መጽሐፍ ቅዱስና ሥነ ቁፋሮ

መጽሐፍ ቅዱስና ሥነ-ቁፋሮ

ሥነ-ቁፋሮ ቅሪተ አካላትን፣ ጥንታውያን መዛግብትንና የሰው እጅ አሻራዎች ያረፉባቸውን ቅርሶች የሚያጠና የሳይንስ ዘርፍ ነው፡፡ ይህ የጥናት ዘርፍ በተለይም ባለፉት ሁለት ምዕተ ዓመታት አስደናቂ ውጤቶችን ያስገኘ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስን በተመለከተ የነበሩትን የተሳሳቱ አመለካከቶች በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል፡፡ በተለይም በቅድስት አገርና  በሜድትራንያን ባህር አካባቢ በሚገኙ አገራት የሚደረጉ ምርምሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ትክክለኛነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጎሉት ይገኛሉ፡፡ በእርግጥ ሥነ ቁፋሮ መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ቀጥተኛ የሆነ ማስረጃ መሆን ባይችልም ነገር ግን ትኣማኒነቱን በማረጋገጥ የእግዚአብሔር ቃል ስለመሆኑ ተዘዋዋሪ ማስረጃ በመሆን ያገለግላል፡፡

የመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ-ቁፋሮ ምርምርም ራሱን እንደቻለ የጥናት ዘርፍ የጎለበተ ሲሆን “ፓለስቲኖሎጂ” በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ዘርፍ በምርምሩ ዓለም ከበሬታን ካተረፉ ክርስቲያን አርኪዎሎጂስቶች መካከል ጆርጅ ኢርንስት ራይት (1909-1974) እና ዊልያም ፎክስዌል አልብራይት (1891-1971) ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህ ምሑራንን ጨምሮ ስለ ዘርፉ ዕውቀት ያላቸው ወገኖች ከሰጧቸው አስተያየቶች መካከል ጥቂቶቹን እንደሚከተለው እንጠቅሳለን፡-

ዊሊያም ኤፍ. አልብራይት፡- “በ18ውና በ19ው ክፍለ ዘመናት በነበሩ ወሳኝ የታሪክ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተሰነዘሩ ከልክ ያለፉ ጥርጣሬዎችና ዛሬም በየጊዜው የሚታዩት ውሱን ገጽታዎች የሚሰጣቸው ክብደት በሂደት እየወረደ ይገኛል፡፡ ተከታታይ ግኝቶች ኁልቁ መሣፍርት የሌላቸውን ዝርዝሮች ትክክለኛነት አረጋገጠዋል፤ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ጠቃሚ የታሪክ ምንጭ ያለውን እሴት አጉልተዋል፡፡”

ሚለር ቡሮውስ፡- “በአጠቃላይ የሥነ-ቁፋሮ ሥራ በማያጠያይቅ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ ተዓማኒነት ላይ ያለውን መተማመን አጠናክሯል፡፡”

ኔልሰን “እስከዛሬ ድረስ በትክክል የተረዳነውን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ንግግር እንኳ የተጻረረ የሥነ-ቁፋሮ ግኝት የለም።” (Jay Smith. The Bible in the British Museum and in the British Library, p. 14)

የእነዚህን ምሑራን ምስክርነት ሊያረጋግጡ ከሚችሉ ግኝቶች መካከል የተወሰኑትን እንደሚከተው እንጠቅሳለን፡-

  1. በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ ምዕራፍ 9 እና 10 ላይ አክአብ የተሰኘውን
    ንጉሥና ሚስቱ ኤልዛቤልን ይበቀል ዘንድ እግዚአብሔር ኢዩን ንጉሥ

የእስራኤል ንጉሥ ኢዩ ለአሦር ንጉሥ ለስልምናሶር ሲገብር የሚያሳይ ምስል (9ኛው ክ.ዘ. ቅድመ ክርስቶስ)
የፎቶ ምንጭ፡ Oxford Bible Atlas 4th Edition

