በእስልምና ምንጮች መሠረት “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሎ የጸለየው ነቢይ ማን ነው?

በእስልምና ምንጮች መሠረት “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” ብሎ የጸለየው ነቢይ ማን ነው?

አንድ ሰለምቴ ነኝ ባይ አብዱል “የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው” የሚለውን ንግግር በተመለከተ በኛ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኝ ነጥብ በመጥቀስ በስድብ የታጀበ አጭር ጽሑፍ ለቋል፡፡ የጽሑፉ ሙሉ ቃል ሲቀነስ የአረብኛው ኮተት እንዲህ የሚል ነው፡-

—–

ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4417

አነሥ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛ በሑድ ጦርነት የፊት ጥርሳቸው ተሰበረ፣ እራሳቸው ቆሰለ፤ ደም ከፊታቸው ይጠርጉ ነበር፤ እንዲህ አሉ፦ “ያ ህዝብ እንዴት ሊድን ይችላል ነብዩን እያቆሰለ እና ጥርሱን እየሰበረ ወደ አላህ ይፀልይለታል? በዚያን ጊዜ የላቀው እና ክቡሩ አላህ፦ 3፥128 “አላህ በእነርሱ ላይ ይቅርታ እስኪያደርግ ወይም እነርሱ በዳዮች ናቸውና እስኪቀጣቸው ድረስ ለአንተ ከነገሩ ምንም የለህም” የሚለውን አንቀጽ አወረደ።

ነብያችንየጸለዩት ጸሎት ደግሞ ምን እንደሆነ ዐብደላህ ከእርሳቸው የሰማውን በሦስተኛ መደብ በሚቀጥለው ቁጥር እንዲህ ይነግረናል፦

ኢማም ሙስሊም : መጽሐፍ 19, ሐዲስ 4418

ለእኔ የአላህን መልእክተኛ ስመለከት ታዩኝ የተናገሩትን ሰማዋቸው፦ ነብይ በህዝቡ ሲደበድቡት፣ ደም ከፊቱ ሲጠርግ፦ “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” አለ።

አንዳንድ ቂል መሃይማን “ጌታዬ ሆይ ህዝቦቼን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅርታ አድርግላቸው” የሚለውን ከዚህ ጥቅስ ጋር ለማዛመድ ሞክረዋል፦

ሉቃስ 23፥34 ኢየሱስም፦ *አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው* አለ።

የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም። ይህንን የአዲስ ኪዳን ለዘብተኛ ምሁር ዶክተር ሄርማን እና ጽንፈኛ ምሁር ጀምስ ኃይት ተናግረዋል። NIV የግርጌ ማስታወሻ ላይም፦ “Luke 23፥34 some early manuscripts do not have this sentence” በማለት እርማችሁን እንድታወጡ አርድቷችኃል፡፡

እኛ የጠቀስነው ሐዲስ ሳሒህ አል-ቡኻሪ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን እንዲህ ይላል፡-

Bukhari, Volume 9, Book 84, Number 63:

Narrated ‘Abdullah: As if I am looking at the Prophet while he was speaking about one of the prophets whose people have beaten and wounded him, and he was wiping the blood off his face and saying, “O Lord! Fnetive my people as they do not know.

አብዱላህ እንዳስተላለፈው፡- ወደ ነቢዩ (ሙሐመድ) እያየሁ ሳለሁ ከነቢያ መካከል አንዱ ሕዝቦቹ ደብድበውት ባቆሰሉት ጊዜ ደሙን ከፊቱ ላይ እየጠረገ እንዲህ ሲል የተናገረውን ተናገሩ፡- “ጌታ ሆይ! ሕዝቤ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው፡፡”

