የሙሐመድ የሐሰት ትንቢት
የደጃልን (የክርስቶስ ተቃሚ) መምጣት በተመለከተ የእስልምና ጀማሪ የሆነው ሙሐመድ ተከታዩን ትንቢት መናገሩ ሱናን አቡ ዳውድ በተሰኘው የሐዲስ መጽሐፍ ውስጥ ተጽፏል፡-
ሙአዝ ኢብን ጀበል እንደተረከው፡-
ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢየሩሳሌም የምታብበው ያሥሪብ ስትፈራርስ ነው፣ የያሥሪብ መፈራረስ ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ነው፣ ታላቁ ጦርነት የሚነሳው ኮንስታንትኖፕል ተሸንፋ ስትያዝ ነው፣ የኮንስታንትኖፕል መያዝ ደግሞ ደጃል (የክርስቶስ ተቃዋሚ) ሲመጣ ነው፡፡” ነቢዩ ባቱን ወይም ደረቱን በመምታት እንዲህ አለ፡ “ይህ አንተ (ሙአዝ ኢብን ጀበል) እዚህ የተቀመጥከውን ያህል እውነት ነው፡፡” ሱናን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 37፣ ሐዲስ ቁጥር 4281
ሙአዝ ኢብን ጀበል እንደተረከው፡-
ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፡- “ታላቁ ጦርነት፣ የኮንስታንትኖፕል መያዝና የደጃል መምጣት በሰባት ወር ውስጥ ይፈፀማል፡፡” ሱናን አቡ ዳውድ መጽሐፍ 37፣ ሐዲስ ቁጥር 4282 (ማሳሰብያ፡ ይህንን ሐዲስ ሙስሊም ሊቃውንት ደካማ ወይም ዷኢፍ ነው ይሉታል።)
“የፍጻሜው ዘመን ሲደርስ ኮንስታንትኖፕል ትሸነፋለች፡፡” ጃሚ አቲርሚዚ ቅጽ 4፣ መጽሐፍ 7፣ ሐዲስ 2239
ኮንስታንትኖፕል (ቁስጥንጢንያ) በቱርክ ጂሃዳውያን ተወርራ ከተያዘች ይኸው ድፍን 500 ዓመታት አለፉ፤ ሙሐመድ የተናገረው ደጃል ግን አልመጣም፡፡ ስለዚህ ትንቢቱ ሐሰት መሆኑ ተረጋግጧል፡፡
ሙሐመድ እውነተኛ ነቢይ ላለመሆኑ ይህ ግልፅ ማስረጃ አይደለምን?
በዚህ ዙርያ ከአንድ ሙስሊም ጋር በፌስቡክ ላይ አጭር ውይይት አድርገናል። የሙስሊሙ ወገን የቃላት አጠቃቀም ጥሩ ባይሆንም ሙግቱ ሙስሊሞች ለዚህ ጥያቄ የሚሰጡት የተለመደ ምላሽ በመሆኑ አምጥተነዋል፡፡
ሙስሊም፦
ታውቃለህ በዌብሳይትህ ላይ ይህን ክስ ስታቀርብ ከክስህ ጋር የሚሄድ አንድ ደካማ(ዶዒፍ) ሀዲስ “እነዚህ ሁሉ በ7 ወራት ይፈጸማሉ” የሚለውን ለጥፈህ ነበር፡፡ ያኛው ሀዲስ ምንም እንኳ ዳዒፍ ቢሆንም ትንቢቱ መቼ መፈጸም እንዳለበት #ጊዜ ጠቋሚ ነው፡፡ ዛሬ ግን ያ ደካማ ሀዲስ ማስረጃ እንደማይሆን ተምረህ ሳታቀርበው በመቅረት ከክስህ ጋር #ምንም #የማይገናኝ ሀዲስ ማለትም ተንቢቶቹ ከሚፈጸሙበት Sequence(ቅደም ተከተል) በዘለለ መቼ እንደሚፈጸሙ ምንም የማይገልጽን ጥሩ ሀዲስ በመለጠፍ 500 አመታት አልፈውታል ስለዚህ የሀሰት ትንቢት ብለህ አረፍከው😂😂
ደካማውን ሀዲስ ማስረጃ እንደማይሆን አውቀህ በማስወገድ ጽሁፍህን ማሻሻልህን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ አሁን የቀረህ ትንሽ intelligent መሆን ስለሆነ ትንሽ ትምህርት ልሰጥህ እመሞክራለሁ፡፡
ከላይ የለጠፍከው ሀዲስ ነገራት የሚፈጸሙበትን Sequence(ቅደም ተከተል) የሚገልጽ እንጂ መቼ ምን ይፈጸማል የሚለውን አይገልጽም፡፡ በሌላ አባባል X ከመጣ በኋላ Y ይመጣል፡፡ Y ከመጣ በኋላ ደግሞ Z ይመጣል ነው የሚለው፡፡ ታድያ አንድ ሰው ተነስቶ X ከመጣ በኋላ Y መጥቷል፤ ነገር ግን Zን ጠብቄው እስካሁን ስላልመጣ Z ከY በኋላ ይመጣል ያለን ሰውዬው ዋሽቷል ማለት ይችላል? በፍጹም አይችልም፡፡ ልቅ ስህተት የሚሆነው ቅደም ተከተሉ ቢሳሳትና Y ከመጣ በኋላ X መጥቶ ቢሆን ወይም Y ሳይመጣ በፊት Z ቢመጣ ነበር፡፡ ያኔ ስለ ቅደምተከተል የተናገረውን ሰው ቅደም ተከተሉ ተሳስቷል ብለን ክስ ማቅረብ እንችላለን፡፡ ግን ካልተባለ ነገር በመነሳት Fallacy አርጉመንት መፍጠር የከሳሹን ደካማነትና ግንዛቤ እጥረት የሚያሳይ ነው፡፡
