አስገራሚ እስላማዊ ሐዲሳት – 15

አስገራሚ እስላማዊ ሐዲሳት – 15

በወንድም ማክ


እስልማዊ የሐዲስ መጻሕፍት ብዙ አስገራሚ፣ አስቂኝና አስደንጋጭ ታሪኮችንና ትምህርቶችን በውስጣቸው ይዘዋል። በዚህ ተከታታይ ጽሑፍ የኛን አስተያየት ሳናክል በሐዲሳት መጻሕፍት ውስጥ የሚገኙ ወጎችንና ትምህርቶችን እናቀርባለን። አንባቢያንም እግዚአብሔር አምላክ የሰጣቸውን አእምሮ በመጠቀም እንዲመዝኗቸው እናበረታታለን።

የሁደይቢያህ የውል ስምምነት

(15) የጂሃድ ቅድመ ሁኔታ እና የውል ስምምነት

አል ሚስዋር ቢን ማኽራማ እና መርዋን እንደዘገቡት፦ የአላህ መልእክተኛ በሁደይቢያህ የውል ስምምነት ጊዜ ወጡ። የተወሰነ ርቀት እስኪቀር ድረስ ተጓዙና “ኻሊድ ቢን አል-ወሊድ የቁረይሽ ፈረሰኞችን እየመራ አል-ጋሚም በሚባል የጦር ግንባር የሆነውን ቦታ ላይ ይገኛል። ስለዚህ በስተቀኛችሁ ተጓዙ።” አላቸው። ከሙስሊሞች የጦር ሠራዊት ጉዞ የተነሳ አቧራው እርሱ ጋ እስኪደርስ ድረስ ኻሊድ የሙስሊሞችን መምጣት አላወቀም ነበር። ከዚያም ጉዳዩን ለቁረይሾች ለማሳወቅ በፍጥነት ተመልሶ ሄደ። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሰው ወደ እነሱ ወደሚሄድበት እስከ ታኒያ  (ተራራማው መንገድ) እስኪደርሱ ድረስ እየገሰገሱ ሄዱ። የነቢዩ ሴት ግመል ተንበረከከች። ሰዎችም ግመሏን ለማስነሳት የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ። “አል-ቀስዋ ዛለች፤ አል-ቀስዋ ዛለች” ማለት ጀመሩ። ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) “አል-ቀስዋ አልዛለችም፤ መዛል ልማዷ አይደለምና። ነገር ግን ዝሆንን ባስቆመው ነው የቆመችው” አለ። ከዚያም ነቢዩ “ነፍሴ በእጁ በሆነው እምላለሁ! እነሱ(ቁረይሾች) የአላህን ሕግጋት የሚያከብር ምንም ነገር ቢጠይቁኝ እፈቅድላቸው ነበር” አለ። ከዚያም ነቢዩ ግመሊቱን ገሰፃት። እርሷም ተነሳች። ነብዩ (ሰአወ)ሰዎች በትንሽ መጠን ይጠቀሙበት የነበረ ከአል-ሁደይቢያ በጣም ርቆ በሚገኝ አንድ ጉድጓድ (ጉድጓድ) ላይ እስኪደርስ ድረስ መንገዳቸውን ቀይረው ተጓዙ። ከዚያም ሰዎች የነበረውን ውኃ ተጠቅመው ጨረሱና ነቢዩ ላይ ከውኃ ጥማት የተነሳ ማጉረምረም ጀመሩ። ነቢዩም ከከረጢቱ ቀስት አወጣና ቀስቱን በጉድጓዱ ውስጥ እንዲያደርጉ ነገራቸው። ወላሂ ሰዎች ጠጥተው ረክተው እስኪመለሱ ድረስ ውኃ ከጉድጓዱ ውስጥ መውጣት ጀመረ። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ቡዳይል ቢን ዋርቃ አል-ኹዛኢ ከኹዛዓ ሰዎች ጋር ሆኖ መጣ። እነሱም የነቢዩ አማካሪዎች ሲሆኑ ከነቢዩ ምንም ነገር የማይደብቁ ሚስጥረኞች የሆኑ የቲማህ ሰዎች ነበሩ። ቡዳይልም “ካዕብ ቢን ሉአይን እና ዓምር ቢን ሉአይንን የተትረፈረፈ ውኃ በሚገኝበት አል-ሁደይቢያ ግመሎችን እያረቡ (ከነ ልጆቻቸውና ሴቶቻቸው) ነው ትተናቸው የመጣነው። ካዕባን እንዳትጎበኙ በእናንተ ላይም ጦርነትን ማወጃቸው አይቀርም” አለ። ከዚያም ነቢዩ እንዲህ አለ “እኛ እዚህ የመጣነው ኡምራ ልናደርግ እንጂ ከማንም ጋር ለመዋጋት አይደለም። ቁረይሾች በጦርነቱ መዳከማቸውና መጎዳታቸው ምንም ጥርጥር የለውም። ስለዚህ እነሱ የሚፈልጉት ከሆነ ከእነሱ ጋር ስምምነት እፈፅማለሁ። በእኔና በሰዎች (ከቁረይሽ ውጪ ያሉ ዓረቦች) መካከል ከመግባት ይቆጠቡ፤ እኔ አረቦቹን ካሸነፍኳቸው ልክ እንደሌሎቹ ቁረይሾች እስልምናን የመቀበል አማራጭ ይኖራቸዋል። ከፈለጉ ደግሞ ለመዋጋት ቢያንስ በድጋሚ መጠናከር አለባቸው። ስምምነቱን ካልተቀበሉ ግን ነፍሴ በእጁ ባለው እምላለሁ ራሴ እስክሞት ድረስ እዋጋቸዋለሁ። አላህም ድል እንደሚቀዳጅ እርግጠኛ ነኝ።” ቡደይላም መልሶ “ያልከኝን አሳውቃቸዋለሁ” አለ። ከዚያም ወጥቶ ቁረይሾች ጋ እስኪደርስ ሄደ። እንዲህ አላቸው “ፈቃደኛ ከሆናችሁ ሰውዬው (ሙሐመድ) ለእናንተ እንድናደርስ የነገረንን ነገር ልንነግራችሁ መጥተናል።” አላቸው። ከቁረይሾች መካከል ቂሎቹ ምንም መረጃ እንደማይፈልጉ ተንጫጩ። ብልሆቹ ቁረይሾች ግን “እስኪ እሱ ሲናገር የሰማኸውን ንገረን” አሉት።

