አንድ ታሪክ- የሚጋጩ ምንባቦች በቁርኣን

አንድ ታሪክየሚጋጩ ምንባቦች በቁርአን

ሙስሊም ወገኖች የክርስቶስን ትንሣኤ አስመልክቶ የተጻፉትን የአራቱን ወንጌላት የተለያዩ የአዘጋገብ ሁኔታዎች በመጥቀስ እርስ በርሳቸው እንደሚጋጩ ይናገራሉ፡፡ አራቱ ወንጌላት የተጻፉት በተለያዩ ሰዎች አማካይነት ስለሆኑ ጸሐፊያኑ ክስተቱን ከተለያዩ ማዕዘናት በመመልከት ዘግበውታል፡፡ ለምሳሌ ያህል ሐዋርያው ዮሐንስ መግደላዊት ማርያም ላይ በማተኮር በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ጽፏል፡፡ ሌሎች የወንጌል ጸሐፊያን እንዲሁ ታሪኩን ከተለያዩ አቅጣጫዎች በማየት እንዲጽፉ መንፈስ ቅዱስ መርቷቸዋል፡፡ የወንጌላቱም ዘገባዎች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ሳይሆኑ እርስ በርስ በመሰባጠር በወቅቱ ስለነበረው ሁኔታ የተሟላ ምስልን የሚሰጡ ናቸው፡፡ በአንጻሩ ግን በአንድ ሰው በኩል እንደተተረከ የሚነገርለት ቁርኣን አንድን ክስተት ፈጽሞ ሊታረቁ በማይችሉ የተለያዩ መንገዶች ያቀርባል፡፡ በውስጡ የሚገኙ ገጸ-ባህርያትም የሆነ ቦታ ላይ እንደተናገሩት የተጻፈ ተመሳሳይ ንግግር እዚያው መጽሐፍ ውስጥ ሌላ ቦታ ላይ የተወሰነ ሐሳብ ተጨምሮበት ወይንም ደግሞ ከላዩ ላይ ተቀንሶ እንዲሁም አንዱ ቃል በሌላው ተተክቶ ይነበባል፡፡ የሚከተሉትን የቁርኣን ጥቅሶች ጐን ለጐን ካነበብን በኋላ የቁርኣን ደራሲ አንዱ ቦታ ላይ የተናገረውን ሌላ ቦታ ላይ በትክክል በመድገም መናገርየ ማይችል ሰው እንደነበር ለመደምደም እንገደዳለን።

  1. እስራኤላውያን የተቀበሉት ትዕዛዝ

2፡58-59 “ይህችንም ከተማ ግቡ ከእርሷም ካሻችሁት ስፍራ ሰፊን (ምግብ) ተመገቡ በሩንም ያጐነበሳችሁ ሆናችሁ ግቡ (ጥያቄያችን የኃጢዓታችን) መርገፍ ነው በሉም፤ ኃጢአቶቻችሁን ለናንተ እንምራለንና በጐ ሰሪዎችንም (ምንዳ) እንጨምርላቸዋልን ባልን ጊዜ (አስታውሱ)፡፡ እነዚያ የበደሉት ሰዎች ከዚያ ለነሱ ከተባሉት ሌላ ቃልን ለወጡ፤ በነዚያም በበደሉት ላይ ያመፁ በመሆናቸው ምክንያት መቅሰፍትን አወረድንባቸው፡፡”7፡161-162 “ለነሱም በተባሉ ጊዜ (አስታውስ) በዚች ከተማ ተቀመጡ ከርሷም ባሻችሁ ስፍራ ብሉ (የምንፈልገው) የኃጢዓታችንን መርገፍ ነው በሉም፤ የከተማይቱንም በር አጐንብሳችሁ ግቡ ኃጢአታችሁን ለእናንተ እንምራለንና፡፡ ከነርሱ ውስጥ እነዚያ (ራሳቸውን) የበደሉት ሰዎች ከዚያ ከነርሱ ከተባለው ሌላ የሆነን ቃል ለወጡ፤ በነርሱም ላይ ይበድሉ በነበሩት በደል መአትን ከሰማይ ላክንባቸው፡፡”