ከዚህ ሐዲስ እንደምንረዳው አብዱላህ የተባለው የሙሐመድ ተከታይ ባስተላለፈው ዘገባ መሠረት ሙሐመድ ከቆሰለ በኋላ ይህንን ንግግር ተናግሯል፡፡ ነገር ግን ሐዲሱ ግልፅ አድርጎ እንዳስቀመጠው ሙሐመድ ንግግሩን ለመናገር የመጀመርያው ሰው አልነበረም፡፡ ከእርሱ በፊት አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ ነቢይ ተናግሮታል፡፡ የኛ ጥያቄ እንዲህ ያለ ንግግር የተናገረ ሙስሊሞች የሚቀበሉት “ነቢይ” ከኢየሱስ ውጪ ማን ነው? የሚል ነው፡፡ ንፁሃን ሰዎችን በእንቶ ፈንቶ ጉዳዮች ሲያርድና ሲያሳርድ የኖረው ሙሐመድ ሰዎችን ለመግደል በወጣበት አውደ ውጊያ ውስጥ ሆኖ ለዚያውም ቆስሎና ጥርሱ ረግፎ ሳለ እንዲህ ያለ ንግግር መናገሩ የማይመስል ቢሆንም ንግግሩ በሐዲሱ ውስጥ ተጠቅሷል፤ ስለዚህ ሙስሊሞች እንዲህ ያለ ንግግር የተናገረ ከኢየሱስ ሌላ እነርሱ የሚቀበሉት “ነቢይ” ማን እንደሆነ እንዲነግሩን ጠይቀናቸዋል፡፡ ሆኖም ይህ አብዱል ለስድብ የተፈጠረ የሚመስለውን ምላሱን በከንቱ ከማስረዘም በዘለለ ለዚህ ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም፡፡ ይልቁኑ ሐዲሱ በሙሐመድ የተጠቀሰው አባባል ከእርሱ በፊት በኖረ ሌላ ነቢይ ተነግሮ የነበረ መሆኑን በግልፅ ተናግሮ ሳለ ቡኻሪ ውስጥ የሚገኘውን ሐዲስ ሳይሆን ሌላ ሐዲስ በመጥቀስ አልፎ ተርፎም ትርጉሙን በማዛባት ለማድበስበስ ሞክሯል፤ ሐሳዊው አብዱል፡፡

ይህ ሰው በገዛ ሃይማኖቱ ላይ ከዋሸ በኋላ በክርስትና ላይም እንዲህ ሲል ዋሽቷል፡- “የሚያጅበው ግን ይህንን ንግግር እንኳን ኢየሱስ ሊናገረው ይቅርና የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም፡፡” ከዚያም አንዳንድ ጥንታውያን የግሪክ ቅጂዎች ይህንን ንግግር ይዘው አለመገኘታቸውን በተመለከተ NIV የእንግሊዘኛ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻው ላይ ያስቀመጠውን ይጠቅሳል፡፡ ማስታወሻው እንዲህ የሚል ነው፡- “some early manuscripts do not have this sentence.” ስለዚህ በ NIV መሠረት ይህ አባባል በአንዳንድ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ አልተጠቀሰም፡፡ “በአንዳንድ አልተጠቀሰም” ማለት በሁሉም አልተጠቀሰም ማለት አይደለም፡፡ አብዱል ግን  “የሉቃስ ወንጌል ላይ ባሉት የግሪክ እደ-ክታባት ላይ ሽታው የለም” በማለት አረፈው፡፡ ይህ አብዱል አላዋቂ፣ ሲከፋም ቀጣፊ ነው፡፡  ይህ ጥቅስ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ውስጥ የንባብ ልዩነቶች (Textual Variants) ሆነው ከተመዘገቡት መካከል አንዱ ቢሆንም በብዙ ጥንታውያን የግሪክ የእጅ ጽሑፎች ውስጥ ይገኛል፡፡ ቁርአንን ጨምሮ የትኛውም ጥንታዊ መጽሐፍ ከእንዲህ ያሉ ችግሮች የጸዳ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሊቃውንት ጥንታውያን የእጅ ጽሑፎችን በማመሳከር ትክክለኛው ንባብ የትኛው እንደሆነ ያሳውቃሉ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በጥንታውያን የእጅ ጽሑፎች ረገድ ቁርአንን ጨምሮ ከየትኛውም ጽሑፍ ጋር ለውድድር ሊቀርብ በማይችልበት ሁኔታ ቀዳሚውን ስፍራ ይዞ ስለሚገኝ ጥበቃውና አስተላላፉ እጅግ አስተማማኝ ነው፡፡

ለማንኛውም ይህ አብዱል በእስላማዊ ምንጮችም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሲዋሽ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፤ ሐሳዊነቱንም በአደባባይ አሳይቷል፡፡ እንዲህ ያሉ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ እስላማዊ ምንጮችን የማያውቁ ምሑር መሳዮች (Pseudo Scholars) በድፍረትና በራስ መተማመን ሲጽፉና ሲናገሩ ላያቸው ሰው የሚናገሩትን የሚያውቁ ይመስላሉ ነገር ግን ከዚያም ከዚህም የቃረሙትን ውዳቂ መረጃ ከማስተላለፍ የዘለለ ዕውቀት የላቸውም፡፡ ከሐሳውያን ተጠበቁ፡፡

መሲሁ ኢየሱስ