ክርስትና መለኮታዊ ሃይማኖት ነው!
እስልምናስ?
የመጽሐፍ ሒስና ግምገማ – ክፍል 3
ርዕስ – ንቁ! ክርስትና መለኮታዊ ሃይማኖት ነውን?
ደራሲ – ሰልማን ኮከብ
የታተመበት ዘመን – 2010
አሳታሚ – አልተገለፀም
የገፅ ብዛት – 270
ደራሲው “ጥራዝ ነጠቅ ተባልኩ” “ተሰደብኩ” የሚል ስሞታ እያቀረበ መሆኑን ሰምቻለሁ፡፡ አንዳንድ የእርሱ ቢጤዎችም አብረውት ሙሾ እያወረዱ እንደሆነ መረጃ ደርሶኛል፡፡ ምናልባትም የተወሰኑቱ በመጽሐፉ አርትዖት በመሳተፋቸው የእርሱ እንዲህ መጋለጥ የእነርሱንም ስብዕና ይዞ መቀመቅ እንደሚወርድ ሲያስቡት ድንጋጤ ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ በዚህ መጠን ስሜቱን ባልጎዳው ምንኛ ደስ ባለኝ፡፡ ከዚህ ቀደም ለአሕመዲን ጀበልና ለሐሰን ታጁ የሰጠኋቸውን ምላሾች ያነበበ ሰው በዚህኛው ደራሲ ላይ እንዲህ ጠንከር የማለቴ ጉዳይ ጥያቄ ሊፈጥርበት ይችላል፡፡ እነርሱም ቢሆኑ በክርስትና ላይ የጻፏቸው የትችት መጻሕፍት ከዚህኛው ባልተናነሰ ሁኔታ ገለባ ቢሆኑም ግለሰቦቹ ግን ቢያንስ የወረቀት መጻሕፍትን አገላብጠዋል፤ ጥረት በታከለበት መንገድም በገዛ ማሕበረሰባቸው ውስጥ ዕውቅናን ለማትረፍ ችለዋል፡፡ ስለ ክርስትና ቢጽፉም ባይጽፉም በገዛ ሃይማኖታቸው ክበብ ቀደም ሲል ታውቀዋል፡፡ ነገር ግን ይኸኛው አብዱል ከኢንተርኔት ላይ የለቃቀመውን ያልተጣራ መረጃ ከገዛ ምናቡ ካፈለቃቸው ፅርፈታት ጋር በመቀየጥ በመጽሐፍ በማሳተም የምንወደውንና የምናከብረውን፣ የክርስቶስንም ብርሃን እንዲያይ የምንናፍቅለትን ሕዝበ ሙስሊሙን የኮተት ማራገፍያ አድርጓል፡፡ ክርስቲያን እንደነበርና እንደሰለመ መናገሩ ደግሞ “ክርስቲያን ነበርኩ” ያለውን ሁሉ የሃይማኖት ሊቅ አድርጎ የማሰብ አባዜ ባላቸው የዋኃን ሙስሊሞች ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኝ አድርጎታል፡፡ ቅጥፈት የሙስሊም ጸሐፊያን ሁሉ አመል ቢሆንም የዚህኛው ግን ፍፁም ያልተለመደ ነው፡፡ ለሰንበት ትምሕርት ቤት ህፃናት እንኳ ግልፅ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ስህተቶችን ሲፈፅም ይታያል፡፡ እውነቱን ለመናገር ከዳር እስከዳር በመጽሐፉ ውስጥ ስህተት የሌለባቸው ዓረፍተ ነገሮች በቁጥር ናቸው፡፡ እንዲህ ያሉ ግለሰቦችን በሚመጥናቸው ቋንቋ ማናገር ተገቢ ይመስለኛል፡፡ ተመሳሳይ የፕሮፓጋንዳ መጻሕፍትን ለመጻፍና ክርስትናን ለመወረፍ የሚያስቡ ሌሎች አብዱሎችም በተመሳሳይ መንገድ ስለምናጋልጣቸው መሰል የማምታታት ሥራ ዋጋን እንደሚያስከፍላቸው አውቀው እንዲጠነቀቁ ለማሳሰብም ነው፡፡ ይህንን ካልን ዘንዳ ግምገማችንን እንቀጥላለን፡፡ ያለፈውን ክፍል ያላነበባችሁ ወገኖች እዚህ ጋ በመንካት ታነቡ ዘንድ እናበረታታችኋለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ከደራሲው መጽሐፍ በተወሰዱ ቀጥተኛ ጥቅሶች ውስጥ የሚገኙት የፊደልና ሌሎች ግድፈቶች የደራሲው እንጂ የእኔ አይደሉም፡፡ በኢታሊክስ የፊደል አጣጣል ያስቀመጥኩት እኔ ነኝ፡፡
መጽሐፈ መሣፍንት