ቡደይላን “እንዲህ እና እንዲህ ብሏል” በማለት ነቢዩ የተናገረውን ነገር ነገራቸው። ኡርዋ ቢን መስዑድ ተነስቶ “ሰዎች ሆይ እናንተ ልጆቼ አይደላችሁምን?” አላቸው። ሰዎቹም “አዎን ነን!” አሉት። እርሱም መልሶ “እኔስ አባታችሁ አይደለሁንም?” አላቸው እነሱም “አዎን ነህ!” አሉት። እርሱም መልሶ “ትጠራጠሩኛላችሁ?” አላቸው። እነሱም “በፍፁም” አሉት። እርሱም በድጋሚ “እንዲያግዟችሁ የኡዛክን ሰዎ እንደጠራሁላችሁ፤ እነሱ እንቢ ባሉ ጊዜ ዘመዶቼንና የሚታዘዙኝን ልጆቸን እንዳመጣሁላችሁ አታውቁምን?” አላቸው። እነሱም “አዎ እኛውቃለን” አሉት። ከዚያም እርሱ መልሶ “መልካም፣ ይህ ሰው (ነቢዩ) ብትቀበሉ የሚሻላችሁን በጎ ምክንያታዊ ሀሳብ ነው ያቀረበው። እኔም ሄጄ እንድገናኘው ፍቀዱልኝ።” አላቸው። እነሱም “ሂድና ተገናኘው” አሉት። ከዚያም ወደ ነቢዩ ሄዶ ከእርሱ ጋር መነጋገር ጀመረ። ኡርዋ ቡደይል የነገረውን የሚመስል እጅግ ተቀራራቢ ነገር ነቢዩ ነገረው።