ይሆን ዘንድ እንደቀባው እናነባለን፡፡ ይህ የምትመለከቱት ቅርጽ “ጥቁሩ ሃውልት” በመባል የሚታወቅ ሲሆንኢዩ ሣልሳዊ ስልምናሶር በመባል ለሚታወቅ የአሦር ንጉሥ ሲገብር ያሳያል፡፡ በሁለተኛው ረድፍ ላይ በግምባሩ ተደፍቶ ሲሰግድ የሚታየው ኢዩ እንደሆነ በሃውልቱ ላይ የተቀረፀው የኩይኒፎርም ጽሑፍ ይናገራል (ያደገውን ምስል ይመልከቱ)፡፡ ኢዩ ክፉ ነገሥታትንና የበኣል ካህናትን በማጥፋት መልካም ነገሮችን ቢሠራም በፍጻሜው በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ተግባራትን እንደፈጸመ በ2ነገሥት 10፡28-31 ተጽፏል፡፡ ስለዚህ በዚህ ሃውልት ላይ ተስሎ እንደምንመለከተው ለአረማዊ ንጉሥ ቢገብር አያስገርምም፡፡ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከጥንት የእስራኤል ነገሥታት መካከል ስሙ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ በቀደምትነት ተጽፎ የተገኘው ኢዩ ሲሆን ይህ ሃውልት የተቀረፀበት ዘመንና መጽሐፍ ቅዱስ ኢዩ እንደነገሠ የሚናገርበት ዘመን በትክክል ይገጥማል፤ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ኢዩ የተባለ ሰው በዚያ ዘመን በእስራኤለ ላይ መንገሡን መናገሩ
ትክክል መሆኑ ተረጋግጧል ማለት ነው፡፡ (በተጨማሪም ሣልሳዊ ስልምናሶር በ2ነገሥት 17፡3 ላይ ተጠቅሷል፡፡)

  1. በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 15፡19-20 እና በ 1ዜና 5፡26 ላይ መጽሐፍ ቅዱስ በቅፅል ስሙ “ፎሐ” ብሎ ስለሚጠራው ቴልጌልቴልፌልሶር ስለ

    ቴልጌልቴልፌልሶር በሰረገላው ላይ ተቀምጦ የሚያሳይ ጥንታዊ የድንጋይ ላይ ቅርፅ
    የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum tour

    ተባለ የአሦር ንጉሥ እናነባለን (745-727 ቅ.ክ.)፡፡ ይህ ንጉሥ እስራኤል በመባል የሚታወቀውን የአስሩን ነገዶች ግዛት ሁለቴ ያጠቃ ሲሆን በመጀመርያው ጥቃት ምናሔም የተባለ ንጉሥ ለእርሱ ለመገበር ስለተስማማ አገሪቱን ሳያጠፋ ተመልሷል (2ነገሥት 15፡19-20)፡፡ በሁለተኛው ጥቃት ወቅት ግን የተወሰኑ የእስራኤል ከተሞችን በመያዝ ነዋሪዎቻቸውን በምርኮ ወስዷል (2ነገሥት 15፡29)፡፡ የምንመለከታቸው የዲንጋይ ላይ ቅርጾች የዚህ ንጉሥ ምስሎች ሲሆኑ ንጉሡ በሰረገላ ላይ ተቀምጦ በሚታይበት ቅርፅ ላይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰው ፎሐ የሚለው ቅጽል ስሙ ተጽፎ ይነበባል፡፡ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ትክክለኛነት ያረጋግጣል፡፡

በብሪቲሽ ሙዚየም ውስጥ የሚገኝ የቴልጌልቴልፌልሶር ምስል፡፡
የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum tour

  1. በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 17፡6፣24 ላይ የአሦር ንጉስ ዳግማዊ ሳርጎን (በዚህ ሃውልት ላይ ምስሉ በግራ በኩል የሚታየው) የሰሜኑን የእስራኤል ግዛ

    ዳግማዊ ሳርጎን (722-701 ቅ.ክ.) እና ልጁ ሰናክሬም (704-681 ቅ.ክ.)
    የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum tour

    ት በመውረር ለእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታማኞች ያልነበሩትን አስሩን የእስራኤል ነገዶች ማርኮ እንደወሰዳቸው እናነባለን፡፡ በኢሳይያስ 20፡1 ላይ ይህ ንጉሥ “ሳርጎን” በሚለው ስሙ ተጠቅሶ እናገኛለን፡፡ የሚገርመው ነገር በዚህ ንጉሥ የተቆረቆረችው የኮርሳባድ ከተማ በ1843 ዓ.ም.  በቁፋሮ እስከተገኘችበት ጊዜ ድረስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሰው በስተቀር ስለ እርሱ የሚታወቅ ነገር አልነበረም፡፡ ይህ ንጉሥ የደቡቡን የእስራኤልን መንግሥት (ይሁዳን) ማሸነፍ ያልቻለ ሲሆን ልጁ ሰናክሬም ግን (በሃውልቱ ላይ ምስሉ በቀኝ በኩል የሚታየው) በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ኢየሩሳሌምን በመክበብ አስጨንቋል (2ነገሥት 18፡17-19፡37)፡፡ ታላቂቱ የነነዌ ከተማ የተቆረቆረችውም በሰናክሬም ነበር፡፡