እንደተለመደው ጸሐፊው ገና በመጀመርያው ዓረፍተ ነገር ስህተት ይሠራል፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“መጽሐፈ መሳፍንት ከመጽሐፈ ኢያሱ ቀጥሎ የምናገኘው ሰባተኛው መጽሐፍ ሲሆን ከኢያሱ በኋላ በእስራኤል ላይ ስለነገሱት 15 መሳፍንታት (ጎቶንያል፣ ናዖድ፣ ሰሜጋር፣ ዲቦራ፣ ጌዴዎን፣ አቤሜሌክ…) ይነግረናል፡፡” (ገፅ 19)
በመጽሐፈ መሣፍንት ውስጥ የተጠቀሱት መሣፍንት ቁጥር 13 እንጂ ደራሲው እንዳለው 15 አይደሉም፡፡ እንዲያውም አቤሜሌክ ክፉ መስፍን በመሆኑ ብዙ ወገኖች እርሱን በመቀነስ ቁጥራቸውን 12 ያደርጋሉ፡፡ ዝርዝራቸው እነሆ፡-
ታላላቅ መሣፍንት | ታናናሽ መሳፍንት |
1. ጎቶንያል (8፡7-11) 2. ናዖድ (3፡12-13) 3. ዲቦራ 4. ጌዴዎን (6-8) 5. አቤሜሌክ (9) 6. ዮፍታሔ (10፡6-12) 7. ሳምሶን (13-16) | 8. ሰሜጋር (3፡31) 9. ቶላ (10፡1-2) 10. ኢያዕር (10፡3-5) 11. ኢብዳን (12፡8-10) 12. ኤሎም (12፡11-12) 13. ዓብዶን (12፡13-15) |
ደራሲው መጽሐፉ ስለ 15 መሣፍንት መናገሩን ሲያትት በመጽሐፉ ውስጥ ያልተጠቀሱትን 2 ጨምሯል፡፡ በምዕራፉ መጀመርያ የጥንቃቄን አስፈላጊነት ሰብኮ መጀመሩን እናስታውስ!
ሊቃውንት የመሣፍንትን ደራሲ ማንነት በተመለከተ የሰጡት አስተያየት ነው በሚል ተከታዩን ጽፏል፡-
የ20ኛው ክ/ዘመን ተመራማሪዎች እንደደረሱበት ደግሞ መጽሐፉ ከክ.በ በ6ኛው መቶ ዓመት በባቢሎን ምርኮ ዘመን እንደተፃፈና በዘዳግም ፀሐፊዎች የተዘጋጀ ሊሆን እንደሚችል ይገልፃሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ቶማስ ሮሜር አንዱ ሲሆን መጽሐፈ መሳፍንት ከዘዳግም ከኢያሱና ከሳሙኤል መጽሐፍት ጋር የአፃፃፍ ስርዓቱ ተመሳሳይ መሆኑ የአንድ ሰው ስራ እንደሆኑ መገመት ይቻላል ብለዋል፡፡ Gary Neil Knoppers and Gordon McConville (2000), “Reconsidering Israel and Judah”, pp. 119 (ገፅ 20)
ደራሲው የጠቀሰው የተለያዩ ምሑራን ጽሑፎች የተሰባሰቡበትን መጽሐፍ ሲሆን በመጽሐፉ ውስጥ በቶማስ ሮሜር የተጻፈ፣ መሣፍንትን የተመለከተ ምንም ነገር የለም! ከመጽሐፈ መሣፍንት ጋር የተያያዙት ርዕሶች በሙሉ በሌሎች ምሑራን የተጻፉ በመሆናቸው እርሱ በጠቀሰው የመጽሐፉ ገፅ 119 ላይ ቶማስ ሮሜር መጽሐፈ መሣፍንትን ጠቅሶ ምንም ነገር አልተናገረም፡፡ በመጽሐፉ ከገፅ 112-138 ድረስ የሚገኘው በሮሜር የተጻፈ ርዕስ “Deuteronomy in Search of Origins” የሚል እንጂ መሣፍንትን የተመለከተ አይደለም፡፡[1] ደራሲው ይህንን ቅጥፈት መፈፀሙን ካላመናችሁ ከመጽሐፉ የወሰድኩትን ፎቶግራፍ እዚህ ጋ በመንካት ራሳችሁ ተመልከቱ! በመጽሐፉ ውስጥ ከተሳተፉት ጸሐፊያን መካከል መሣፍንትን ጠቅሰው የጻፉት Gordon J. Wenham (p. 194), John Van Seters (p. 204), J. Cherly Exum (p. 578) ናቸው፡፡ ደራሲው ያላነበበውን መጽሐፍ ነው የጠቀሰው፡፡ አወይ ቅሌት! እንዲህ እየቀጠፈ ነው እንግዲህ “ጥራዝ ነጠቅ አሉኝ” ብሎ የሚያለቃቅሰው!
