መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው?
በሳሙኤል ግሪን
መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቲያኖች ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ በእንግሊዝኛ ባይብል የሚለው “ቢብሊያ” ከሚል የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን “መጻሕፍት” ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ አንድ መጽሐፍ ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ነቢያት፣ በተለያዩ ቦታዎችና በተለያዩ ቋንቋዎች በ1500 ዓመታት ውስጥ የተጻፉ የተለያዩ መጻሕፍት ስብስብ ነው፡፡ የሙሴን ሕግ (ቶራ)፣ የዳዊትን መዝሙር፣ የሰለሞንን መጻሕፍት፣ ኢሳይያስ፣ ኤርምያስ፣ ሕዝቅኤል፣ ዳንኤል፣ ሆሴዕ፣ ኢዩኤል፣ አሞፅ፣ አብድዩ፣ ዮናስ፣ ኢዮብ፣ ሚክያስ፣ ናሆም፣ ዕንባቆም፣ ሶፎንያስ፣ ሐጌ፣ ዘካርያስ፣ ሚልክያስና የመሳሰሉትን ነቢያት መጻሕፍት አካቷል፡፡ በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ የተጻፈውን የኢየሱስን ወንጌል ይዟል፡፡ የሐዋርያትም ጽሑፎች በውስጡ ይገኛሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ | |||
የሙሴ ሕግ (ቶራ) | የነቢያት መጻሕፍት | መዝሙራት | ወንጌል |
‹‹—————- 1500 ዓመታት —————-›› |
ቁርአን ስለ ተውራትና ወንጌል (ኢንጂል) (3፡3)፣ የነቢያት መጻሕፍት (3፡84)፣ እና መዝሙራት (ዘቡር) (4፡163) ይናገራል፤ ክርስቲያኖችንም “የመጽሐፉ ሰዎች” በማለት ይጠራቸዋል (ቁርአን 5፡68)፡፡
ክርስቲያኖች እነዚህ ሁሉ መጽሐፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለምን ኖሯቸው?
ክርስቲያኖች ሁሉንም ነቢያት ስለሚቀበሉና በመካከላቸው አድልዎን ስለማያደርጉ ሁሉም መጽሐፍት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አሏቸው፤ ያነቧቸዋልም፡፡
ሁለተኛ እግዚአብሔር በብዙ ነቢያት በኩል ተናግሮናል፡፡ መጻሕፍታቸው አንዳቸው በሌላቸው ላይ የተገነቡ ሲሆኑ በጋራ እንዲነበቡ የታሰቡ ናቸው፡፡ በጋራ በመሆንም የተሟላውን አምላካዊ መመርያ ይሰጡናል፡፡
ክርስቲያኖች ስለ እግዚአብሔር የሚያምኑት ሁሉ አጠቃላዩን የነቢያት መጽሐፍት ያገናዘበ ነው፡፡
የኢየሱስ ሐዋርያት ወንጌልን የተቀበሉ የነበሩ ቢሆኑም ከሙሴ ሕግ፣ ከነቢያትና ከመዝሙራት እየጠቀሱ ያስተምሩ ነበር፤ መጻሕፍቱንም ያነብቡ ነበር፡፡
ከተለያዩ አገራት የሆኑ ብዙ ሕዝቦች ክርስትናን ሲቀበሉ እንደ ሐዋርያት ሁሉ የሙሴን ሕግ፣ ነቢያትን፣ መዝሙራትንና ወንጌልን ተቀብለው ማንበባቸውን ቀጠሉ፡፡ ዛሬም ቢሆን አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን ወንጌልን ብቻ ሳይሆን የነቢያትን መጻሕፍት ሁሉ ይማራል፡፡ በክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ሁሉም የነቢያት መጻሕፍት በአደባባይ ይነበባሉ፣ ይሰበካሉ፡፡
ክርስትና ሰዎች የሙሴን ሕግ፣ ነቢያትንና መዝሙራትን ከወንጌል ጋር በማጣመር እንዲያነብቡና እንዲቀበሉ በማስተማር ነው የተስፋፋው፡፡ የነቢያት ሁሉ መጻሕፍት በሰው ልጆች ሁሉ ይታወቁ ዘንድ ክርስቲያኖች እነዚህን መጻሕፍት ወደ አብዛኞቹ ቋንቋዎች ተርጉመዋል፡፡
እርስዎና ነቢያት
ነቢያትን በሙሉ ማክበር ይፈልጋሉን? ትክክለኛው ነቢያትን የማክበርያ መንገድ እነርሱን መስማትና መጻሕፍታቸውን ማንበብ ነው፡፡ የእግዚአብሔርን ሁሉንም መልእክቶች ማወቅ ይፈልጋሉን? አንዱን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም የነቢያት መጻሕፍት ማንበብ ይጠበቅቦታል፡፡
እነዚህ ነቢያት በገዛ ቋንቋዎ ተተርጉመዋል፡፡ ክርስቲያኖች ቅዱሱን መጽሐፍ እንዲሰጡዎ ይጠይቁ፤ ወይንም ኦንላይን ፍለጋ ያድርጉ፡፡ የእግዚአብሔርን ነቢያት መጻሕፍት እንዳያነብቡ ማንም ሰው እንዲያሳስትዎት ወይንም እንቅፋት እንዲሆንብዎት አይፍቀዱ፡፡
ይህንን ጸሎት መጻለይ ይሻሉን?
ሁሉን ቻዩ አምላካችን በነቢያቶችህ ልትናገረን ፈቃድህ ስለሆነ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሁላቸውንም ማድመጥ እችል ዘንድ እርዳኝ፡፡ አሜን፡፡