የሙሐመድ መገለጥ ከሰይጣን ዘንድ ከሆነ መልካም ትምሕርቶች እንዴት በውስጡ ሊገኙ ቻሉ?

የሙሐመድ መገለጥ ከሰይጣን ዘንድ ከሆነ መልካም ትምሕርቶች እንዴት በውስጡ ሊገኙ ቻሉ?


“ሙሐመድን ያነሳሳው ሰይጣን ከሆነ እንዴት አስካሪ መጠጥንና ሌሎች ክፉ ነገሮችን ሊከለክል ይችላል? ክፉ ነገሮችን የሚከለክል የትኛው ሰይጣን ነው?” ክርስቲያኖች የሙሐመድን የመገለጥ አቀባበል ፀሊም ገፅታዎች ጠቅሰው ምንጩ ከክፉ መንፈስ ዘንድ እንደሆነ በጠቆሙ ቁጥር ይህንን የሚመስል ምላሽ ከሙስሊም ወገኖች ዘንድ መስማት የተለመደ ነው፡፡

ሰይጣን የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን እንደሚለውጥና አገልጋዮቹም የጽድቅ አገልጋዮች ለመምሳል ራሳቸውን እንደሚለውጡ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡-

“ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።” (2ቆሮ. 11፡14-15)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ሐሰተኛ ነቢያትን የበግ ለምድ ከለበሱ ተኩላዎች ጋር አመሳስሏቸዋል፡፡ (ማቴ. 7፡15-20)

በዓለም ታሪክ የተነሱት ዞራስተር፣ ማኒ፣ በሃኡላና ጆሴፍ እስሚዝን የመሳሰሉት ሐሰተኛ ነቢያት ብዙ መልካም ነገሮችን አስተምረዋል፡፡ ነገር ግን መልካም ነገሮችን ማስተማራቸው ሐሰተኛ ነቢያት እንዳይሆኑ አላደረጋቸውም፡፡ ልክ እንደዚሁ በቁርአንና በሌሎች እስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ መልካም ነገሮችን የሚያዙ ትዕዛዛት መኖራቸው ሙሐመድን እውነተኛ ነቢይ አያደርገውም፡፡ ሐሰተኛ ነቢያት ሁሉ መልካም ትዕዛዛትን ትክክለኛውን ማንነታቸውን ለመሰወር እንደ ለምድ ይጠቀማሉ፡፡ እንዲያ ባይሆን ኖሮ የሐሰተኛ ነቢያት ተከታዮች ሁሉ ነቢያቱን በመከተል ባልተታለሉ ነበር፡፡ ሰይጣን “ሰይጣን ነኝ” ብሎ አፍጥጦ አግጥጦ አይመጣም፡፡ ነገር ግን  ሰይጣንነቱን ለመሰወር “ከሰይጣን ተጠንቀቁ” እያለ ሊያምታታ ይችላል፤ መልካም ነገሮችንም ለክፋቱ መሸፈኛነት ይጠቀማል፡፡ ከበስተጀርባው ግን ነፍሳችንን የሚያጠፋ ወጥመድን ያዘጋጃል፡፡ የተመረዘ ምግብ 99% ምግብ ሆኖ መርዙ ግን 1% ወይም ከዚያ ያነሰ ሊሆን ይችላል፡፡ የምግቡ መልክ፣ ሽታና ጣዕም መመረዙን ላይጠቁም ይችላል ነገር ግን ዋናው ጉዳይ ገዳይነቱ በመሆኑ 99% ምግብ መሆኑ መልካም አያሰኘውም፡፡ የሐሰት ነቢያት ትምሕርትም እንደዚያው ነው፡፡ ከውጪ መልካም መስሎ ቢታይም ነፍስን አደጋ ላይ የሚጥል የሰይጣን መርዝ አለበት፡፡ ገዳደይ ነው፡፡

