ነቢዩ ሙሐመድና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ – እውነተኛው የእግዚአብሔር አገልጋይ ማን ነው?

ነቢዩ ሙሐመድና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ 

እውነተኛው የእግዚአብሔር አገልጋይ ማን ነው?

ሙስሊም ወገኖቻችን ከሚነቅፏቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ስብዕናዎች መካከል ሐዋርያው ጳውሎስ በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። የመጀመርያዎቹን የኢየሱስ ተከታዮች ትምህርት በማጣመም ክርስትናን የፈጠረ ሰው አስመስለው የሚስሉት ሲሆን ኢየሱስ ካስተማረው ትምህርት የተለየ ትምህርት ያስተማረ ሐሰተኛ ሐዋርያ ነው ይሉታል። ሙስሊም ወገኖች በሐዋርያው ጳውሎስ ላይ የከረሩ ትችቶችን መሰንዘራቸው ካለማወቅና ከአጉል ጥላቻ የመነጨ እንጂ በተጨባጭ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ ይልቁኑ ጥንታውያን ሙስሊሞች ሐዋርያው ጳውሎስ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታይ መሆኑን መመስከራቸውን መስማት ለዘመናችን ሙስሊሞች በእጅጉ አስደንጋጭ ነው።

ኢብን ኢስሐቅ የተሰኘው ቀዳሚውን የሙሐመድ ግለ ታሪክ የከተበ ሙስሊም እንዲህ ሲል ጽፏል፡-

“ዒሳ የመርየም ልጅ የላካቸው ደቀ መዛሙርትና ከእነርሱ በኋላ የመጡት በአገሪቱ ውስጥ የነበሩት እነዚህ ነበሩ፡- ደቀ መዝሙሩ ጴጥሮስና ከእርሱ ጋር ደግሞ ጳውሎስ ወደ ሮም ተላኩ፡፡ (ጳውሎስ ከተከታዮቹ መካከል ሲሆን ደቀ መዝሙር አልነበረም፡፡) እንድርያስና ማቴዎስ ወደ በላዔ-ሰብዕ ምድር፤ ቶማስ በምስራቅ ወደሚገኘው ወደ ባቤል ምድር፤ ፊልጶስ ወደ ካርቴጅና ወደ አፍሪካ፤ ዮሐንስ የዋሻዎቹ ወጣቶች ምድር ወደሆነው ወደ ኤፌሶን…” (Alfred Guillaume. The Life of Muhammad: a Translation of Ibn Ishaq’s Sirat Rasul Allah, p. 653)

የኢብን ኢስሐቅ ጽሑፍ ሳሂህ አል-ቡኻሪና ሳሂህ ሙስሊምን ከመሳሰሉት ሐዲሳት እንኳ የሚቀድም የሙሐመድ ግለ ታሪክ ነው፡፡ በቅንፍ የተቀመጠው ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ጊዜ ደቀ መዝሙር እንዳልነበረ በትክክል የሚገልፅ በመሆኑ ስህተት የለበትም፡፡

የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ሐዋርያው ጳውሎስ የጻፈውን ከጠቀሰ በኋላ የአላህ ቃል መሆኑን መስክሯል፦

“ነገር ግን፦ ዓይን ያላየችው ጆሮም ያልሰማው በሰውም ልብ ያልታሰበው እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው ተብሎ እንደተጻፈ፥ እንዲህ እንናገራለን” (1ቆሮንቶስ 2፡9)፡፡

ከላይ የተጠቀሰው ሐዋርያው ጳውሎስ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የተጠቀሱትን የእግዚአብሔርን ተስፋዎች በራሱ አባባል ጨምቆ ያስቀመጠበት ዓረፍተነገር ሲሆን ከእርሱ በሚቀድም በየትኛውም ምንጭ ውስጥ በዚህ መልኩ ተጽፎ አይገኝም፡፡ ሙሐመድ እንዲህ ጠቅሶታል፡-

“አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፈው ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹አላህ እንዲህ አለ ‹እኔ ለታማኝ ባርያዎቼ ዓይን ያላየችውን፣ ጆሮ ያልሰማውን የሰው ልብ ሊያስበው የማይችለውን (አስደናቂ ነገሮች)› አዘጋጅቻለሁ፡፡››” (Sahih Al-Bukhari, Vol. 9, Book 93, Number 589)

የዘመናችን ሙስሊሞች ከነቢያቸው በላይ አዋቂ ከሆኑ ይንገሩን፡፡

ለማንኛውም ከሐዋርያው ጳውሎስና ከሙሐመድ እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልጋይ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ማን ነው? የሚል ጥያቄ ቢነሳ ጉዳዩ ሌላ ነው። ሙሐመድ ምንም ዓይነት የእውነተኛ ነቢይነት ምልክት ያልታየበትና እንዲያውም በተጻራሪው ከእግዚአብሔር ያልተላከ ሰው መሆኑን የሚያሳዩ ብዙ አስደንጋጭ ተግባራትን የፈጸመ ሲሆን ሐዋርያው ጳውሎስ ግን ከአንድ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሚጠበቁ መልካም ፍሬዎችን አፍርቷል። በሰንጠረዥ የተቀመጠውን ንፅፅር ይመልከቱ፦

