የእግዚአብሔር የበኵር ልጅ ማነው?
“እስራኤል የበኵር ልጄ ነው” (ዘጸአት 4:23)
“ኤፍሬምም በኵሬ ነውና” (ትንቢተ ኤርምያስ 31:9)
ጥያቄ፡- በአንድ ጊዜ በኵር ሊሆን የሚችል አንድ አካል ብቻ ሆኖ ሳለ እስራኤልና ኤፍሬም የእግዚአብሔር በኵር እንዴት ሊባሉ ቻሉ?
መልስ፡- ዘጸአት 4፡23 ላይ “ልጅ” የሚለው ቃል ዘይቤያዊ እንጂ ቀጥተኛ እንዳልሆ ሁሉ “በኵር” የሚለውም ቃል ዘይቤያዊ እንጂ ቀጥተኛ አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረት ብኵርና ውልደትን ብቻ ሳይሆን ተወዳጅነትና የበላይነትንም ያመለክታል፡፡ ስለዚህ ቃሉ የእሰራኤልንና የኤፍሬምን ተወዳጅነት ለማመልከት የገበ ዘይቤያዊ ቃል እስከሆነ ድረስ ግጭት ሊያስከትል አይችልም፡፡ ሌላው ደግሞ ኤፍሬም ከእስራኤል ነገዶች መካከል አንዱ በመሆኑ ለሕዝበ እስራኤል የተነገረው ብኵርና ይመለከተዋል፡፡ ስለዚህ እስራኤል የእግዚአብሔር በኵር ከሆነ እያንዳንዱ የእስራኤል ነገድ የእግዚአብሔር በኵር ነው ማለት ነው፡፡ በዚህም መሠረት እስራኤል በኵር ከሆነ ብኵርናው የእስራኤል አንዱ ነገድ የሆነውን ኤፍሬምን እንደሚያጠቃልል ግልፅ ነው፡፡ ስለዚህ በእነዚህ ጥቅሶች መካከል ምንም ዓይነት ግጭት የለም፡፡