  1. በ701 ዓ.ዓ. ሰናክሬም ለኪሶ የተባለችውን የተመሸገች የይሁዳ ከተማ ተዋግቶ ያዘ፤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ከበባት፡፡ ይህ ታሪክ በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 18 እና 19 ላይ በስፋት ተዘግቦ ይገኛል፡፡ ይህ በለኪሶ ከተማ በሥነ ቁፋሮ

    በለኪሶ የተገኘ የሰናክሬም የጦርነት ውሎዎች የተመዘገቡበት ባለ ስምንት ጎን ቅርፅ፡፡ በዚህ ቅርፅ ላይ ሕዝቅያስን በተመለከተ በተጻፉ ጽሑፎች ውስጥ “በወጥመድ ውስጥ እንዳለች ወፍ ሕዝቅያስን በዋና ከተማው በኢየሩሳሌም ውስጥ ከበብኩት” የሚል አረፍተ ነገር ይገኝበታል፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum tour

    ሊቃውንት የተገኘው ባለ ብዙ ጎን ቅርፅ የሰናክሬምን የጦርነት ታሪኮች የሚናገር ነው፡፡ በዚህ ቅርፅ ላይ የለኪሶ መያዝና የኢየሩሳሌም ከበባ ተዘግቧል፡፡ የሚገርመው ነገር በዚህ ባለ ስምንት ጎን ቅርፅ ላይ የተጻፈው ጽሑፍ ሕዝቅያስ በሰናክሬም ላይ ማመጹን፣ የተመሸጉ የይሁዳ ከተሞች መያዛቸውን፣ ሕዝቅያስ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጣ ተከቦ መታፈኑን፣ የወርቅ ግብር ለሰናክሬም መስጠቱን፣ ኢየሩሳሌም አለመያዟንና አሦራውያን ምንም ዓይነት ጥቃት ሳይሰነዝሩ መመለሳቸውን በተመለከተ ሙሉ በሙሉ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ ሲሆን ነገር ግን አሦራውያን በኢየሩሳሌም ላይ አንድ ቀስት እንኳ ሳይወረውሩ የተመለሱበትን ሚስጥር በዝምታ አልፎታል፡፡ ይህ አረማዊ ንጉሥ ለመናገር ያፈረበትን ሚስጥር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ በማለት ይነግረናል፡-  “ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል። ወደዚች ከተማ አይመጣም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፥ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም። በመጣበት መንገድ በዚያው ይመለሳል፥ ወደዚህችም ከተማ አይመጣም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ ስለ እኔም፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ።

በዚያችም ሌሊት የእግዚአብሔር መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ። የአሦርም ንጉሥ ሰናክሬም ተነሥቶ ሄደ፥ ተመልሶም በነነዌ ተቀመጠ። በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አደራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት ወደ አራራትም አገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።” 2ነገሥት 19፡32-37

ነነዌ ከተማ የሰናክሬም ቤተ መንግሥት ግድጊዳ ላይ ተስሎ የተገኘ የይሁዳ ከተማ የሆነችውን የለኪሶን ከበባ የሚያሳይ ቅርጽ (2ነገሥት 18፡13-14)፡፡ ሰናክሬም በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ የከተማይቱን ምርኮ ሲቀበል ያሳያል፡፡ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እውነት መሆኑን ያረጋገጠ ግኝት ነው፡፡ የፎቶ ምንጭ፡ Oxford Bible Atlas Fourth Edition

  1. በመጽሐፈ ነገሥት ካልዕ እና በመጽሐፈ ዜና ካልዕ 32፡30 ላይ ንጉሥ ሕዝቅያስ ውኃን ከአንዱ የኢየሩሳሌም ከተማ ጥግ ወደሌላው ለመ


    530 ሜትር የሚረዝመው አስደናቂው የሕዝቅያስ የውኃ ማስተላለፍያ መስመር፡፡ በማስተላለፍያው ውስጥ አሁንም ውኃ ይታያል፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ bibleplaces.com

