የቁርኣን ምዕራፎች ስያሜ
ቁርኣን 114 ሱራዎች (ምዕራፎች) ያሉት ሲሆን የአንቀፆቹ (የቁጥሮቹ) ብዛት 6236 ናቸው፡፡ በየጊዜው ለማንበብ እንዲያመች ደግሞ በሰላሳ ክፍሎች ተከፍሏል፡፡ እነዚህም ክፍሎች ጁዝዕ በመባል ይታወቃሉ፡፡ 79 የሚያህሉ ምዕራፎች በመክፈቻቸው ላይ በሚገኙ ቃላት የተሰየሙ ሲሆን 35 የሚሆኑት ደግሞ በውስጣቸው በሚገኙ ቃላት ተሰይመዋል፡፡ የምዕራፎቹን አቀማመጥ ስንመለከት የጊዜ ቅደም ተከተላቸው (chronological sequence) ሳይጠበቅ በአብዛኘኛው ከረጅሙ ወደ አጭሩ ምዕራፍ ተደርድረው እናገኛቸዋለን፡፡ ከመጀመሪያው አልፈቲሃ (የመክፈቻይቱ ምዕራፍ) ውጪ ያሉት ምዕራፎች ሁሉ አቀማመጣቸው በዚሁ መልኩ ይመስላል፡፡ በዚህም መሠረት ረጅሙ ምዕራፍ ሱራ አልበቀራ (የላም ምዕራፍ) ከአል-ፈቲሃ ቀጥሎ የሚገኝ ሲሆን አጭሩ ምዕራፍ ሱራ አል-ናስ ደግሞ የመጽሐፉ መጨረሻ ላይ ይገኛል ማለት ነው፡፡ (የአማርኛ ቁርኣን መቅድም ይመልከቱ።)
ቁርኣንን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚያነቡ ሰዎች ግርምትን ሊፈጥሩባቸው ከሚችሉ ይዘቶቹ መካከል የምዕራፎቹ ስያሜዎች የመጀመሪያዎቹ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በተለያዩ ነቢያትና ቦታዎች ስም የተሰየሙ ምዕራፎች በውሰጡ ቢገኙም ነገር ግን የአንዳንዶቹ ምዕራፎች ስያሜዎች መጽሐፉ እውን የፈጣሪ ቃል ነውን? ያስብላሉ፡፡ የመጽሐፋቸውን ህፀፅ በማሳየት የሙስሊም ወዳጆቻችንን ስሜት የመጉዳት አላማ የለንም፡፡ በመሆኑም የሚከተሉት ስያሜዎች እንደ ፈጣሪ ቃል ለሚታሰብ መጽሐፍ የሚመጥኑና ተገቢዎች እንደሆኑ ሙስሊም ወዳጆቻችን ያመኑበትን ምክንያት ለማወቅ መፈለጋችን እንደ ክፋት እንዳይታሰብብን በፍፁም ቅንነት እጠንቃለን፡፡
-
ሱረቱ አልበቀራ – የላም ምዕራፍ
-
አል አንዓም -የቤት እንስሳዎች ምዕራፍ
-
አል ካህፍ – የዋሻው ምዕራፍ
-
አል ነህል – የንብ ምዕራፍ
-
አል ነምል – የጉንዳን ምዕራፍ
-
አል አንከቡት – የሸረሪት ምዕራፍ
-
አል ዡኽሩፍ – የጌጣጌጥ ምዕራፍ
-
አል ዱሃን – የጭስ ምዕራፍ
-
አል አህቃፍ – የአሸዋዎች ምዕራፍ
-
አል ነጅም – የኮከብ ምዕራፍ
-
አል ቀመር – የጨረቃ ምዕራፍ
-
አል ሐዲድ – የብረት ምዕራፍ
-
አል ሙናፊቁን – የመናፍቃን ምዕራፍ
-
አል ተገቡን – የመጎዳዳት ምዕራፍ
-
አል መእርጅ – የመሰላሎች ምዕራፍ
-
አል አበሰ – የማጨፍገግ ምዕራፍ
-
አል ተክዊር – የመጠቅለል ምዕራፍ
-
አል ኢፊጣር – የመሰንጠቅ ምዕራፍ
-
አል ኢንሺቃቅ – የመቀደድ ምዕራፍ
-
አል ሙጠፊፊን – የሰላቢዎች ምዕራፍ
-
አል ቲን – የበለስ ምዕራፍ
-
አል አለቅ – የረጋ ደም ምዕራፍ
-
አል ማኡን – የዕቃ ትውስትምዕራፍ
-
አል ካፊሩን – የከሃዲች ምዕራፍ
-
አል ሸምስ – የፀሐይ ምዕራፍ
-
አል ለይል – የሌሊት ምዕራፍ
-
አል ዘልዘላህ – የምድር መንቀጥቀጥ ምዕራፍ
-
አል ቃሪኣህ – የቆርቋሪቱ ምዕራፍ
-
አል ሁምዛህ – የአሚተኛ ምዕራፍ
-
አል ፊል – የዝሆን ምዕራፍ
-
አል ጂን – የጋኔን ምዕራፍ
በእርግጥም እነዚህ ስያሜዎች ለፈጣሪ ቃል የሚመጥኑና ተገቢዎች መሆናቸውን ሊያስረዳን የሚችል ሙስሊም ይገኝ ይሆን?
ቅዱስ ቁርኣን