ማንነታችን

የኛ ማንነትና ዓላማ

ወደዚህ ገፅ እንኳን በደህና መጡ!


PATREON ላይ ተመዝግበው ይህንን አገልግሎት ይደግፉ!


“እውነት ለሁሉ” በዓለም ዙርያ በሚገኙ በጎ ፈቃደኛ ክርስቲያኖች የተመሠረተ ድረ-ገፅ ሲሆን እስልምናንና ክርስትናን የተመለከቱ መጣጥፎችን፣ መጻሕፍትን፣ ዜናዎችንና የመሳሰሉትን ያስነብባል፡፡ የኦዲዮና የቪድዮ መረጃዎችንም ያቀርባል፡፡

ድረ-ገፁን ለመመሥረት መነሻ ምክንያቶች

  • ውጪያዊ ምክንያቶች
  1. ዓለም አቀፍ እስላማዊ ኃይላት ዐይኖቻቸውን ኢትዮጵያ ላይ በማድረግ ከፍተኛ የኾነ የማስለም ዘመቻ መክፈታቸው፡፡
  2. በድምፅ፣ በምስልና በጽሑፍ የመገናኛ አውታሮች በመጠቀም ክርስትናን የማብጠልጠል ዘመቻ በአክራሪ ሙስሊሞች አማካይነት እየተካሄደ መኾኑ፡፡
  3. ክርስትናን የሚተቹ እስላማዊ ድረ-ገፆች፣ ጦማሮችና የማሕበራዊ ድረ-ገፆች ቡድኖች መበራከታቸው፡፡
  4. የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች በፖለቲካ፣ ኢኮኖሚና ማሕበራዊ ጉዳዮች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሽመድመድ በውጪና በአገር ውስጥ እስላማውያን ኃይላት ዘመቻ እየተደረገ መኾኑ፡፡
  5. በአንፃራዊነት ሰላማዊ ሊባል የሚችለው ባሕላዊው እስልምና ተሸርሽሮ በሕዝቦች ሰላምና አብሮ መኖር በማያምን አክራሪ እስልምና እየተተካ መምጣቱ፡፡
  6. በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አክራሪ ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን በማስፈራራትና የሽብር ጥቃቶችን በመፈፀም የወንጌልን ሥራ ለማስተጓጎል ጥረት እያደረጉ መኾናቸው፡፡
  • ውስጣዊ ምክንያቶች
  1. አማኞች ወንጌልን የማዳረስ ሥራ የጥቂት ግለሰቦችና የአገልግሎት ዘርፎች ኃላፊነት እንደኾነ በመቁጠር ከጌታ የተቀበሉትን አደራ መዘንጋታቸው፡፡
  2. ክርስቲያን ምሑራን እስልምናን በተመለከተ እየሠሩ ያሉት ዓቃቤ እምነታዊ ሥራ በእጅጉ አናሳ መኾኑ፡፡
  3. ብዙ ክርስቲያኖች ከእስልምና ወገን የሚነሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ያላቸው ዝግጅት አናሳ መኾኑ፡፡
  4. ክርስቲያን ሚድያዎች በሙስሊሞች ላይ ያተኮረ ስብከተ ወንጌል አለማድረጋቸው፡፡

የድረ-ገፁ አጠቃላይ ዓላማ

የዚህ ድረ-ገፅ አጠቃላይ ዓላማ “ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” በሚለው የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ መሠረት ወንጌልን በፍቅር ለሙስሊሞች ማድረስና ክርስቲያን ወገኖች እስላማዊ ጥያቄዎችን መመለስ እንዲችሉና ወንጌልን ለሙስሊም ባልንጀሮቻቸው በተሳካ ሁኔታ ማድረስ እንዲችሉ ማስታጠቅ ነው፡፡

የድረ-ገፁ ዝርዝር ዓላማዎች

  1. ለሙስሊም ወገኖች በሚገባቸው ንግግርና አቀራረብ ወንጌልን ማድረስ፡፡
  2. የሙስሊሞችን የተለመዱ ጥያቄዎች መመለስ፡፡
  3. በክርስትና ላይ ለሚሰነዘሩት እስላማዊ ትችቶች ተገቢውን ምላሽ መስጠት፡፡
  4. የእስልምናን መሠረታዊ አስተምህሮዎች ጥልቅ በኾነ መንገድ መመርመር፡፡
  5. ጥላቻንና አለመተማመንን በማስወገድ ለጋራ መረዳት በክርስቲያኖችና በሙስሊሞች መካከል ድልድይን መሥራት፡፡