በዚህ ዘመን የሚገኙት ለዘብተኛ ሊቃውንት ኦሪት ዘዳግም፣ መጽሐፈ ኢያሱ፣ መጽሐፈ መሣፍንት፣ መጽሐፈ ሳሙኤልና መጽሐፈ ነገሥት በአንድ ጸሐፊ እንደተዘጋጁ የሚናገሩ ሲሆን ይህ ትወራ Deuteronomistic History (ዘጸአታዊ ትራኬ) በመባል ይታወቃል፡፡ ጀማሪው ደግሞ ማርቲን ኖሥ የተሰኘ የጀርመን የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቅ ነው፡፡ ይህ ትወራ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በብዙ ሊቃውንት ዘንድ ተቀባይነትን አግኝቶ የቆየ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ከብዙ ሊቃውንት ዘንድ የከረረ ትችት እየቀረበበት እንደሚገኝና ተቀባይነቱ እያሽቆለቆለ መምጣቱን ደራሲው የጠቀሰው መጽሐፍ በመቅድሙ ላይ ይናገራል፡፡ እናንብበው፡-
Within the past decade an increasing number of scholars have called into question a number of central tenets and assumptions of the Deuteronomistic history hypothesis. For these scholars, the hypothesis itself, and not just particular aspects of it, needs to be completely revised or rejected altogether.[2]
ትርጉም፡- ባለፈው አሥርተ ዓመት ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ሊቃውንት የዘጸአታዊ ትራኬን ንድፈ ሐሳብ ቁልፍ ነጥቦችን አጠራጣሪ ሆነው አግኝተዋቸዋል፡፡ በነዚህ ሊቃውንት መሠረት የንድፈ ሐሳቡ የተወሰነ ገፅታ ብቻ ሳይሆን ንድፈ ሐሳቡ ራሱ ሙሉ በሙሉ መከለስ ወይንም ደግሞ ውድቅ መሆን ያስፈልገዋል፡፡
ይህ ሐሳብ ደራሲው በጠቀሰውና (አለማንበብ የነቢዩ ሱና በመሆኑ ምክንያት) ባላነበበው መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ እንግዲህ “በራስ ገመድ መታነቅ” የምንለው ነው!