____________________

  1. ሙሴና የሚነድደው ቁጥቋጦ

20፡9-24 “የሙሳም ወሬ በእርግጥ መጥቶልሃል፤ እሳትን ባየና ለቤተሰቦቹ (እዚህ) ቆዩ እኔ እሳትን አየሁ ከርሷ ችቦን ላመጣላችሁ ወይም እሳቲቱ ዘንድ መሪ ላገኝ እከጅላለሁ ባለ ጊዜ አስታውስ።”27፡7 “ሙሳ ለቤተሰቦቹ፡- እኔ እሳትን አየሁ ከርሷ ወሬን አመጣላችኋለሁ ወይም ትሞቁ ዘንድ የተለኰሰ ችቦን አመጣላችኋለሁ ባለ ጊዜ (የሆነውን አስታውሳቸው)።”28፡29 “ሙሳም ጊዜውን በጨረሰና ከቤተሰቦቹ ጋር በሄደ ጊዜ ከጡር ተራራ ጐን እሳትን አየ ለቤተሰቡ (እዚህ) ቆዩ እኔ እሳትን አየሁ፤ ከርሷ ወሬን ወይም ትሞቁ ዘንድ ከእሳት ትንታግን አመጣላችኋለሁ አለ።”

____________________

  1. የሙሴ እጅ

20፡22 “እጅህንም ወደ ብብትህ አግባ ሌላ ታምር ስትሆን ያለነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና፡፡ ከታምራቶቻችን ታላቋን እናሣይህ ዘንድ (ይህንን ሠራን )፡፡”28፡32 “እጅህን በአንገትጌህ ውስጥ አግባ ያለነውር ነጭ ሆና ትወጣለችና…”

____________________

  1. የፈርኦን ንግግር

7፡123 “ፈርኦን አለ፡- እኔ ለናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት በርሱ አመናችሁን? ይህ በከተማይቱ ውስጥ ሰዎቿን ከርሷ ለማውጣት በእርግጥ የተስማማችሁበት ተንኰል ነው፡፡ ወደፊትም (የሚደርስባችሁን) ታውቃላችሁ፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁንም በማፈራረቅ በእርግጥ እቆራርጣለሁ፤ ከዚያም ሁላችሁንም በእርግጥ እሰቅላችኋለሁ፡፡”20፡71 “(ፈርኦንም) ለናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለርሱ አመናችሁን? እርሱ በርግጥ ያድግምትን ያስተማራችሁ ትልቃችሁ ነው፡፡ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን በማናጋት (ግራና ቀኝ በማፈራረቅ) እቆራርጣችኋለሁ፤ በዘንባባም ግንዶች ላይ እስቅላችኋለሁ፤ ማንኛችሁንም ቅጣቱ በጣም ብርቱ የሚቆይም መሆኑን ታውቃላችሁ አላቸው፡፡”26፡49 “(ፈርኦንም) ለእናንተ ሳልፈቅድላችሁ በፊት ለርሱ አመናችሁን? እርሱ ያ ድግምትን ያስተማራችሁ ታላቃችሁ ነው፤ ወደፊትም (የሚያገኛችሁን) በእርግጥ ታውቃላችሁ፤ እጆቻችሁንና እግሮቻችሁን (ቀኝና ግራን) በማናጋት እቆራርጣለሁ፤ ሁላችሁንም እሰቅላችኋለሁም አለ፡፡”

____________________

  1. የአዳምና የአላህ ንግግር

2፡35 “አደም ሆይ! አንተ ከነሚስትህ በገነት ተቀመጥ፤ ከርሷም በፈለጋችሁት ሥፍራ በሰፊው ተመገቡ፤ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ፤ ከበደለኞች ትሆናላችሁና አልን፡፡”7፡19 “አደምም ሆይ! አንተም ሚስትህም በገነት ተቀመጡ ካሻችሁም ሥፍራ ብሉ ግን ይህችን ዛፍ አትቅረቡ ራሳቸውን ከሚበድሉት ትሆናላችሁና አላቸው፡፡”

በተጨማሪም ቁርአን 20፡38-40፤ 28፡7-13፤ ቁርአን 7፡12-18፤ 15፡32-42፤ 17፡61-65፤ 38፡75-85 ያነጻጽሩ፡፡

ሙስሊሞች መጽሐፍ ቅዱስን ለመመዘን የሚጠቀሙትን ተመሳሳይ መስፈርት ቁርአንን ለመመዘን የሚጠቀሙ ከሆነ ከላይ የተቀመጡትን አልተገናኝቶ ምንባቦች እንዴት ያስታርቋቸው ይሆን?

ቅዱስ ቁርአን