ሐሰተኛ ነቢይ የመነኩሴ ልብስ ለብሶ፣ መስቀልና መቋሚያ ይዞ በሚዞር ነገር ግን ከልብሱ ስር ሰይፍ በታጠቀ ወንበዴ ሊመሰል ይችላል፡፡ እንዲያ ያለውን ሰው እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው መስሏችሁ በቤታችሁ ልትቀበሉትና ምግብና ማረፍያ ልትሰጡት ትችላላችሁ፡፡ አክብራችሁም እግሩን ልታጥቡትና እንዲመርቃችሁ ከፊቱ ቆማችሁ እጃችሁን ዘርግታችሁ አንገታችሁን ዝቅ አድርጋችሁ የበረከት ቃሉን ልትጠባበቁ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን በማንኛውም ሰዓት ከልብሱ ስር የታጠቀውን ሰይፍ በመምዘዝ አንገታችሁን ሊያሳጣችሁ ይችላል፡፡ ከዚያስ? ከዚያማ ቤትና ንብረታችሁን ይዘርፋል፣ ሚስታችሁን ዕቁባት ያደርጋል፣ የ9 ዓመት ልጃችሁን ያገባል፡፡ ልብሱ የእውነተኛ ማንነቱ መሸፈኛና እናንተ ትቀበሉት ዘንድ ማታለያ እንጂ ትክክለኛ ገፅታው አይደለምና፡፡ አስተዋይ ሰው ቢጫ ልብስ የለበሰውን ሁሉ ማንነቱን ሳያጣራ የእግዚአብሔር ሰው ነው ብሎ ወደ ቤቱ በማስገባት ራሱንና ቤተሰቡን ለአደጋ አያጋልጥም፡፡ ማንነቱን ያጣራል፣ መታወቂያውን ይመለከታል፣ በቃልና በተግባር ይፈትነዋል፡፡ ልክ እንደዚሁ ነቢይ ነኝ ያለው ሁሉ መልካም ነገሮችን ስለተናገረ ብቻ አንቀበለውም፡፡ በቀደሙት ነቢያት ሚዛን እንመዝነዋለን፣ ከአምላክ ለመሆኑ ማረጋገጫ የሚሆን በቃሉ የተደገፈ ምልክት ይኖር እንደሆን እናያለን፣ ትምሕርቱና ሕይወቱ መጣጣም አለመጣጣማቸውን እንፈትሻለን፡፡

ሙሐመድ የተወሰኑ መልካም ትዕዛዛትን ቢያስተምርም በቃልና በተግባር ያስተማራቸው መጥፎ ነገሮች በዓለም ላይ ከተነሱት ሐሰተኛ ነቢያት ሁሉ በከፋ ሁኔታ ጎልተው የሚታዩ መሆናቸው ሐሰተኝነቱን ከጥርጣሬ በጸዳ ሁኔታ ያረጋግጣል፡፡ ለበለጠ መረጃ የሙሐመድን ነቢይነት የማልቀበልባቸው 12 ምክንያቶች በሚል ርዕስ የተጻፈውን ጽሑፍ ይመልከቱ፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሐሰተኛ ነቢያት የተናገረውን በማስታወስ ጽሑፋችንን እንቋጫለን፡-

“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ። ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል። መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ።” (ማቴ. 7፡15-20)

በዚህ የጌታችን መርህ መሠረት እስልምና ምንም ይበል ምን በዘመናት መካከል ካፈራቸው መራራና ገዳይ ፍሬዎቹ በመነሳት መሠረቱ ሐሰትና ፀረ-ሰላም መሆኑን መስራቹም ከእግዚአብሔር ያልተላከና ሐሰትን ያስተማረ መሆኑን መደምደም እንችላለን፡፡ የኩርንችት ዘር በወይን ቅጠል ተጠቅልሎ ስለተቀበረ የወይንን ፍሬ የሚያፈራ ዛፍ ወደመሆን ማደግ እንደማይችል ሁሉ ሐሰተኛ ነቢያት የሚያስተምሩት ትምህርትም ምንም ያህል ለጆሮ የሚጣፍጥና በጥሩ ቃላት የተቀመመ ቢሆን መልካም ውጤትን ሊያስገኝ አይችልም፡፡ በእስልምና ውስጥ መልካም ትምሕርቶች እንዳሉ ባንክድም መልካም ትምሕርቶቹ መሸፈኛ እንጂ ትክክለኛ ገፅታው ባለመሆናቸው እስልምና የተስፋፋበት ዓለም የመልካም ነገር ምንጭ ከመሆን ይልቅ የሽብርና የእልቂት ዓለም ሆኗል፡፡ የእስልምና ፍሬዎችም የሽብር ቡድኖችና የተደራጁ ነፍሰ ገዳዮች ሆነው እናያቸዋለን፡፡ ትክክለኞቹ የእስልምና ትምህርት ባሕርይ ማሳያዎች እነርሱ ናቸው፡፡ እናም ሙሐመድ ሐሰተኛ ነቢይ፣ እስልምናም መሠረቱ ሐሰት ነው፡፡


 

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሙሐመድ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ አለመሆኑን የሚገልጥ ጥንታዊ ታሪክ

የሙሐመድ አሟሟት ሐሰተኛ ነቢይ መሆኑን ያረጋግጣል

 

ሙሐመድ