ለምሳሌ ኮንስታንቲኖፕል በሙስሊም እጅ ሳትወድቅ ደጃል ቢመጣ፤ ወይም ደጃል ሳይመጣ ቂያማ ብትቆም የነብዩ(ሰዐወ) ትንቢት ትክክል አይደለም ብለህ መክሰስ ትችላለህ፡፡
Dani ነገራትን ሳትረዳና ባምሮህ ሳታገናዝ እንደው በጎቹ ብቻ ጻፉትና ወደ አማርኛ ልከርብት ከምትል በርጋት ራስህ ብታሰላስለው ይህን ወራዳና አዋራጅ ሙግት ታነሳለህ ብዬ አላስብም፡፡
Man I thought you were smart…
የኔ ምላሽ፦
ለመልስ ከሚሆኑ አረፍተ ነገሮች ይልቅ እኔን ለማብጠልጠል የጻፍካቸው ይበዛሉ፡፡ በመልስህ ከተማመንክ ይህ ሁሉ ማጀብያ አይረቤ ቃላት አያስፈልጉም፡፡ የህፃነናት ብሽሽቅ አታድርገው፡፡ ቅደም ተከተል ብቻ ነው ያልከው? በጣም ያስቃል፡፡ ሙሐመድ ሲናገር የነበረው ቅደም ተከተል ሳይሆን መቼ ምን እንደሚፈፀም ነው፡፡ ልብ ብለህ አንብብ፡- “”Constantinople will be conquered with the coming of the Hour.” በዚህ መሠረት የኮንስታንትኖፕል መሸነፍና የፍፃሜው ሰዓት Simultaneously ወይም በጣም በተቀራረበ ጊዜ የሚፀሙ እንጂ ተራርቀው የሚፈፀም አይደሉም፡፡ ልብ በል ሙሐመድ በዚህ ቦታ እየተናገረ የነበረው ስለ ሰዓቲቱ እንጂ ስለ ዘመን አይደለም፡፡ ስለዚህ በዓምስት መቶ ዓመታት ልታቀራርበው አትችልም፡፡ (ከዚህ በኋላ ምን ያህል እንደሚቆይ ማን ያውቃል?) ደዒፍ የተባለው ሐዲስ በሰባት ወራት አራርቆ ማስቀመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ነው፡፡ በነገርህ ላይ ደዒፍ ማለት ውድቅ ወይም ውሸት ማለት ሳይሆን አስተማማኝነቱ ላይ የተወሰነ ጥርጣሬ ያለበት ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ሊቃውንቶቻችሁ በጣም ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች እንኳ ሳይቀር ከሌሎች ሐዲሳት ጋር አስደግፈው የሚጠቀሙበት፡፡ ለማንኛውም እርሱ ሌላ ርዕስ ነው፡፡ አሁን እዚህ በተጠቀሰው እንነጋገር፡፡
ሁለተኛውንም ሐዲስ ልብ ብለህ አንብበው፡- “the outbreak of the great war will be at the conquest of Constantinople and the conquest of Constantinople when the Dajjal (Antichrist) comes forth.” “ታላቁ ጦርነት የሚነሳው ኮንስታንትኖፕል ተሸንፋ ስትያዝ ነው፣ የኮንስታንትኖፕል መያዝ ደግሞ ደጃል ሲመጣ ነው፡፡” ሙሐመድ እየተናገረ የነበረው ደጃል በሚመጣበት ጊዜ ኮንስታንትኖፕል እንደምትያዝ እንጂ ከተያዘች በኋላ 500 ዓመታትና ከዚያ በላይ ዘግይቶ እንደሚመጣ አይደለም፡፡ እንግሊዝኛውን ደጋግመህ አንብበው፡፡ ቅደም ተከተልን ሳይሆን መቼ ምን እንደሚፈፀም ነው እየተናገረ ያለው፡፡ እነዚህ የተባሉት ነገሮች ፈጣን በሆነ ሁኔታ በአጭር ጊዜ የሚፈፀሙ እንጂ በተራዘመ ጊዜ የሚፈፀሙ አይደሉም፡፡ ሙሐመድ ስለ ፍጻሜው ዘመን የተናገራቸውን ሌሎች የሐሰት ትንቢቶች ከግንዛቤ ውስጥ ካስገባህ ደግሞ ጉዳዩ ከዚህ በላይ የከፋ መሆኑ ይገባሃል፡፡
ስለዚህ መልስ ብለህ ከምትጣደፍ ጉዳዩን በሰከነ መንገድ ብታጠና ጥሩ ነው፡፡
