የኢየሱስ ልጅነት ጅማሬ ያለውና የአማኞች ዓይነት ነውን?

የኢየሱስ ልጅነት ጅማሬ ያለውና የአማኞች ዓይነት ነውን?

ተከታዩ ልውውጥ አንድ ሙስሊም በፌስ ቡክ ገጻችን ላይ ከለጠፈው የተወሰደ ነው፡፡ ጸሐፊው ኢየሱስ ዘላለማዊና አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለመካድ የሚሞክር ሲሆን  የምሑር ጽሑፍ ለማስመሰል ግሪክ ጣል ጣል ተደርጎበታል፡፡ ከአጻጻፉ እንደሚታየው ደራሲው የኾነ ዓይነት የኑፋቄ ትምሕርት አቀንቃኝ እንጂ ሙስሊም አይመስልም፡፡ ነገር ግን ሙስሊሞች ከእምነታቸው ጋር ባይስማማም እንዲህ ያሉ ጽሑፎችን የመቀባበል ልማድ ስላላቸው እዚህ ገጽ ላይ ቢቀመጥ ጠቃሚ ይመስለናል፡፡ በኢታሊክስ ከተጻፉት የደራሲው ሙግቶች በማስከተል የኛ ምላሾች ተቀምጠዋል፡፡

ሙግት

አንድያ ልጅየሚለው የግሪኩ ቃልሞኖጌነስ” μονογενὴς ሲሆን የሁለት ቃላት ውቅር ነው፤ሞኖስ” μόνος ማለትብቸኛማለት ሲሆንጌኑስ” γένος ማለት ደግሞየተወለደማለት ነው፤ በጥቅሉብቸኛ የተወለደ”the only begotten” ማለት ነው፦
1
ዮሐንስ 49 እግዚአብሔርአንድ ልጁን” μονογενῆ ወደ ዓለም ልኮታልና።

በግዕዝወልድ ዋሕድይሉታል። ይህንን ውልደት እግዚአብሔር በመዝሙር ኢየሱስን እኔ ዛሬ ወለድሁህ ብሎታል፦
መዝሙር 27 ትእዛዙን እናገራለሁ፤ እግዚአብሔር አለኝ፦ አንተ ልጄ ነህ፥ እኔዛሬወለድሁህ” γεγέννηκά

ዛሬየሚለው የጊዜ ተውሳከ ጊዜን የሚያሳይ ነው፣ ኢየሱስ መወለዱ ጅማሬ ያለው መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳያል፣ ይህ ጊዜ ከሞት ሲነሳ እንደሆነ ጳውሎስ ይናገራል፦
የሐዋርያት ሥራ 1333 ይህን ተስፋ እግዚአብሔር በሁለተኛው መዝሙር ደግሞ፦ አንተ ልጄ ነህእኔ ዛሬ ወለድሁህ” γεγέννηκά ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ ኢየሱስን አስነሥቶ ለእኛ ለልጆቻቸው ፈጽሞአልና።

እኔ ዛሬ ወለድሁህተብሎ በሁለተኛው መዝሙር የተጻፈው ቃል ኢየሱስ ሲነሳ ተፈጽሞአል እያለን ነው፤ ስለዚህዛሬ ወለድሁህየተባለን ቅድመዓለም ከአብ ያለ እናት የሚለው ዶግማ ውኃ የሚያስበላና ድባቅ የሚያስገባ ነው።

ምላሽ

ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ነገሮችን ነው እየተናገርክ ያለኸው፡፡ 1ዮሐ. 4፡9 ላይ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ወደ ዓለም እንደላከ የተናገረውን ከጠቀስክ በኋላ ሐዋ. 13፡33 ላይ ጳውሎስ የተናገረውን “ልጅ የሆነው በትንሣኤው ወቅት ነው” ብለህ ከተረጎምክ ግጭት ነው፡፡ ሲላክ ልጅ ከነበረ ኋላ ላይ በትንሣኤው ዕለት ልጅ ሆነ ልትል አትችልም፡፡ ይልቅ ትንሣኤው የልጅነት ጅማሬ ሳይሆን ልጅነቱ ለፍጥረት በኃይል የተገለጠበት መሆኑን ሐዋርያው ጳውሎስ እንዲህ ይነግርሃል፡-

“ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ኾኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” (ሮሜ 1፡4-5)፡፡

በዚህ ክፍል ግልፅ ኾኖ እንደሚታየው እግዚአብሔር ለዓለም ኹሉ ተዓምራዊ በሆነ ኹኔታ የኢየሱስን ልጅነት ያረጋገጠው በትንሣኤው ወቅት መኾኑን እንገነዘባለን፡፡ 

“ዛሬ ወልጄሃለሁ” የሚለው አነጋገር ጊዜን አመላካች አይደለምን? በዚህ ላይ የተለያዩ አመለካከቶች አሉ፡፡ ኦሪጎንና አትናቴዎስን የመሳሰሉት አበው እግዚአብሔር ዘለዓለማዊ በመኾኑ “ዛሬ” የተባለው እግዚአብሔር የሚኖርበትን ዘለዓለም አመላካች እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር “ዛሬ” በሰውኛ አነጋገር ሳይኾን በእግዚአብሔር ዘለዓለማዊነት መታየት ስላለበት ይህ አባባል የኢየሱስን ዘለዓለማዊ የእግዚአብሔር ልጅነት እንደሚያመለክት አትተዋል፡፡ የቅርብ ዘመን የመጽሐፍ ቅዱስ ሐታቾች (Commentators) ደግሞ ይህ ንግግር ኢየሱስ በትንሣኤው ወቅት የእግዚአብሔር ልጅ ስለመኾኑ ለፍጥረት መረጋገጡን የተመለከተ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በዚህ መረዳት መሠረት “ዛሬ ወልጄሃለሁ” ማለት ከዚህ ቀደም ልጅ አለ መኾንን የሚያመለክት ሳይኾን ኢየሱስ ከሠራው ታላቅ ሥራ የተነሳ አብ ደስ መሰኘቱን የገለፀበት መንገድና “የባርያን መልክ” ይዞ በመምጣቱ ምክንያት የተሸፈነውን መለኮታዊ ልጅነቱን ዳግመኛ በማቀዳጀት ለፍጥረት ኹሉ ማረጋገጫ የሰጠበት ነው፡፡ [1]

ሙግት

ኢየሱስ ከሙታን በኵር ተብሏል፤በኵርተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃልፕሮቶቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን የሁለት ቃላት ጥምረት ነው፤ አንዱፕሮቶስ” πρῶτος ማለትፊተኛሲሆን ሁለተኛውቶኮስ” τοκος ማለትምመወለድነው፤ በጥቅሉመጀመሪያ የተወለደማለት ነው። ኢየሱስ በብዙ ወንድሞች መካከል ፊተኛ በመሆን ከሙታን በአብ እንደተወለደ ይናገራል፦
ሮሜ 829 “ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከልበኵር” πρωτότοκον ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤

የበኵር ልጅሁለተኛ ልጅ እስኪመጣ ድረስ ለወላጅአንድያ ልጅነው፦
ዘካርያስ 1210 ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።

አንድያ ልጁእናየበኵር ልጁተለዋዋጭ ሆነው እንደገቡ ልብ በል፤ ታዲያ ቀጣይ ልክ እንደ ኢየሱስ ከአብ የሚወለዱ እነማን ናቸው?

መልስ

የመጀመርያው ዓረፍተ ነገር የሥነ-ልሳን ተፋልሶ ነው፡፡ አንድ ቃል በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ያለው ትርጉም የሚወሰነው በአውድ እንጂ በመነሻው ወይም መገኛው አይደለም፡፡ “በኩር” ማለት በኛ ቋንቋም ቢሆን “መጀመርያ የተወለደ” ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ለምሳሌ ያህል “በኩረ-ጽሑፍ” ካልን “መጀመርያ የተወለደ ጽሑፍ” ማለታችን ሳይሆን መጀመርያ የተጻፈ ጽሑፍ ማለታችን ነው፡፡ ልክ እንደዚሁ በኩር የሚለው ቃል በግሪኩም ቢሆን መወለድን የሚያሳይ ቢሆንም “ከሙታን በኩር” የሚለውን ከውልደት ጋር ማያያዝ ትርጉም አይሰጥም፡፡ ከሙታን በኩር ማለት ከሙታን አስቀድሞ የተነሳ ማለት ነው፡፡