    ውሰድ ማስተላለፍያ ሰርቶ እንደነበር ተጽፏል፡፡

“የቀረውም የሕዝቅያስ ነገር፥ ጭከናውም ሁሉ፥ ኵሬውንና መስኖውንም እንደ ሠራ፥ ውኃውንም ወደ ከተማይቱ እንዳመጣ፥ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?” 2ነገሥት 20፡20

“ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።” 2ዜና 32፡30

የዚህ አስደናቂ ታሪካዊ ቅርስ ግኝት መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተዘገበው ታሪክ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጧል፡፡ የ S ቅርፅ ያለው ይህ ማስተላለፍያ አሠራሩ አስገራሚ ሲሆን በሥራው ሂደት ወቅት ስለነበረው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ “የሲሎአም (ሳሊሆም) ቅርፅ” በመባል የሚታወቅ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በ1880 ዓ.ም. በጊዮን ምንጭ ውስጥ ሲታጠብ በነበረ ወጣት ልጅ ተገኝቷል፡፡ ይህ ጽሑፍ ቆፋሪዎቹ ከሁለት ተቃራኒ አቅጣጫዎች መቆፈር እንደጀመሩና በአንድ ነጥብ ላይ እንደተ

በቱርክ ኢስታምቡል ሙዝየም ውስጥ የሚገኘው የሳሊሆም ቅርፅ በመባል የሚጠራው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ፡፡
የፎቶ ምንጭ፡ Oxford Bible Atlas, Fourth Edition

ገናኙ ይገልፃል፡፡ በአሁኑ ወቅትም በቱርክ አገር ኢስታምቡል ከተማ በሚገኝ ቤተ መዘክር ውስጥ ተቀምጧል፡፡ የሕዝቅያስ የውኃ ማስተላለፍያ መስመርና በስድስተኛው ክፍለ ዘመን ቅ.ክ. የተሠራው በግሪክ አገር የሚገኘው የኢውፋሊዮስ የውኃ ማስተላለፍያ ከጥንቶቹ የውኃ ምህንድስና ቴክኖሎጂዎች መካከል ግንባር ቀደሞቹ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል፡፡

  1. ሰናክሬም ይሁዳን ለማጥቃት በወጣበት ጊዜ ግብፅን ይገዛ የነበረ ቲርሐቅ የተባለ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ ሊወጋው በመገስገስ ላይ መሆኑን ስለሰማ ወደ ሕዝቅያስ የማስፈራርያ መልዕክት ብቻ በመላክ ሊፈጽመው የነበረውን ጥቃት ወ


    ከክርስቶስ ልደት በፊት በ664 ዓ.ዓ. የተሰራ በኑቢያ የተገኘ ግብፅን ይገዛ የነበረው የኢትዮጵያዊው ንጉሥ የቲርሐቅ ሃውልት፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ ብሪቲሽ ሙዚየም formerthings.com

    ደ ሌላ ጊዜ በማስተላለፍ እንደተመለሰ በ2ነገሥት 19፡9 ላይ እናነባለን፡፡ የምትመለከቷቸው የድንጋይ ሃውልቶች እስከተገኙበት ጊዜ ድረስ ቲርሐቅ አፈታሪክ ብቻ እንደሆነ ይታሰብ ነበር፡፡

ግብፅን ይገዛ የነበረው የኢትዮጵያዊው ንጉሥ የቲርሐቅ ስም የተጻፈበት የድንጋይ ቅርፅ፡፡
የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum tour

  1. በዕዝራና በነህምያ መጻሕፍት ውስጥ ቂሮስ የተሰኘ ንጉሥ አይሁድን ጨምሮ በባቢሎን የነበሩ ምርኮኛ ሕዝቦች ወደ አገሮቻቸው እንዲ

    ንጉሥ ቂሮስ በግዛቱ ስር የሚገኙ ምርኮኛ ሕዝቦች ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ትዕዛዝ እንዳወጣ የሚገልጽ ጥንታዊ የሸክላ ጽሐፍ፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ Jay Smith, British Museum Tour

    መለሱ አዋጅ እንዳወጣ እናነባለን፡፡ ነገር ግን አንድ ንጉሥ በእርሱ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ምርኮኛ ሕዝቦች ወደ አገሮቻቸው በመመለስ እንዲደራጁና እንዲጠናከሩ በመፍቀድ ለራሱ አገዛዝ ስጋት ሊፈጥር የሚችል ትዕዛዝ ሊያወጣ አይችልም በሚል መነሻ ብዙ ምሑራን በመጽሐፍ ቅዱሱ ታሪክ ላይ ጥርጣሬ ነበራቸው፡፡ ነገር ግን በዚህ ፎቶ ግራፍ ላይ በሚታየው ባሕላዊ የንብ ቀፎ መሳይ ሲሊንደር ላይ የተቀረፀው ጽሑፍ በቂሮስ ዘመን የተጻፈ ሲሆን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኘው ታሪክ ጋር ሙሉ በሙሉ ይስማማል፡፡ ይህም የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪኮች ተዓማኒነት ያረጋገጠ ሌላ ግኝት ሆኗል፡፡

