋ ምኞቴ! ምነው ከዚህ በፊት በሞትኩ፡፡ ተረስቼም የቀረሁ በሆንኩ» አለች፡፡ ከበታቿም እንዲህ ሲል ጠራት «አትዘኝ፡፡ ጌታሽ ከበታችሽ ትንሽን ወንዝ በእርግጥ አድርጓል፡፡ «የዘምባባይቱንም ግንድ ወዳንቺ ወዝውዣት ባንቺ ላይ የበሰለን የተምር እሸት ታረግፍልሻለችና፡፡ «ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን ዝምታን ተስያለሁ፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡”

መስመ-ማቴዎስ (Pseudo-Matthew) በተሰኘ የአፖክሪፋ መጽሐፍ ውስጥ ይህ ታሪክ እንዲህ ቀርቧል፡-

“በእናቱ ጭን ላይ በደስታ ተቀምጦ የነበረው ህፃኑ ኢየሱስ ዘንባባዋን እንዲህ አላት፡ “አንቺ ዛፍ ሆይ ቅርንጫፎችሽን ዝቅ አድርጊና እናቴን በፍሬዎችሽ አጥግቢ፡፡” ወድያውኑ በድምፁ ትዕዛዝ ዘንባባዋ ብፅዕት ወደሆነችው ወደ ማርያም እግሮች ዝቅ አለች፡፡ ሁላቸውም ፍሬዎቿን በመልቀም ጠገቡ፡፡ “ከስሮችሽ ውሃን አፍልቂ … ውሃውም ይፍሰስ” [ብሎ አዘዛት] … የውሃውንም ምንጭ ባዩ ጊዜ በጣም ደስ አላቸው፣ ጥማቸውንም አረኩ፡፡”[8]

ሁለቱ ታሪኮች መጠነኛ ልዩነት ቢኖራቸውም እጅግ የተቀራረቡ ናቸው፡፡ የቁርኣን ጸሐፊ በታሪኩ ላይ ለውጥ ማድረጉ በትክክል አለማስታወሱን ወይንም ደግሞ ከተዛባ ምንጭ መቅዳቱን ያመለክታል፡፡

ሱራ 19፡29-30 ላይ ቁርኣን እንዲህ ይላል፡-

“ወደርሱም ጠቀሰች፡፡ «በአንቀልባ ያለን ሕጻን እንዴት እናናግራለን!» አሉ፡፡ (ሕፃኑም) አለ «እኔ የአላህ ባሪያ ነኝ፡፡ መጽሐፍን ሰጥቶኛል ነቢይም አድርጎኛል፡፡» «በየትም ስፍራ ብሆን ብሩክ አድርጎኛል፡፡ በሕይወትም እስካለሁ ሶላትን በመስገድ ዘካንም በመስጠት አዞኛል፡፡»”

ይህ ታሪክ የህፃንነቱ ታሪክ በተሰኘ የአረብኛ መጽሐፍ ውስጥ ሰፍሯል። የግሪኩ ኦሪጅናል በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ሲሆን The First Gospel of the Infancy of Jesus Christ በሚል ርዕስ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሟል። እንዲህ ይላል፦

“በክርስቶስ ዘመን በነበረው በሊቀ ካህኑ በዮሴፍ መጽሐፍ ውስጥ (አንዳንዶች ቀያፋ ነው ይሉታል) ኢየሱስ በአንቀልባ ውስጥ ሆኖ እንደተናገረና ለእናቱ ለማርያም እንዲህ እንዳላት ተጽፏል፡- “እኔ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ፣ መልአኩ ገብርኤል በነገረሽ መልካም ዜና መሠረት የወለድሽኝ ቃል ነኝ፤ አባቴም ዓለም ይድን ዘንድ ልኮኛል፡፡”[9]

የቁርኣን ጸሐፊ ይህን በምድረ አረብ የታወቀ ታሪክ አስልሞ አቅርቦታል፡፡ ድንቄም ከሰማይ የመጣ መገለጥ!

ለበለጠ መረጃ እዚህ ጋ ይጫኑ፡፡

——————————–

[1] Geisler. Encyclopedia; p. 504

[2] Britannica, Encyclopedia of World Religions; p. 380

[3] Geisler. Encyclopedia; p. 504

[4] Britannica, Encyclopedia of World Religions; p. 380

[5] The New Testament Apocrypha, vol. 1, rev. ed. by W. Schneemelcher, trans. R. McL. Wilson, Westminster / John Knox, 1991, p. 444 https://www.earlychristianwritings.com/text/infancyjames-roberts.html

[6] Ibid., pp. 429-430

[7] Ibid., 429

[8] Ibid., p. 463

[9] Rev. W. ST Clair Tisdall. The Sources of Islam; p. 58. መጽሐፉ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ስለመሆኑ የእንግሊዝኛ ተርጓሚው እንዲህ በማለት አስቀምጧል፦ “የኢየሱስ ክርስቶስ የሕፃንነት ወንጌል፣ በተለምዶ የቶማስ የሕፃንነት ወንጌል እየተባለ የሚጠራው (በቀላሉ የቶማስ ወንጌል ተብሎ ከሚጠራው የአዋልድ መጻሕፍት መጽሐፍ ጋር መምታታት የለበትም) በ185 ዓ.ም የተጻፈ ሲሆን…” “The First Gospel of the Infancy of Jesus Christ, also commonly referred to as The Infancy Gospel of Thomas (not to be confused with the apocryphal book simply called the Gospel of Thomas), dates to AD 185…” ወደ ምንጩ ለመሄድ እዚህች ጋር ጠቅ ያድርጉ።

 

 

ቅዱስ ቁርኣን