ሮሜ 8፡29 ላይ ብኩርና ልደትን በሚያሳይ መንገድ ጥቅም ላይ ቢውልም የኢየሱስ ልጅነትና የአማኞች ልጅነት እንደሚመሳሰል እንጂ አንድ ዓይነት እንደሆነ አያረጋግጥም፡፡ ይህንንም መጨረሻ ላይ ከምጠቅሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መረዳት ይቻላል፡፡

ዘካ. 12፡10 እዚህ ጋ መምጣት ያለበት ጥቅስ አይደለም፡፡ አንድያ ልጅና የበኩር ልጅ በዚህ ቦታ እየተለዋወጡ ስለ መግባታቸው እርግጠኛ መሆን አይቻልም፡፡ የጥቅሱ ሐሳብ እስራኤላውያን የመሲሁን ማንነት ሲገነዘቡ የሚሰማቸውን መሪር ኀዘን መግለፅ በመሆኑ ኀዘናቸው አንድ ልጁን ያጣ ሰው ወይንም የበኩር ልጁን ያጣ ሰው ከሚሰማው ኀዘን ጋር ተመሳስሏል፡፡ ይህ ሁለቱ አንድ ናቸው እንድንል አያደርገንም፡፡ ይልቅ አንድያ ልጅና የበኩር ልጅ አንድ እንዳልሆኑ መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ ይናገራል፡፡ ለምሳሌ ያህል እስማኤል ለአብርሃም የበኩር ልጅ ሆኖ ሳለ ይስሐቅ አንድያ ልጅ (ሞኖጌኔስ) ተብሏል (ዘፍ. 22፡2)፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ይስሐቅ እንደተስፋው ቃል የተወለደና እስማኤል ደግሞ እንደ ሥጋ ፈቃድ የተወለደ በመሆናቸው ነው፡፡ ስለዚህ የበኩር ልጅና አንድያ ልጅ ይለያያሉ፡፡

ሙግት

ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፦
1
ዮሐንስ 5:1 ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል γεγέννηται ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን γεγεννημένον ደግሞ ይወዳል።
የሐዋርያት ሥራ 17:28-29 ከእናንተ ከባለ ቅኔዎች አንዳንዶች ደግሞ። እኛ ደግሞ ውልደቶቹ γένος ነንና ብለው እንደ ተናገሩ፥ በእርሱ ሕያዋን ነንና እንቀሳቀሳለን እንኖርማለን። እንግዲህ የእግዚአብሔር ውልደቶች γένος ከሆንን፥
ዮሐንስ 113 እነርሱም ከእግዚአብሔርተወለዱ” ἐγεννήθησαν እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድአልተወለዱም

ጌኑስ” γένος የሚለው ቃል ልክ ለኢየሱስ እንደተጠቀመበት እዚህ ላይም ተጠቅሟል፤ እንደ ጳውሎስ ትምህርት ኢየሱስ ከሞት ሲነሳ እንደተወለደ ሁሉ አማኞች በትንሳኤ ቀን ሲነሱ ሲጠባበቁት የነበረውን ልጅነት ዳግም ያገኛሉ። የሚቀድሰው ኢየሱስ እና የሚቀደሱት ወንድሞቹ ሁሉ ከአንድ እግዚአብሔር የተገኙ ናቸውና፦
ሮሜ 823 ”የሰውነታችን ቤዛ የሆነውን ልጅነት እየተጠባበቅንራሳችን በውስጣችን እንቃትታለን።
ማቴዎስ 1928 ”በዳግመኛ ልደትየሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥
ዕብራውያን 211 ”የሚቀድሰውና የሚቀደሱት ሁሉ ከአንድ ናቸውና

ዳግም ልደት ማለት አዲስ ልደት ማለት ነው፤ ኢየሱስ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድያ ልጅ የሚለው እሳቤ ፉርሽ ሆነ ማለት ነው።

መልስ

አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው፡፡ ነገር ግን ይህ ልጅነት የኢየሱስ ዓይነት ልጅነት እንዳልሆነ አንተ የጠቀስከው ሮሜ 8፡23 ይናገራል፡፡ በዚያ ቦታ ላይ ልጅነትን ለማመልከት የገባው የግሪክ ቃል υἱοθεσία “ሁዮቴስያ” የሚል ሲሆን ማደጎን (Adoption) የሚያመለክት ነው፡፡ የእስትሮንግ ግሪክ ዲክሺነሪ ይህንን እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፡-