  2. የጌታ ወንድም ያዕቆብ የኢሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን መሪ እንደነበር የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ይናገራል፡፡ ጆሲፈስ ፍላቭየስ ያዕቆብ በሊቀ ካህኑ በሐናንያ ውሳኔ መሠረት በድንጋይ ተወግሮ መሞቱን ዘግቧል፡፡ በ2002 ዓ.ም. “ዲስከቨሪ” በተሰኘ የቴሌ ቪዥን ጣብያና “ቢብሊካል አርኪዎሎጂ ሶሳይቲ” በተባለ ተ

    የጌታ ወንድም የያዕቆብ አጥንት እንደ ተቀመጠበት የሚገልፅ የአራማይክ ጽሑፍ ያለበት የመጀመርያው ክፍለ ዘመን ሳጥን፡፡ ይህ ሳጥን የተገኘው በኢየሩሳሌም አካባቢ በቄድሮን ሸለቆ ውስጥ ነው፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ time magazine (time.com)

    ቋም ትብብር በተዘጋጀ የዋሽንግተን ፕሬስ ኮንፍረንስ ላይ በመጀመርያው ክፍለ ዘመን የተሠራ የያዕቆብ አጥንት የተቀመጠበት የድንጋይ ሳጥን መገኘቱ ይፋ ሆኖ ነበር፡፡ ነገር ግን የእስራኤል የጥንታዊ መዛግብት ባለሥለጣን ጽሕፈት ቤት ሳጥኑ በመጀመርያው ክፍለ ዘመን መሠራቱን አምኖ ነገር ግን በዚህ ሳጥን ላይ በተቀረፀው “የኢየሱስ ወንድም የዮሴፍ ልጅ ያዕቆብ” በሚለው የአረማይክ ቋንቋ ጽሑፍ ውስጥ የኢየሱስ ወንድም የሚሉት ቃላት ተመሳስለው የተጻፉ እንጂ እውነተኞች አይደሉም በማለት ቅርሱን በሸጠው ኦዴድ ጎላን በተባለ ኢንጂነርና የጥንታዊ ቅርሳ ቅርሶች አጥኚ ላይ ክስ መስርቶ ነበር፡፡ ነገር ግን ጉዳዩን ሲመለከት የነበረው ፍርድ ቤት እነዚህ ቃላት የተጭበረበሩ ስለመሆናቸው ማስረጃ ባለማግኘቱ የተነሳ የመጀመርያውን ክስ ውድቅ በማድረግ “ሕገ ወጥ የቅርስ ንግድ” በሚል ክስ ብቻ ተጠያቂ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ቅርሱን በባለቤትነት የያዘው በካናዳ አገር የሚገኘው ሮያል ኦንታሪዮ ቤተ መዘክር ዘመናዊ ምርመራዎችን በመጠቀም እነዚህ ቃላት የተጭበረበሩ እንዳልሆኑ ቢያስታውቅም ነገር ግን ክርክሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ለማንኛውም ይህንን እሰጥ አገባ ጊዜ የሚፈታው ቢሆንም፡፡ 

    በቂሣርያ የተገኘው የጲላጦስ ቅርፅ በመባል የሚታወቀው የድንጋይ ላይ ጽሑፍ፡፡ ይህ ቅርስ በአሁኑ ወቅት በእስራኤል ቤተ መዘክር ውስጥ ይገኛል፡፡
    የፎቶ ምንጭ፡ የእስራኤል ቤተ መዘክር ድረ ገፅ (imjnet.org.il)