ከዚያም ዑርዋ “ሙሐመድ ሆይ! ግንኙነትህን ለማጥፋት በመነሳትህ ምንም አይነት ችግር አይሰማህም? ከአረቦች መካከል ካንተ በፊት የገዛ ዘመዶቹን የጨፈጨፈ ሰው ሰምተህ ታውቃለህ? በሌላ በኩል ደግሞ ተቃራኒው ቢከሰት ወይም ብትሸነፍ (ማንም ሰው አይረዳህም)፤ ከጎንህም የሚረባ ሰው አላይም። ሁሉም ከተለያየ ጎሳ ሲሆኑ ችግር ቢፈጠር ብቻህን ጥለውህ የሚፈረጥጡ ናቸው። ደግሞም ትሰደባለህ” አለው። ይህንን ሲሰማ አቡበከር “ሂድና የአላትን ቂንጥር ጥባ። እኛን ነው ነቢዩን ጥለው ይሮጣሉ ያልከን?” አለው። ዑርዋም “ማነው ይሄ ሰውዬ?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎችም “አቡ በከር ነው” አሉት። ዑርዋም ለአቡ በከር መልሶ “ስላደረጋችሁልኝ ውለታ ባይሆን ኖሮ እበቀልህ ነበር።” አለው። ዑርዋም የነቢዩን ፂም ይዞ ሲያስወራው ሳለ አል-ሙጊራ ቢን ሹዕባ ሰይፉን ይዞ የራስ መከላከያ ቆቡን እንዳደረገ ከነቢዩ ራስጌ ቆሞ ነበር።

ዑርዋም እያወራ እጁን ወደ ነቢዩ ፂም በሰደደ ቁጥር አል-ሙጊራ በሰይፉ እጄታ እጁን እየመታው “እጅህን ከነቢዩ ፂም አንሳው” ይል ነበር። ዑርዋም ቆመና “ማነው ይሄ ሰውዬ?” ብሎ ጠየቀ። ሰዎቹም “አል-ሙጊራ ቢን ሹብዓ ነው” አሉት። ዑርዋም መልሶ “አንተ አታላይ! የክህደትህን መጥፎ ውጤት ለማስተካከል የተቻለኝን እያደረግኩ አይደለምን?” አለው። አል-ሙጊራ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከአንዳንድ ሰዎች ጋር አብሮ ይኖር ነበር። ሰዎቹን ገድሎ ንብረታቸውንም ከዘረፈ በኋላ (ወደ መዲና) በመምጣት እስልምናን ተቀበለ። ነቢዩም “እስልምናህን እቀበላለሁ። ከንብረትህ ግን አንዳች አልወስድም” ብሎት ነበር። ዑርዋን የነቢዩን ጓዶች (ሰሃቦች) መመልከት ጀመረ። ወላሂ ነቢዩ ምራቁን በተፋ ቁጥር ምራቁ ከመካከላቸው በአንዳቸው እጅ ላይ ያርፍ ነበር። ምራቁንም ፊታቸውንና ቆዳቸውን ይቀቡት ነበር። ነቢዩ ካዘዛቸው ትእዛዙን ወዲያውኑ ይፈፅሙ ነበር። ዉዱዕ (ትጥበት) ከፈፀመ የተረፈውን ውሃ ለመውሰድ ይታገሉ ነበር። ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩም ድምፃቸውን ከእርሱ አያስበልጡም፣ ፊቱንም ቀና ብለው አይመለከቱም ነበር።

ዑርዋም ወደ ህዝቦቹ ተመልሶ “ሰዎቼ ወደ ተለያዩ ነገስታትና ቄሳሮች ወደ ኾስራኡዎች እና ነጃሺዎች ሄጃለሁ። ነገር ግን ነቢዩ እንደሚከበረው አንዳቸውም ሲከበሩ አላየሁም። ምራቁን በተፋ ቁጥር ምራቁ ከመካከላቸው በአንዳቸው እጅ ላይ ያርፍ ነበር። ምራቁንም ፊታቸውንና ቆዳቸውን ይቀቡት ነበር። ነቢዩ ካዘዛቸው ትእዛዙን ወዲያውኑ ይፈፅሙ ነበር። ዉዱዕ (ትጥበት) ከፈፀመ የተረፈውን ውሃ ለመውሰድ ይታገሉ ነበር። ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩም ድምፃቸውን ከእርሱ አያስበልጡም፣ ፊቱንም ቀና ብለው አይመለከቱም ነበር” አላቸው። ጨምሮም “የሰጣችሁ አማራጭ በጎ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም። ስለዚህ ተቀበሉት” አላቸው። ከበኒ ኪናና የሆነ ሰው “ወደእርሱ እኝድሄድ ፍቀዱልኝ” አላቸው። እነሱም ፈቀዱለት። እርሱም ወደ ነቢዩና ወደ ጓዶቹ ሲቀርብ ነቢዩ “ይህ ሰው እገሌ ነው። ቡድንን (የግመል መስዋዕትን) ከሚያከብሩ ሰዎች ጊሳ ነው። ስለዚህ ቡድን አምጡለት” አላቸው። ከዚህም የተነሳ ቡድን ወደ ፊቱ አመጡለት። ሰዎቹም ታልቢያን እየቀሩ ተቀበሉት።

