ሙስሊም ሀገራትና የሃይማኖት ነፃነት
አንዳንድ ወገኖች በእስላማዊ ሀገራት ውስጥ ክርስቲያኖች መኖራቸውን በመጥቀስ እስልምና የሀይማኖት ነፃነትን የሚያከብር መሆኑን ለማሳየት ይሞክራሉ ዳሩ ግን ሙስሊም ሀገራት የአምልኮ ነፃነትን እንጂ የሃይማኖት ነፃነት እንደማይሰጡ አያስተውሉም፡፡ አብዛኞቹ ሙስሊሞች በቁጥር የሚበዙባቸው ሀገራት የአምልኮ ነፃነትን ይፈቅዳሉ እንጂ የሃይማኖት ነፃነት የሚባል ነገር የላቸውም፡፡ የዚህም ትርጉም ክርስቲያኖች በየቤተ ክርስቲያኖቻቸው ማምለክ ቢፈቀድላቸውም እምነታቸውን ለሙስሊሞች ማካፈል አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህም ሙስሊሞች ሌላ እምነት የመምረጥ ነፃነት እንደሌላቸው ያሳያል፡፡ የክርስትና ወሳኙ ክፍል ወንጌልን ለሌሎች ማካፈልና የክርስቶስ ተከታዮች እንዲሆኑ ማገዝ ነው (ማቴዎስ 28፡18-20)፡፡ ክርስቲያኖች ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ምንም እንኳን በየቤተ ክርስቲያናቸው ማምለክ ቢችሉም ሙሉ የሃይማኖት ነፃነት ተነፍጓቸዋል ማለት ነው፡፡ የአምልኮ ነፃነት አላቸው ሆኖም የሃይማኖት ነፃነታቸውን ተገፈዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ሙስሊሞቹም ሃይማኖታቸውን ለመቀየር ነፃነት ከሌላቸው ሙሉ የሃይማኖት ነፃነት የላቸውም ማለት ነው፡፡
በሌላ ወገን ደግሞ እነዚህ ሀገራት የሃይማኖት ነፃነትን በማክበር ሰዎች ሃይማኖታቸውን እንዲያስፋፉና እንዲቀይሩ ቢፈቅዱ እንኳ በሃይማኖት ነፃነት ላይ ገደብ የሚጥለውን የእስልምናን ሕግ አለመቀበላቸውን እንጂ እስልምና የሰዎችን የሃይማኖት ነፃነት ማክበሩን አያረጋግጥም፡፡ የሃይማኖት ነፃነትን በተመለከተ እስልምና ምን እንደሚያስተምር ለማወቅ ተከታዮቹን ጽሑፎች ያንብቡ፡-
የቁርኣን ኢ-ምክንያታዊ ትምህርት
የአክራሪ እስልምና ሁለቱ የማደናገርያ ጥቅሶች
እስልምናና ሽብርተኝነት