ለዘብተኛ ሊቃውንት መጽሐፉ በምርኮ ዘመን እንደተጻፈ ቢናገሩም የመጽሐፉ ውስጣዊ ማስረጃ ግን በሳዖል ወይንም በዳዊት ዘመን በ1000 ዓ.ዓ. ገደማ እንደተጻፈ ያሳያል፤ ይህም የመጽሐፉ ደራሲ እንደሆነ በትውፊት ከተነገረው ከሳሙኤል ዘመን ጋር ይገጣጠማል፡-
“ነገር ግን በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን የብንያም ልጆች አላወጡአቸውም፤ ኢያቡሳውያንም ከብንያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢየሩሳሌም ተቀምጠዋል።” (መሣ. 1፡21)
የመሣፍንት ጸሐፊ መጽሐፉን በሚጽፍበት ወቅት ኢያቡሳውያን ከቢንያም ልጆች ጋር በኢየሩሳሌም ይኖሩ እንደነበር ይነግረናል፡፡ ይህም የሚያሳየው ዳዊት ወደ ከተማይቱ ከመግባቱ በፊት የነበረውን ዘመን ነው (2ሳሙ. 5፡6-10)፡፡ ስለዚህ በምርኮ ዘመን ተጻፈ የሚለው ግምት በመጽሐፉ ውስጣዊ ማስረጃ መሠረት ውድቅ ነው፡፡
መጽሐፉን ማን ጻፈው? ለሚለው ጥያቄ የአይሁድ ትውፊት ሳሙኤል ነው የሚል ምላሽ ይሰጣል፡፡ በቀደሙት ምላሾቻችን እንዳልነው የኛ የሥልጣን ምንጮች ጌታ ኢየሱስና ሐዋርያቱ በመሆናቸው እነርሱ የብሉይ ኪዳንን መጻሕፍት መለኮታዊ ምንጭነት ተቀብለው ስላስተማሩ እኛም እንቀበላለን፡፡ የጌታ ኢየሱስንና የሐዋርያቱን ሥልጣን ተለዋዋጭ በሆነው የለዘብተኛ ሊቃውንት መላምት የምንቀይርበት ምክንያት ፈፅሞ አይታየኝም፡፡
ግብረ ገባዊ ተቃውሞ
ደራሲው በመጽሐፈ ኢያሱ ላይ የሰነዘረውን ግብረ ገባዊ ትችት በመሣፍንትም ላይ ያቀርባል፡፡ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን አድልቷል የሚል ስሞታም ያሰማል (ገፅ 20-21)፡፡ ለዚህ ማስረጃ ይሆነው ዘንድ የጠቀሳቸው ጥቅሶች ደግሞ በጣም አስገራሚ ናቸው፡፡ አንድ በአንድ እንያቸው፡-
“ከከነዓናውያንም ጋር መዋጋት ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ፥ በፊትም ሰልፍን ያልለመዱ የእስራኤል ልጆች ትውልድ መዋጋትን ያውቁና ይማሩ ዘንድ እግዚአብሔር ያስቀራቸው አሕዛብ እነዚህ ናቸው፡፡” (መሣ. 3፡1-2)
ጥቅሱ 3፡1-2 ላይ የሚገኝ ቢሆንም ደራሲው 2፡1-3 ብሎ ጠቅሷል፡፡ ይህ ሊያጋጥም የሚችል ስህተት በመሆኑ በዚህ ልንወቅሰው አንሻም፡፡
በመጽሐፈ ኢያሱ ላይ ለቀረቡት ትችቶች መልስ ስንሰጥ እንዳልነው እነዚህ ሕዝቦች እግዚአብሔር ለክፍለ ዘመናት የታገሳቸው ነገር ግን ህፃናትን መሠዋት፣ ከቤተሰብ አባላትና ከእንስሳት ጋር ወሲብ መፈፀምን የመሳሰሉ ጸያፍ ተግባራትን ባሕል ያደረጉ መጥፋት የሚገባቸው ፍፁም ሰይጣናዊ ሥልጣኔዎች ነበሩ፡፡ ለእስራኤላውያን የጦር መለማመጃነት መቅረታቸው ከርኩሰታቸው አንፃር እንደ ምሕረት መታየት ያለበት እንጂ እንደ አድልዎ ሊታሰብ የሚገባው አይደለም፡፡
በማስከተል ይህንን ጥቅስ ጠቅሷል፡-
“የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ መቱአቸውም፤ እስራኤልም በዚያ ምድር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን ምድር ሁሉ ወረሰ።” (መሣ. 11፡21)
ከዚህ ጥቅስ ቀድመው የተጻፉትን ሁለት ጥቅሶች (ቁ. 19-20) ያነበብን እንደሆን የደራሲው አለማስተዋልና ችኩልነት ግልፅ ይሆንልናል፡-
እንዲህ ይላል፡-
“እስራኤልም ወደ አሞራዊው ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም፦ በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን፥ እባክህ፥ አሳልፈን አለው። ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ አላመነውም ነበር፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፥ በያሀጽም ሰፈረ፥ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፥ መቱአቸውም፤ እስራኤልም በዚያ ምድር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞራውያንን ምድር ሁሉ ወረሰ።” (መሣ. 11፡19-21)
ከጥቅሶቹ እንደምንረዳው እስራኤላውያን ሐሴቦንን የመጉዳት ዓላማ አልነበራቸውም፡፡ ነገር ግን በግዛቱ በኩል እንዲያሳልፋቸው ንጉሣቸው ሴዎንን ለመኑት እርሱ ግን አላሳልፍም አለ፤ ይባስ ብሎም ሕዝቡን ሁሉ ሰብስቦ ከባርነት አምልጦ በበረሃ ውስጥ አድካሚ ጉዞ እያደረገ በሚገኘው ምስኪን የእስራኤል ሕዝብ ላይ ጦርነትን ከፈተ፡፡ በምላሹም እስራኤላውያን መቱአቸው፤ ምድራቸውንም ወረሱ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ባለ እኩይ ንጉሥ ላይ ለሕዝቡ ድልን በመስጠቱ ሊከፋ የሚችለው እስራኤላውያንን በጭፍን የሚጠላ ዘረኛ ብቻ ነው!