ሰውዬውም ይህንን እንዳየ “አላህ የተመሰገነ ይሁን። በእውነቱ እነዚህን ሰዎች ካዕባን እንዳይጎበኙ መከልከል አይገባም” አለ። ወደ ሰዎቹ ሲመለስ “ያጌጡና ምልክት የተደረገባቸው ቡድኖች አየሁ። እነዚህን ሰዎች ካዕባን እኝዳይጎበኙ መከልከልን አልመክርም” አላቸው። ሌላ ሚክራዝ ቢን ሃፍስ የተባለ ሰው ተነሳና ወደ ሙሐመድ ለመሄድ ፍቃድ ጠየቃቸው። እነሱም ፈቀዱለት። እሱም ወደ ሙስሊሞች ሲደርስ “እነሆ ሚቅራዝ! እርሱም ጨካኝ ሰው ነው” አሉ። እርሱም ከነቢዩ ጋር እየተነጋገረ በነበረ ጊዜ ሱኸይል ቢን ዓምር መጣ። ሱኸይል ብን ዓምር ሲመጣ ነቢዩ “አሁን ነገሩ ቀለለ” አለ። ሱኸይልም ነቢዩን “እባክህ ከእኛ ጋር የሰላም ስምምነት አድርግ” አለው። ስለዚህ ነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጸሃፊውን ጠርቶት “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ብለህ ጻፍ” አሉት። ሱሀይልም “ለረህመቱላሂ” በአላህ ይሁንብኝ ምን ማለት እንደሆነ አላውቅም አለ።

ስለዚህ ከዚህ በፊት ትጽፍ እንደነበረው አላህ ሆይ በአንተ ብለህ ጀምር” አለው።  ሙስሊሞችም “በአላህ እንምላለን! በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ብለን ካልሆነ አንጽፍም” አሉ። ነቢዩም “አላህ ሆይ በስምህ” ብላችሁ ጻፉ አላቸው። ከዚያም በኋላ “ይህ የአላህ መልእክተኛ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ያጠናቀቁት የሰላም ስምምነት ነው” ብሎ አስጻፋቸው። ሱኸይልም መልሶ “የአላህ መልእክተኛ መሆንህን የማንም ቢሆን ኖሮ ካዕባን እንዳትጎበኝ ባልከለከልኩህና ባልተዋጋሁህ ነበር። ስለዚህ ‘ሙሐመድ ቢን አብደላህ’ ብለህ አስጽፋቸው።” አለው። ከዚያም ነቢዩ መልሶ “እናንተ ሰዎች ባታምኑበትም ወላሂ እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ። ሙሐመድ ቢን አብደላህ ብላችሁ ጻፉ” አላቸው። አዝ-ዙህሪ “ነቢዩ የአላህን ህግ እስካልጣሰና እስካከበረ የሚፈልጉትን ሁሉ አደርጋለሁ እንዳለው እንዲሁ አደረገ” አለ። ነቢዩም ሱኸይልን “ካዕባን እንድንጎበኝና ተዋፍ እንዳደርግ በምትፈቅድልን ቅድመ ሁኔታ ነው” አለው። ሱኸይልም መልሶ “ለሙሐመድ ተገዝተዋል ብለው ዓረቦቹ እንዳያወሩብን በዚህ ዓመት አንፈቅድላችሁም። ነገር ግን በሚቀጥለው ዓመት እንፈቅድላችኋለን” አለው። ነቢዩም ይህንን አስጽፎ ያዘው።