  3. ጌታችን ኢየሱስ በተሰቀለበት ዘመን የይሁዳን ግዛት ያስተዳድር የነበረው ጲላጦስ የተባለ ሮማዊ እንደ ነበርና እንዲሰቀል በመፍረድም አሳልፎ የሰጠው እርሱ እንደ ነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ በ1961 ዓ.ም. በቂሣርያ ከተማ ቁፋሮ ሲያደርጉ የነበሩ ጣልያናውያን የሥነ ቁፋሮ ተመራማሪዎች በምስሉ ላይ የምትመለከቱትን የድንጋይ ላይ ቅርፅ እስካገኙበት ጊዜ ድረስ ይህ ሰው ይታወቅ የነበረው በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች ጥንታውያን ጽሑፎች ውስጥ ብቻ ነበር፡፡
  4. በአዲስ ኪዳን ውስጥ ከሚገኙ መጻሕፍት መካከል እንደ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ የብዙ ምሑራንን ትችቶች ያስተናገደ መጽሐፍ የለም፡፡ ነገር ግን በሚያስገርም ሁኔታ የሥነ ቁፋሮ ግኝቶች እነዚህ ውንጀላዎች ስህተት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ቀደም ሲል ያነሳናቸው ሰር ዊሊያም ራምሰይ የተባሉ ዕውቅ ምሑር የሉቃስ ጽሑፎች የፈጠራ ታሪኮች መሆናቸውን የሚያምኑ ሰው ነበሩ፡፡ ነገር ግን በትንሹ ኢስያ (ቱርክ) ውስጥ ለምርምር ሲዘዋወሩ በነበሩበት ዘመን ካገኟቸው ብዙ ማስረጃዎች የተነሳ ሉቃስ ከመጀመርያ ደረጃ የታሪክ ጸሐፊዎች ተርታ መመደብ እንዳለበት ተናግረው ነበር፡፡

ይህ የድንጋይ ላይ ጽሑፍ በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተቀረፀ ሲሆን በተሰሎንቄ ከተማ የተገኘ ነው፡፡ ፖሊታርክ በመባል የተጠሩ ስድስት ሰዎችን ይጠቅሳል፡፡ በአሁኑ ወቅት ንብረትነቱ የብሪቲሽ ቤተ መዘክር ነው፡፡
የፎቶ ምንጭ፡ holylandphotos.org

በምርምር ሰዎች መካከል በሰፊው ሲናፈሱ ከነበሩ ውንጀላዎች መካከል በሐዋርያት ሥራ 17፡5-6 ላይ ሉቃስ የተሰሎንቄ ከተማ መሪዎችን ሲጠራ “አለቆች” የሚል ማዕረግ መጠቀሙ ይጠቀሳል፡፡ ይህ ቃል “ፖሊታርክ” ከሚል የግሪክ ቃል የተተረጎመ ሲሆን ሉቃስ “ስትራቲጎይ” (ሹማምንት) ከሚለው የተለመደ ቃል ይልቅ በየትኛውም ጥንታዊ የግሪክ መዝገብ ውስጥ በዚያ ዘመን ለነበሩ ባለ ሥልጣናት ያልተሰጠን ማዕረግ መጠቀሙ እንደ ትልቅ የታሪክ ቅጥፈት ተቆጥሮ ሲያስተቸው ነበር፡፡ ነገር ግን በ1960 ዓ.ም. በተሰሎንቄ ከተማ ውስጥ የተገኙ በቁጥር 19 የሚያህሉትን ጨምሮ 32 “ፖሊታርክ” የሚለውን ቃል የያዙ ጥንታውያን የድንጋይ ላይ ጽሑፎች የሉቃስን ትክክለኛነት አረጋግጠዋል፡፡ በተሰሎንቄ ከተማ ከተገኙት ከአስራ ዘጠኙ መካከል ሦስቱ በመጀመርያው ክፍለ ዘመን የተቀረፁ ነበሩ፡፡

እንግዲህ ከላይ የተመለከትናቸው የሥነ ቁፋሮ ግኝቶች በጣም በርካታ ከሆኑ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ተያያዥነት ካላቸው ግኝቶች መካከል በጣም ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ አነዚህና መሰል ሌሎች ማስረጃዎች መጽሐፍ ቅዱስ እውነት ለመሆኑ ጠንካራ ማሳያዎች ናቸው፡፡ ይህንን ርዕስ የምንቋጨው ታዋቂው እስራኤላዊ የሥነ  ቁፋሮ ምሑር ኔልሰን ግሉክ የተናገሩትን በድጋሚ በመጥቀስ ይሆናል፡- “እስከዛሬ ድረስ በትክክል የተረዳነውን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ንግግር እንኳ የተጻረረ የሥነ-ቁፋሮ ግኝት የለም።”

መጽሐፍ ቅዱስ ተዓማኒ ቃለ እግዚአብሔር ነውን? ዋናው ማውጫ

መጽሐፍ ቅዱስ