The placing as a son, i.e. adoption (figuratively, Christian sonship in respect to God). adoption (of children, of sons). https://biblehub.com/greek/5206.htm

የኢየሱስ ልጅነት ከእግዚአብሔር መለኮታዊ ማንነት ጋር ቀጥተኛ ተያያዥነት ያለው ሲሆን የኛ ግን Adoption ነው፡፡ የአማኞች ልጅነት በአንድያ ልጁ በማመናችን ምክንያት ያገኘነው የጸጋ ልጅነት፤ ስለዚህ የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጆች ባለመሆናችን “የማደጎ ልጅነት” (Adoption) በግሪኩ “ሁዮቴስያ” ተብሏል (ሮሜ 8:15፣ 8፡23፣ 8:23፣ 9:4፣ ገላ 4:5፣ ኤፌ. 1:5 የአማኞችን ልጅነት ለማመልከት ተመሳሳይ የግሪክ ቃል ተጠቅሷል)፡፡ ይህ ከጥንት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን ስታስተምረው የኖረችው እንጂ አዲስ ትምሕርት አይደለም፡፡

እግዚአብሔር አብም ሆነ ራሱ ኢየሱስ ልጅነቱ የተለየና በመካከላቸው ቀጥተኛ ቁርኝት መኖሩን የሚገልፅ መሆኑን ግልፅ አድርገዋል፡፡ አብ በኢየሱስ የአገልግሎት ዘመን ቢያንስ ሁለት ጊዜ የሚወደው በእርሱም ደስ የሚለው ልጁ መሆኑን መስክሯል (ማቴዎስ 3፡17፣ 17፡5፣ ማርቆስ 1፡10፣ 9፡17፣ ሉቃስ 3፡22፣ 9፡35)፡፡ እግዚአብሔር አብ በእንዲህ ያለ ሁኔታ የመሰከረለት አንድም ፍጥረት የለም፡፡ መላእክትና አማኞች ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ቢሆኑም የኢየሱስ ልጅነት የተለየ መሆኑንና አብ ለማንም አባትነቱን ባልገለፀበት የተለየ መንገድ ለኢየሱስ መናገሩን መጽሐፍ ቅዱስ በግልፅ አስፍሮልናል (ዕብራውያን 1፡5፣ ሉቃስ 20፡13)፡፡ ጌታችን ራሱን “አንድያ የእግዚአብሔር ልጅ (ሞኖጌኔስ)” በማለት ነው የገለፀው (ዮሐንስ 1፡13)፡፡ ይህ ደግሞ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነበት መንገድ ማንም አለመሆኑንና የእርሱ ልጅነት የተለየ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከአብ ወጥቶ ወደ ዓለም መምጣቱንም በመናገር የአብ ባሕርይ ተካፋይ መሆኑን በግልፅ ተናግሯል (ዮሐንስ 8፡42፣ 16:28)፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ አይሁድ ኢየሱስን ለምን ሊገድሉት ይፈልጉ እንደነበር ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡- “እንግዲህ ሰንበትን ስለ ሻረ ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ደግሞ ራሱን ከእግዚአብሔር ጋር አስተካክሎ፦ እግዚአብሔር አባቴ ነው ስላለ፥ ስለዚህ አይሁድ ሊገድሉት አብዝተው ይፈልጉት ነበር” (ዮሐንስ 5፡18)፡፡


 

[1] As to the phrase, “This day have I begotten thee,” there is a difference of view among both ancient and modern expositors. The word “begotten” (γεγέννηκα) naturally suggests μονογενὴς, and is hence taken by some as referring to the eternal generation of the Son; in which case it can have had no application in any conceivable sense to the human type. “This day” has also in this case to be explained as denoting the ever-present today of eternity. So Origen, in a striking passage,”It is said to him by God, to whom it is always today, for God has no evening, nor (as I deem) any morning, but the time which is coextensive with his own unbegotten and eternal life is (if I may so speak) the day in which the Son is begotten, there being thus found no beginning of his generation, as neither is there of the day.” Athanasius takes the same view; also Basil, Primasius, Thomas Aquinas, and many others. Source: Pulpit Bible Commentary

 

መሲሁ ኢየሱስ