ከዚያ ሱኸይልም መልሶ “ከመካከላችን ማንም ሰው ወደ እናንተ ቢመጣ ሃይማኖታችሁን ቢቀበል እንኳን ሰውዬውን ወደ እኛ ትልኩታላችሁ” አላቸው። ሙስሊሞችም መልሰው “አላህ ጥራት ተገባው። አንድ ሰው ሙስሊም ከሆነ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት አምልኮ ይመለሳል?” አሉ። በዚህም ሁኔታ እያሉ አቡ ጃንዳል ሱኸይል ቢን ዓምር ታስሮ እየተንገዳገደ ወደ ሙስሊሞች መጥቶ በፊታቸው ወደቀ። እንዲህም አለ “ሙሐመድ ሆይ ይህ ስምምነት ከአንተ ጋር ያደረግነው ስምምነት የመጀመሪያችን ነው። አቡ ጃንዳልን ስጠኝ” አለው። ነቢዩም መልሶ “የውል ስምምነቱ ገና ተጽፎ አልተጠናቀቀም” ብሎ መለሰለት። ሱኸይልም “እርሱን እንድትይዘው አልፈቅድልህም” አለው።

ነቢዩም “አድርገው” አለው። ሰውዬውም “አላደርገውም” አለው። ሚክራዝም “ውሰደው በቃ” አሉት። አቡ ጃንዳልም “ሙስሊሞች ሆይ ሙስሊም ከሆንኩ በኋላ ወደ ጣዖት አምልኮ ልመሰለስ ነው? እንዴት እንደተሰቃየሁ አይታያችሁም?” አላቸው።

አቡ ጃንዳልም በአላህ መንገድ እጅግ አሰቃይተውት ነበር። ዖማር ኢብኑ አል-ኻጣብ እንዲህ አለ “ወደ ነቢዩ ሄድኩና አንተ ቆይ የአላህ መልእክተኛ አልነበርክ እንዴ? አልኩት። እርሱም ‘አዎን ነኝ’ አለ። እኔም መልሼ ‘የእኛ መንገድ ፍትሃዊና የጠላቶቻችን መንገድ አመጽ አይደለምን?’ አልኩት። እርሱም ‘ አዎን’ ብሎ መለሰልኝ። እኔም መልሼ ‘ታድያ ለምንድነው የምንለማመጣቸው?’ አልኩት። እርሱም ‘እኔ የአላህ መልእክተኛ ነኝ። እርሱን ማስከፋት አልፈልግም። አላህም ድልን ይሰጠኛል’ አለ። እኔም ‘ወደ ካዕባ እንደምንጎበኝና ተዋፍ እንደምናደርግ ነግረኸን አልነበረም?’ አልኩት። እርሱም ‘ታድያ በዚህ ዓመት እንደምንሄድ ነው የነገርኳችሁ?’ አለ። እኔ ‘አይደለም’ አልኩት። እርሱም ‘ስለዚህ ካዕባት ትጎበኛላችሁ በዙሪያውም ትዞራላችሁ’ አለ።” ዖማርም ጨምሮ “ወደ አቡበከር ሄድኩና ‘አቡበከር ሆይ ይህ ሰው የአላህ መልእክተኛ አይደለም እንዴ?’ አልኩት። እርሱም መልሶ ‘አዎን’ አለኝ። እኔም መልሼ ‘ታድያ ለምንድነው በሃይማኖታችኝ ተለማማጭ የምንሆነው?’ አልኩት። አቡበከርም ‘እርሱ የአላህ መልእክተኛ ነው። አላህን ማሳዘን አይፈልግም። አላህ ድልን ይሰጠዋል። ስለዚህ እርሱ ትክክል ነው። ከእርሱ ወገን ሁን’ አለኝ። እኔም ‘ካዕባን እንደምንጎበኝና ተዋፍ እንደምናደርግ ቃል ገብቶልን አልነበረም?’ አልኩት። እርሱ ‘አዎን ነገር ግን በዚህ ዓመት ነው የምትጎበኙት ብሎህ ነበር?’ አለኝ። እኔም ‘አይደለም’ አልኩት። እርሱም ‘ወደ ካዕባ ትሄዳለህ ተዋፍም ታደርጋለህ’ አለኝ።”