ቀጥሎ ይህንን ጥቅስ ጠቅሷል፡፡ አሁንም ዓላማው እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን እንዳደላ ማረጋገጥ ነው፡-
“እግዚአብሔርም፦ በእርግጥ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ትመታለህ አለው።” (መሣ. 6፡16)
እግዚአብሔር ለምን ጌዴዎን ምድያምን እንዲመታ ኃይልን እንደሰጠው ቀደም ብለው ከሚገኙት ጥቅሶች እንረዳል፡-
“የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራራ ላይ ጕድጓድና ዋሻ ምሽግም አበጁ። እስራኤልም ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያን አማሌቃውያንም በምሥራቅም የሚኖሩ ሰዎች ይመጡባቸው ነበር፤ በእነርሱም ላይ ይሰፍሩ ነበር፥ እስከ ጋዛም ድረስ የምድሩን ቡቃያ ያጠፉ ነበር፥ ምግብንም ለእስራኤል አይተዉም ነበር፤ በግ ወይም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይተዉም። እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡ ነበር፤ ለእነርሱና ለግመሎቻቸውም ቍጥር አልነበራቸውም፤ ምድሪቱንም ያጠፉ ዘንድ ይመጡ ነበር። ከምድያምም የተነሣ እስራኤል እጅግ ተጠቁ፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።” (መሣ. 6፡1-6)
ሕዝቡ ክፉ ሥራ ሲሠራ እግዚአብሔር አሳልፎ ሰጠው፡፡ ተጨንቆ ንስሐ ሲገባ ደግሞ በጠላቶቹ ላይ ድልን ሰጠውና አሳረፈው፡፡ ይኸው ነው! ይህ አድልዎና ዘረኝነት ከተባለ እኔ ሳልሰማ የቃላት ትርጉም ተለውጧል ማለት ነው! የደራሲው ችግር እስልምና በአይሁድ ላይ በሚነዛው የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ልቡ መታወሩ ነው፡፡ የሆነው ሆኖ ይህ ወገናችን የቁርአን ደራሲ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሲኮርጅ የጌዴዎንን ታሪክ በስህተት የሳዖል ታሪክ በማስመሰል ማቅረቡን ያውቅ ይሆን? (ቁርአን 2፡249)
አንዲህ ሲል ትችቱን ይቋጫል፡-
“በነገራችን ላይ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አንዳንድ ሰዎች እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን ማድላቱ አምላክነቱን በመቀበላቸው ነው የሚል አስተያየት ቢሰጡም እንኳን በዚሁ በመጽሐፈ መሳፍንትና በሌሎችም መጽሐፍት ውስጥ እስራኤላውያን ለበርካታ ጊዜያት አምላክን ክደው ጣዖታትን እንዳመለኩ ተገልፆ እያለ ለእነሱ ብቻ ምህረት ማውረዱና ማድላቱ ጉዳዩ ከአምልኮ ጋር የተያያዘ ሳይሆን ዘረኛ አይሁዶች የፃፉት እንደሆነ መረዳት እንደሚቻል መጠቆም እወዳለሁ፡፡” (ገፅ 21)
ጠቁመህ ሞተሃል! አንድን መጽሐፍ በሰከነ መንፈስ አንብቦ ከመረዳት ይልቅ እንደ ፌንጣ ከገፅ ገፅ እየዘለሉ ማንበብ ችግሩ ይህ ነው፡፡ የመጽሐፈ መሣፍንት ዋና ዓላማ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በመተው አምልኮተ ጣዖታትን ሲለማመዱ እግዚአብሔር አምላክ እንዴት ሲቀጣቸው እንደነበርና በንስሐ ሲመለሱና መንገዳቸውን ሲያስተካክሉ ደግሞ እንዴት ምሕረትን አድርጎላቸው ሲምራቸው እንደነበር ማሳየት ነው፡-
