የአል-ፋቲሃ እርግማን

የአል-ፋቲሃ እርግማን

ቁርኣን በብዙ የእርማት ሥራዎች ውስጥ አልፎ አሁን ያለውን መልክ ቢይዝም ነገር ግን በሙስሊሞች ዘንድ እንከን አልባ እንደሆነ የአምላክ ቃል ይቆጠራል፡፡ ስለዚህ አንድ እውነተኛ ሙስሊም በውስጡ የሚገኙትን ትዕዛዛትና መመሪያዎች ለመፈፀም የቻለውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ ነገር ግን በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት ብዙ ትዕዛዛትና ትምህርቶች ፍቅርን፣ መቻቻልንና ሰላምን ከመስበክ ይልቅ ጥላቻን፣ አለመቻቻልንና ነውጠኝነትን ስለሚያስተምሩ ቁርኣንን አጥብቀው የሚይዙ ሙስሊሞች ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር ከመቸገር አልፈው ጥቃቶችን እስከመፈፀም ይደርሳሉ፡፡

በቁርኣን ውስጥ የሚገኙት ብዙ ጥቅሶች የሌሎች እምነቶችን አስተምህሮዎች፣ በተለይም ደግሞ ክርስትናንና ይሁዲን የሚያወግዙና የሚያንቋሽሹ በመሆናቸው ምክንያት አንድ ሙስሊም የሌሎችን እምነት ሳይነካና ሳይነቅፍ የራሱን ብቻ መከተል አይችልም፡፡ የቁርኣን መክፈቻ በሆነው “አልፋቲሃ” ተብሎ በሚጠራው ምዕራፍ ሰባተኛው ቁጥር ላይ እንዲህ የሚል ቃል ተጽፎ እናነባለን፡- “የነዚያን በነርሱ ላይ በጎ የዋልክላቸውን በነሱ ላይ ያልተቆጣህባቸውንና ያልተሳሳቱትንም ሰዎች መንገድ (ምራን በሉ)፡፡” በሙሐመድ ትውፊቶች  መሰረት አላህ የተቆጣባቸው ሰዎች አይሁዶች ሲሆኑ የተሳሳቱት ደግሞ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡[1] ሙስሊሞች ይህንን ጸሎት በቀን አስራ ሰባት ጊዜ ይደግሙታል፡፡ ይህንንም ሲያደርጉ አይሁዶች በአምላክ ቁጣ ሥር ያሉና ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ መሆናቸውን ያውጃሉ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ አንድ ሙስሊም ዕድሜ ልኩን ሳያቋርጥ ስለ ሌሎች እምነቶች ተከታዮች እያሰበና እምነታቸውን እየነቀፈ እንዲኖር ያደርገዋል፡፡ እንዲህ ዓይነት ጥቅሶች እስካሉ ድረስ ሙስሊሞች የሌሎችን እምነት ሳይነኩ መኖር አይቻላቸውም፡፡

[1] Dr. Muhammad Taqi-ud-Din al-Hilali and Dr. Muhammad Muhsin Khan, Interpretation of the Meanings of the Noble Qur’an in the English Language with Comments from Tafsir At-Tabari, Tafsir Al-Qurtubi and Tafsir Ibn Kathir and Ahadith from Sahih Al-Bukhari, Sahih Muslim and other Ahadith books [Darussalam Publishers & Distributors, Riyadh, Lahore, Houston, New York], Part 1: From Surah 1 to 5, p. 30