የእምነት አቋማችን

  1. መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት እውነተኛና ያልተለወጠ ቃለ እግዚአብሔር መኾኑን፣ ለክርስቲያናዊ አስተምህሮዎች ብቸኛ ምንጭና የበላይ መኾኑን እናምናለን፡፡
  2. በእግዚአብሔር ሥሉስ አሓዳዊነት እናምናለን፡፡ ይህም የመጀመርያውን የኒቅያ ጉባኤ ጨምሮ አበይት በኾኑት የቤተ ክርስቲያን ጉባኤዎች እንዲሁም ቅዱስ አትናቴዎስን በመሳሰሉት አበው በተብራራው መሠረት ነው፡፡
  3. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠ አምላክ መኾኑን፣ ከድንግል መወለዱን፣ መለኮታዊ ባሕርዩ ሳይለወጥ ኃጢአት የሌለበት ፍፁም ሰው ኾኖ በምድር ላይ መኖሩን፣ መለኮታዊ ተዓምራትን ማድረጉን፣ የሰው ልጆችን ኃጢአት ለማስተሠረይ ሲል በመስቀል ላይ መሞቱን፣ በሦስተኛው ቀን በሥጋ ከሙታን መነሣቱን፣ ወደ ሰማይ ማረጉን፣ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ መኾኑን፣ በሕያዋንና በሙታን ለመፍረድ በክብር ዳግመኛ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡
  4. የዘለዓለም ሕይወት የሚገኘው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን መሞቱንና ከሙታን መነሳቱን አምኖ በመቀበል የሰው ሥራ ባልታከለበት  የእግዚአብሔር ጸጋ (ነፃ ስጦታ) መኾኑን እናምናለን፡፡
  5. መንፈስ ቅዱስ ሦስተኛው የሥላሴ አካል መኾኑን፣ ከአብና ከወልድ የተካከለ መለኮት መኾኑን፣ በአማኞች ውስጥ በመኖር መልካሙን ሥራ ይሠሩ፣ ይቀደሱና ለክርስቶስ ይመሰክሩ ዘንድ ኃይልን እንደሚሰጣቸው እናምናለን፡፡
  6. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ ሙታን ኹሉ እንደሚነሱና የዳኑት ወደ ዘለዓለም ሕይወት እንደሚኼዱ፣ ያልዳኑት ደግሞ ወደ ዘለዓለም ጥፋት እንደሚኼዱ እናምናለን፡፡
  7. ሦስቱ አበይት የክርስትና ቅርንጫፎች (ካቶሊክ፣ ኦርቶዶክስና ፕሮቴስታንት) የሚስማሙባቸውን ነጥቦች ማዕከል በማድረግ እንጽፋለን እንናገራለን፤ ነገር ግን በእምነት አቋማችን ወንጌላውያን ክርስቲያኖች ነን።

እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ!

ewnet4hulu@gmail.com

ከኛ ጋር በአገልግሎቱ መሳተፍ ይሻሉን? እዚህ ጋ ጠቅ በማድረግ መረጃዎችን ያግኙ። 

About the Website

“እውነት ለሁሉ” (Truth for All) website is established by Ethiopian Christians. We provide our visitors with articles, news, books, audio, and video resources in Amharic and other Ethiopian languages concerning Christianity and Islam. The English section of our website is aimed to inform our international visitors about Islam and Christianity in Ethiopia. Our exhaustive discussions of topics related to Christianity and Islam are available in Ethiopian languages.

1. What Prompted Us

1.1. External Influences:-

  • Global Islamic forces are mobilizing huge resources to Islamize Ethiopia.
  • Radial Muslims are assaulting fundamental Christian doctrines by using different mediums of communication. Islamic polemicists’ writings, VCDs, and CDs on the authority of the bible and Christianity are rampant in the country.
  • These polemical materials are disseminated over the Internet. There are many Islamic Pal talk rooms, websites, enumerable blogs, YouTube channels, and other social media groups. Many Ethiopian Christians, especially those living in Arab Countries are converting to Islam because of these materials.
  • Global Islamic forces are working vigorously to cripple Ethiopian Christians politically, economically and socially. The part Christians play in politics, business, and in the shaping of the overall social fabric is dwindling from time to time.
  • The relatively peaceful form of Islam (Sufi Islam) is on radicalization at an alarming pace as the outcome of the Global Islamic revival.
  • As a result of this radicalization process, many Christians are being victimized by fanatical groups.
  • The government is submitting to virtually every demand of Islam.

1.2. Internal Problems:-

  • The task of the Great Commission is being relegated to quite a few people and ministries.
  • There are no adequate rebuttals and apologetic works from Ethiopian Christians.
  • Christians are ill-equipped to answer issues Muslims raise on Christianity and the Bible.
  • Christian Media are not paying attention to Muslim Evangelism.

2. Objectives

2.1. General Objective

The general objective of this website is to reach Muslims with the Gospel of Jesus Christ and equip Christians to fulfill the Great Commission by reaching their Muslim neighbors with the love of Christ.

2.2. Specific Objectives of the Website

  • Reaching our Ethiopian Muslim friends with the Gospel of Jesus Christ.
  • Answering Common Questions of Muslims.
  • Answering objections against Christianity (polemics rebuttals).
  • Critical evaluations of fundamental Islamic doctrines.
  • Building a bridge between Christians and Muslims for Mutual understanding.

3. Materials on the Website

Visitors can find the following types of materials on the website for free:-

  • Articles
  • E-books
  • Video and audio recordings

4. Languages of the Website

  • Amharic – is the main language of the website. Materials in Amharic will be the basis for materials in other languages on the website
  • Afan Oromo – is the mother tongue of over 35,000,000 Ethiopians. Nearly half of the Oromos in Ethiopia are adherents of Islam. The Islamization process in Ethiopia is mainly focused on Oromo people; hence it is very important to have this section on our website.
  • English – In this section of the website we will put information and news about Islam and Christianity in Ethiopia for the benefit of our international visitors. Since there are many English websites dealing with Islam we don’t need to reinvent the wheel. For those who are interested in studying topics related to Christianity and Islam, we recommend the Answering Islam website.
  • Tigrigna – is the mother tongue of over 10,000,000 Ethiopians and Eritreans. 

5. Why the Website?

  • Internet is becoming part and parcel of the daily activity of millions of Ethiopians.
  • Launching a website will enable us to counter Islamic websites, Equip Christians in apologetics, and Evangelize Muslims.
  • It is cost-effective.
  • It is secure (we can reach the Muslims without compromising our security).
  • We can reach the maximum number of urban Muslims and Christians.

Contact us at: ewnet4hulu@gmail.com

May God Bless you!