ነቢዩ ሙሐመድና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ – ንፅፅር

ነቢዩ ሙሐመድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ
ነቢይነቱን ካወጀ በኋላ ነፍሰ ገዳይ ሆኗል፣ ነፍሰ ገዳይነትንም አስተምሯል ሱራ 4፡89፣ 5፡33፣ 33፡26፣ Sahih Muslim, 6985 የክርስቶስ ተከታይ ከሆነ በኋላ ስለ ቀድሞ ጥፋቱ ንስሐ ገብቷል 1ጢሞቴዎስ 1፡13-16
መድብለ ጋብቻን ፈፅሟል፣ የአክስትና የአጎት ልጆቹን አግብቷል (ሱራ 33፡50-52)፣ በአንድ ሌሊት ከ 9 ሴቶች ጋር ተኝቷል (Sahih al-Bukhari Vol. 7, Bk 62, No. 5)፣ እንዲሁም የ 6 ዓመት ህፃን አጭቶ በ 9 ዓመቷ አግብቷታል (Sahih al-Bukhari, Vol. 5 No. 234; Vol. 7 No. 65) ለወንጌል አገልግሎት ሲል ከጋብቻ ታቅቦ ኖሯል (1ቆሮ. 7፡8)፣ የአንድ ለአንድ ጋብቻን አስተምሯል (1ጢሞ. 3፡2፣ 3፡12፣ ቲቶ 1፡6)
ሚስቶችን መምታት ፈቅዷል ሱራ 4፡34 ባል ሚስቱን እንደ ገዛ ሥጋው እንዲንከባከብ አስተምሯል ኤፌ. 5፡25-33
ባል ሚስቱን እንደ ግል እርሻው በመቁጠር እንዲደርስባት አስተምሯል ሱራ 2፡223፣ Sunan Abu Dawud Bk. 11, No. 2159 ባልና ሚስት አንዳቸው በሌላቸው አካል ላይ እኩል ሥልጣን እንዳላቸው አስተምሯል 1ቆሮ. 7፡1-5
ወንዶች ከሴቶች እንደሚበልጡ አስተምሯል ሱራ 2፡228፣ 4፡34 (ይህ ብልጫ የሥልጣን ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ጭምር ነው Tafsir Ibn Kathir Part 2, Abridge by Sheikh Muhammad Nasib, 1998, P. 204) ወንዶችና ሴቶች እኩል እንደሆኑ አስተምሯል ገላቲያ 3፡28
አጋንንት ነበረበት Sahih al-Bukhari Vol. 4, Bk 53, No. 400; Bk 54, No. 490, Bk 71, No. 658, Sahih Muslim 39:6757 ሰዎችን ከአጋንንት ነፃ አውጥቷል ሐዋ. 16፡16-18፣ 19፡11-16
አንድም ተዓምር አላደረገም ሱራ 2፡118፣ 6፡37፣ 6፡109፣ 10፡20፣ 13፡7፣ 13፡27፣ 17፡59፣ 17፡90-93፣ 28፡48፣ 29፡49-51 ብዙ ተዓምራትን አድርጓል ሐዋ. 14፡3፣ ሮሜ 15፡18-19፣ 2ቆሮ. 12፡11-12
በቀልና ጥላቻን አስተምሯል ሱራ 2፡191-193፣ 8፡12፣ 8፡67፣ 8፡65፣ 9፡5፣ 9፡14፣ 9፡29፣ 9፡73፣ 9፡123፣ 48፡29፣ 58፡22 ሰዎችን ሁሉ ስለመውደድና አብሮ በሰላም ስለመኖር አስተምሯል ሮሜ 12፡18-19፣ 1ቆሮ. 13፡1-8
ዘራፊ ነበር ሱራ 8፡1 በገዛ እጆቹ እየሰራ ሌሎችን ይረዳ ነበር ሐዋ 18፡3፣ 20፡34፣
ለገዛ ጥቅሙ መገለጦችን ይናገር ነበር ሱራ 33፡50-51፣ 33፡37፣ 33፡53 ስለ ወንጌል ሲል ጥቅሙን አሳልፎ በመስጠት ብዙ መከራዎችን አሳልፏል 2ቆሮ. 11፡24-33
ውሸትን ፈቅዷል ሱራ 16፡106 ውሸታሞችን ተቃውሟል ቆላስይስ 3፡5-10፣ 2ቆሮ. 11፡13-15
ቅዱሳት መጻሕፍትን የማያውቅ መሐይም ነበር ሱራ 29፡48፣ 7፡158 ቅዱሳት መጻሕፍትን ጠንቅቆ የተማረ ሕግ አዋቂ ነበር ሐዋ. 22:3
የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን የሚጠላ ሰው ነበር (ሱራ 5:60፣ 2፡65-66፣ 9፡29፣ Sahih Muslim, 698; SiIbn Ishaq, P. 464) የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆኑትን እስራኤላውያንን የሚወድ እስራኤላዊ ነበር ሮሜ 9፡1-5
መርዝ በልቶ ሞቷል (Sahih al-Bukhari Vol. 3, Bk 47, No. 786; Vol. 5, Bk 59, No. 713) የእባብ መርዝ በእርሱ ላይ ሊሰራ አልቻለም ሐዋ. 28፡3-9

 

የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ከእግዚአብሔር ያልተላከ ሐሰተኛ ነቢይ ሲሆን ሐዋርያው ጳውሎስ ግን  በቅድስና በመኖርና በትህትናና በፍቅር በማገልገል በትምሕርቱም ሆነ በኑሮው ክርስቶስን መግለጥ የቻለ እውነተኛ የእግዚአብሔር ሰው ነው። ሙሐመድ ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር ለንፅፅር ለመቅረብ እንኳ የሚበቃ አይደለም።

ሙሐመድ