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ የሆነ ነገር አደረጉ፥ በኣሊምንም አመለኩ። ከግብፅ ምድርም ያወጣቸውን የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ተዉ፥ በዙሪያቸውም ካሉት ከአሕዛብ አማልክት ሌሎችን አማልክት ተከተሉ፥ ሰገዱላቸውም፤ እግዚአብሔርንም አስቈጡ። እግዚአብሔርንም ትተው በኣልንና አስታሮትን አመለኩ። የእግዚአብሔርም ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ወደ ማረኩአቸውም ማራኪዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በዙሪያቸውም ባሉት በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ ጠላቶቻቸውንም ከዚያ ወዲያ ሊቋቋሙ አልቻሉም። እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ እግዚአብሔርም በእነርሱ ላይ እንደማለ፥ ወደ ወጡበት ሁሉ የእግዚአብሔር እጅ ትከፋባቸው ነበረች፤ እጅግም ተጨነቁ። እግዚአብሔርም መሳፍንትን አስነሣላቸው፥ ከሚማርኩአቸውም እጅ አዳኑአቸው። (መሣ. 2፡11-16)
የመሣፍንት መጽሐፍ ትራኬ በአጭሩ ይህ ነው፡፡ እስራኤላውያን እግዚአብሔርን በመተው ጣዖታትን ያመልካሉ፤ እግዚአብሔር ክፉኛ ይቀጣቸዋል፤ ንስሐ ገብተው ወደ እግዚአብሔር ይጮኻሉ፤ መሥፍንን አስነስቶ ያድናቸዋል፤ ከመሥፍኑ ሞት በኋላ እንደገና ጣዖት ያመልካሉ፤ እንደገና ክፉኛ ይቀጣሉ፤ ንስሐ ይገባሉ… ለ300 ዓመታት ያህል በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ከቆዩ በኋላ የነገሥታት ዘመን መጣ፡፡
በነገሥታት ዘመንም ተመሳሳይ ነገር ውስጥ ሲገቡ እየተቀጡ በንስሐ ሲመለሱ ምሕረት እየተደረገላቸው ለክፍለ ዘመናት ኖሩ፡፡ ክፋታቸው እየበዛ ሲመጣ የሰሜኑ መንግሥት ለአሦራውያን፣ የደቡቡ መንግሥት ደግሞ ለባቢሎናውያን አልፈው ተሰጡ (2ነገ. 17፣ 25)፡፡ ከ70 ዓመታት ሥቃይና ውርደት በኋላ የደቡቡ ሕዝብ ሲመለስ የሰሜኑ ግን ሕልውናውን ሊያጣ ችሏል፡፡ ይህ እንዴት አድልዎ ሊባል ይችላል? በኃጢአቱ ምክንያት እንደ ሕዝበ እስራኤል የተቀጣ ሕዝብ በዓለም ላይ ከቶ የት ይገኛል? እግዚአብሔር አምላክ አድልዎን የማያውቅ ፍትሃዊ አምላክ ነው፡፡ ደራሲውን ጥራዝ ነጠቅ ብንለው ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም!
ንቁ! ሙስሊም ሰባኪያን ሐሰተኞች ናቸው፡፡
ይቀጥላል…
[1] Gary N. Knoppers, J. Gordon McConville. Reconsidering Israel and Judah: Recent Studies on the Deuteronomistic History; Eisenbrauns Winona Lake, Indiana, 2000, p. 119
[2] Ibid., p. 3