ምስክርነቶች


PATREON ላይ ተመዝግበው ይህንን አገልግሎት ይደግፉ!


ከእስልምና ወደ ክርስትና ፈታኝ ጉዞ (ዶ/ር ማርክ ገብርኤል)

ማርክ ገብርኤል (ሙስጠፋ) በአል-አዝሃር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የእስልምና ታሪክ ፕሮፌሰር የነበሩ ሲሆን የብዙ ተወዳጅ መጻሕፍት ደራሲ ናቸው፡፡ አስደናቂውን ምስክርነታቸውን ያንብቡ…

አስደናቂ ፍቅር : የሙቲዓ አል-ፋዲ ምስክርነት

እኔ የቀድሞ ወሃቢ ሙስሊም ስኾን ተወልጄ ያደግሁት በሳዑዲ አረብያ በሚኖር ሙስሊም ቤተሰብ ውስጥ ነበር፡፡ ለሃይማኖቴ ያደርኩና እያንዳንዱን የእስልምና አስተምሕሮ በያንዳንዱ የሕይወቴ ገፅታ ላይ ለመተግበር የምተጋ ፅኑ ሙስሊም ነበርኩ፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…

እውነተኛውን አዳኜን አወቅሁት! ባለታሪኩ፡– ወንድም ሰዒድ

ሰዒድ እባላለሁ፡፡ ተወልጄ ያደግሁት በአርሲ ዞን ውስጥ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ውስጥ ነው፡፡ ቤተሰቦቼ የባሕላዊ እስልምና እምነት ተከታዮች ሲሆኑ የኔም አስተዳደግ በዚሁ መልኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ራሴን ወደማወቅ እድሜ ስደርስ ቁርኣንን በመቅራትና ሌሎች የእስልምና ትምህርቶችን  በመማር ጠንካራ ሙስሊም ለመሆን ከፍተኛ ጥረት አድርጌአለሁ፡፡ እንደኔ ሙስሊም የነበረው ታላቅ ወንድሜ ለሥራ ጉዳይ ራቅ ወዳለ ስፍራ ከሄደ በኋላ የክርስትናን እምነት ተቀብሎ ተመለሰ፡፡ ቤት ውስጥ አብረን በምንሆንበት ሰዓት ስለመሲሁ ስለ ኢየሱስና ስለመጽሐፍ ቅዱስ ሲነግረን አንድ ሌላ ወንድሜ ብዙም ተቃውሞ ሳያቀርብ ይሰማው የነበረ ሲሆን እኔ ግን አጥብቄ እቃወመው ነበር፤ ሐሳቡንም ላለማስተናገድ ቆራጥ አቋም ያዝኩኝ፡፡ ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…

የመናዊው አቡ አል-ፈት፤ የጨለማው ዘመን ሻማ

አባ ዕንባቆም (የልደት ስማቸው አቡ አል-ፈት) በ1489 ዓ.ም እ.ጎ.አ ወደ ኢትዮጵያ የመጡ የመናዊ ሙስሊም ነጋዴ የነበሩ ሲሆን እስላማዊ መጻሕፍትን ለብዙ ዘመናት ካጠኑ በኋላ ክርስትናን የተቀበሉ ሰው ነበሩ። ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…

ሼኽ ዘከርያህ – ኢትዮጵያዊው የወንጌል አርበኛ

ሼኽ ዘከርያህ (1845-1920 ዓ.ም) ካዩዋቸው ተከታታይ ራዕዮች የተነሳ ወደ ክርስትና የገቡ የቀድሞ ሙስሊም ነበሩ። ሼኽ ዘከርያህ በ1845 በበጌምድር ክፍለ ሀገር ናጋላ አካባቢ እንደተወለዱ የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል። ወላጆቻቸው የአማራ ሙስሊሞች ሲሆኑ በመጠነኛ ንግድ ይተዳደሩ ነበር። ሼኽ ዘከርያህ በወሎ ክፍለ ሀገር ገና በለጋ እድሜያቸው የቁርኣንን ትምህርት ተምረዋል። ሙሉ ጽሑፉን ያንብቡ…