እግዚአብሔር ምላጭ ተከራየ?

እግዚአብሔር ምላጭ ተከራየ?

ኢሳይያስ 7:20 “በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ፤ የራሱንና የእግሩን ጠጉር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል” ይላል፡፡ አምላክ ምላጭ ይከራያልን? ሁሉን የፈጠረና ዓለሙ ሁሉ የርሱስ አይደለምን? ጸጉር ይላጫልን? ተራ የሰው ማህበራ ድርጊቶቹን ሁሉ የፈጣሪ እለታዊ ድርጊት እንደሆኑ አድርጎ መግለፅ ለፈጣሪ ያለንን እሳቤ በብዥታ የተሞላ አያደርግምን?

“ምላጭ” የተባለው የአሦር ንጉሥ መሆኑ በግልፅ እየታየ ይህ ጥያቄ መነሳቱ በራሱ በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡ ይህ ቃል እግዚአብሔር እርሱን በማያቀውቀው፣ ጣዖት አምላኪ በሆነው የአሦር ንጉሥ ተጠቅሞ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ጠላት የሆነውን ኤፍሬምን እንደሚያዋርድ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው፡፡ (መላጨት የኀዘንና የውርደት ምልክት ነው 2ሳሙኤል 10፡4፣ ኤርምያስ 41፡5፡፡) ይህ ነጥብ የሙግት ሐሳብ ሆኖ መቅረቡ በራሱ እጅግ አስቂኝ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሙስሊም ወገኖች ይህንን ነጥብ “ከጠንካራ” ሙግቶቻቸው መካከል እንደ አንዱ በመቁጠር በተደጋጋሚ ማንሳታቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞች አንዱ የጻፈውን በመያዝ በደመነፍስና በድርቅና ከመከራከር በዘለለ ክፍሉን አውጥቶ የማንበብ ልማድ የላቸውም፡፡

 

ለእስልምና ሙግቶች ምላሽ