ሦስቱ የጂሃድ ደረጃዎች

ሦስቱ የጂሃድ ደረጃዎች

ጂሃድ ሦስት ደረጃዎች አሉት፡፡ የመጀመርያው ደረጃ አክራሪ ሙስሊሞች ደካሞችና ሙስሊም ያልሆኑ ሕዝቦች በሚበዙበት አገር ውስጥ ሲኖሩ የሚተገበር ነው፡፡ የአገሪቱን ሕግ በማክበር ቢኖሩም ነገር ግን ቁጥራቸውን በመጨመርና ኢኮኖሚያዊ የበላይነትን በመቀዳጀት ላይ በትጋት ይሠራሉ፡፡ በዚህ ደረጃ ሙሐመድ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ “በሃይማኖት ማስገደድ የለም” በማለት የተናገሩትን ቃል ተግባራዊ ያደርጋሉ (የላም ምዕራፍ 2፡256)፡፡ በአገሪቱ ውስጥ የሚተገበረው የንግግር ነፃነት የሚፈቅድላቸውን የመጨረሻ ነፃነት በመጠቀም በጽሑፍና በተለያዩ የመገናኛ አውታሮች በሌሎች እምነቶች ላይ ትችቶችን ይሰነዝራሉ፤ የአደባባይ ሙግቶችን ያደርጋሉ፤ በአካባቢው መገኘታቸው እንዲታወቅ እስላማዊ አልባሳትን ይጠቀማሉ፡፡

ሁለተኛው የጂሃድ ደረጃ የዝግጅት ደረጃ በመባል ይታወቃል፡፡ ተግባራዊ የሚሆነውም አክራሪ ሙስሊሞች ቁጥራቸው አናሳ ቢሆንም ነገር ግን ተፅዕኖ ማሳደር ወደሚችል ማሕበረሰብ ካደጉ በኋላ ነው፡፡ በዚህ ጊዜ በቀጣይ አገሪቱን ለመቆጣጠር በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በወታደራዊ ሥልጠናዎች፣ የጦር መሣርያዎችን በማከማቸትና በመሳሰሉት ራሳቸውን ያዘጋጃሉ (የጦር ዘረፋዎች ምዕራፍ 8፡59-60)፡፡ ምቹ ሁኔታዎች ሲፈጠሩላቸው ጥቃቶችን ይሰነዝራሉ፡፡ እስልምናን በአደባባይ የሚቃወሙትን ግለሰቦች በማጥቃት የትችት አንደበቶችን ይዘጋሉ፡፡ ራሳቸውን ከሌሎች ማሕበረሰቦች በመነጠል በእስላማዊ ሕጎች የሚተዳደሩትን አካባቢዎች ይፈጥራሉ፡፡ በዚህ መካከል ደግሞ ሙስሊም አሸባሪዎች ጥቃቶችን በፈፀሙ ቁጥር ሽብር እስላማዊ አለመሆኑንና እስልምና የሰላም ሃይማኖት መሆኑን በመስበክ ሕብረተሰቡን ግራ የሚያጋቡ ግለሰቦች ይኖራሉ፡፡ የተለያዩ የመገናኛ ብዙኀንን በገንዘብ በመደለል የእስልምናን በጎነት እንዲሰብኩ ያደርጋሉ፡፡

ሦስተኛውና የመጨረሻው የፍልሚያ ደረጃ ነው፡፡ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ አክራሪ ሙስሊሞች የግድ ከሌላው ሕብረተሰብ በቁጥር መብለጥ አይጠበቅባቸውም፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ በተጠቀሱት የዝግጅት መንገዶች ከሌላው ማሕበረሰብ ከተሻሉና ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የሚያመለክቱ ሁኔታዎች ካሉ ሙሉ እርምጃ ወደ መውሰድ ይገባሉ፡፡ ብዙ ጊዜ ፅንፈኛ ሙስሊም ጂሃዳውያን የአምላካቸው እርዳታ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆንና ድልን እንደሚሰጣቸው ከልባቸው ስለሚያምኑ አናሳዎች ሆነው ሳሉ እንኳ አገሪቱን ለመቆጣጠር ሙሉ ወደሆነ ፍልሚያ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ፍልሚያው የማያዋጣቸው ከሆነ ደግሞ ወደ መጀመርያው ወይም ወደ ሁለተኛው ደረጃ በመመለስ ትግሉን ለጊዜው ሊገቱት ይችላሉ፡፡[1]

————————-

[1] Mark A. Gabriel. Islam and Terrorism; 2002, pp. 85-89

 

እስልምናና ሽብርተኝነት