የሐፍሷ ቢንት ዑመር “ኦሪጅናል” ቁርኣን ለምን ተቃጠለ?

የሐፍሷ ቢንት ዑመርኦሪጅናልቁርኣን ለምን ተቃጠለ?

በኸሊፋ አቡበክር ትዕዛዝ በዘይድ ተዘጋጅቶ የነበረው ቁርኣን ሐፍሷ ቢንት ዑመር በተሰኘችው የሙሐመድ ሚስት እጅ ነበር፡፡ ኡሥማን በዘይድ አማካይነት ተሻሽሎ እንዲዘጋጅ ላደረገው ቁርኣን መነሻ ያደረገው የሐፍሷን ቁርኣን ሲሆን ሌሎች ቅጂዎችን በሙሉ የእሳት ሲሳይ ቢያደርግም ይኸኛውን ግን ሳያቃጥል መልሶላት ነበር (Sahih Bukhari 6:61:510)፡፡ ይህ ቅጂ ማርዋን ኢብን አል-ሐካም የተሰኘ ሰው የመዲና ገዢ እስከሆነበት ዘመን ድረስ በእጇ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን የእስልምናው ዓለም ዋና መቀመጫ የሦርያዋ ደማስቆ ስትሆን ዋና ገዢው ደግሞ ሙዓውያ ነበር፡፡  ማርዋን በዚህ ቁርኣን ምክንያት ወደ ፊት በሙስሊሞች መካከል ጥርጣሬና መለያየት እንዳይፈጠር በሚል ይህንን ቁርኣን ማጥፋት ይፈልግ የነበረ ቢሆንም ሐፍሷ ግን አሳልፋ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነችም። ነገር ግን ከእርሷ ሞት በኋላ ማርዋን የሐፍሷ ወንድም የነበረው አብደላህ ኢብን ዑመር ቅጂውን እንዲልክለት ጠየቀው፤ እርሱም ላከለት፡፡ እስላማዊ ድርሳናት ውስጥ በግልፅ እንደሠፈረው ከኡሥማን ቁርኣን ጋር ያለው ልዩነት ኋላ ላይ በሕዝበ ሙስሊሙ መካከል ችግር እንዳይፈጥር በሚል ፍርሃት ማርዋን ከቀደደው በኋላ አቃጠለው፡፡ (Ibn Abi Dawud. Kitab al-Masahif, p.24)። ይህ ታሪክ በሌሎች ብዙ ሙስሊም የታሪክ ጸሐፍት ተዘግቧል።

የሐፍሳ ቁርኣን በኡሥማን ትዕዛዝ በዘይድ ኃላፊነት ከተዘጋጀው ቁርኣን የተለየ ይዘት ስለነበረው የማርዋን ስጋት ትክክል ነበር፡፡ ለምሳሌ ያህል ኢብን አቢዳውድ የሚከተለውን ጽፈዋል፡-

“It is reported by Abdullah on the authority of Muhammad ibn Abdul Malik who reported from Yazid (etc.) … It is written in the codex of Hafsah, the widow of the Prophet (saw): “Observe your prayers, especially the middle prayer and the afternoon prayer”. (Ibn Abi Dawud, Kitab al-Masahif, p.87).

“አብዱላህ ከያዚድ በሰማው  የሙሐመድ ኢብን አበዱል ማሊክ ሥልጣን እንዳስተላለፈው (ወዘተ.) የነቢዩ (ሰዐወ) መበለት በነበረችው የሐፍሳ ጥራዝ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- “በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ እንዲሁም የአስር ሶላት ላይ ተጠባበቁ፡፡”

በአስ-ሱዩጢ “አል-ኢትቃን” መጽሐፍ ውስጥ ተመሳሳይ ዘገባ እናገኛለን (as-Suyuti, Al-ltqan fii Ulum al-Qur’an, p.193)

የኡሥማን ቅጂ እንደሆነ የሚነገርለት ዛሬ ያለው ቁርኣን “በሶላቶች (በተለይ) በመካከለኛይቱም ሶላት ላይ ተጠባበቁ” የሚል ሲሆን “እንዲሁም የአስር (ሰርክ) ሶላት” የሚል የለውም፡፡ በአረብኛ የኡሥማን ጥራዝ “ወሰላቲል ውስታ” ብቻ የሚል ሲሆነ የሐፍሷ ቁርኣን “ወሰላቲል አስር” የሚል ተጨማሪ ሐረግ አለው ማለት ነው፡፡ ይህ ከኡሥማን ንባብ ውስጥ የተወገደው ንባብ በሐፍሷ ቅጂ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአይሻ ቅጂ ውስጥም እንደሚገኝ ተነግሯል (Muwatta Imam Malik, p.64)፡፡

ቁርኣን ሰው ሠራሽ መጽሐፍ ነው የምንለው በምክንያት ነው!

 

ቅዱስ ቁርኣን