አዝ-ዙህሪ እንዲህ አለ “ዖማር እንዲህ አለ ‘ለጠየኳቸው ያልተገባ ጥያቄ መካሻ ብዙ ሥራ ሰራሁ’ አለ።” የውል ስምምነቱ ጽሑፍ ሲጠናቀቅ ነቢዩ ለጓዶቹ “ተነሱና መስዋዕታችሁን እረዱ ራሳችሁንም ተላጩ” አላቸው። ነገር ግን ከመካከላቸው አንድም ሰው አልተነሳም። ነቢዩም ሦስት ጊዜ ደጋገመ። ማንም ሰው ሳይነሳ ሲቀር ወደ ኡም ሰላማህ ሄዶ ሰዎቹ ለእርሱ ያሳዩትን ባህርይ ነገራት። ኡም ሰላማም “የምታዛቸውን እንዲፈጽሙ ትፈልጋለህን? እንግዲያውስ ሂድና ማንንም ሰው ሳታናግር ከእነሱ ቀድመህ መስዋዕትህን እረድ ፀጉር ቆራጭህን ጠርተህ መላጨት ጀምር” አለችው። ከዚያም ነቢዩ ወጣ መስዋዕቱን እስኪያርድና ፀጉር ቆራጩን ጠርቶ እስኪላጭ ድረስ ማንንም ሰው አላናገረም። ይህንንም ሲያዩ የነቢዩ ጓዶች ተነስተው መስዋዕታቸውን ማረድ ፀጉራቸውንም እርስ በረስ መላጨት ጀመሩ። ከፍተኛ ጥድፊያ ስለነበረ እርስ በርስ የመገዳደል አደጋ ነበር። ከዚያም በኋላ አንዳንድ አማኝ ሴቶች ወደ ነቢዩ መጡና አላህ የሚከተለውን ጥቅስ አወረደ “ምእምናት ስደተኞች ኾነው በመጧችሁ ጊዜ ፈትኑዋቸው (60:10)”። ከዚያም ዖማር ካፊር የነበሩ ሁለት ሚስቶቹን ፈታቸው። በኋላም ሙዓዊያህ ቢን አቡ ሱፍያን አንደኛዋን ሲያገባት ሳፍዋን ቢን ኡመያህ ሌላይቱን አገባት።

ነቢዩ ወደ መዲና በተመለሱ ጊዜ አቡ ባሲር አንድ ከቁረይሽ እስልምናን የተቀበለ ሰው ወደ እርሱ ሲመጣ ተመለከተው። ካፊሮችም በእርሱ ፈንታ ሁለት ካፊሮችን ካሉ። እነሱም ነቢዩን “የገባህልንን ቃል ጠብቅ” አሉት። ከዚያም ነቢዩ አሳልፎ ሰጣቸው። ከዚያም ሰውዬውን ይዘውት እስከ ዱል-ሁለይፋ ድረስ ይዘውት ሄዱ። በዚያም ይዘውት የነበረውን ቴምር ለመብላት ተቀመጡ። አቡ ባስርም ከመካከላቸው ለአንዱ “እገሌ ሆይ ወላሂ ምርጥ ሰይፍ ይዘሃል” አለው። ሌላኛው ሰውም ከሰገባው አወጣውና “ወላሂ በጣም ምርጥ ነው። ብዙ ጊዜ ሞክሬዋለሁ” አለ። አቡ ባስርም “እስኪ ልሞክረው” አለው። ሰውዬውም ሲሰጠው እስኪሞት ድረስ መታው። ወደ እየሮጠ መጥቶ መስጊድ ውስጥ እስኪገባ ድረስ የሰውዬው ጓዶች ሮጠው ሸሹ። የአላህ መልእክተኛም ሲያየው “ይህ ሰው የፈራ ይመስላል” አለ። ወደ ነቢዩም ሲደርስ “ጓዶቼ ተገድለዋል። እኔም ተገድዬ ነበር ለጥቂት ተረፍኩ” አለ። አቡ ባስርም መጣና እንዲህ አለ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ እኔን ለካፊሮች መልሰህ ሃላፊነትህን እንድትወጣ አድርጎ እኔን ግን ከእነሱ አድኖኛል” አለው። ነቢዩም “ለእናቱ ወዮለት! ምነኛ የጦር አጋዥ ይሆናል። ደጋፊዎች ብቻ ይኖሩታል” አለ። አቡ ባስርም ይህንን ሲሰማ ነቢዩ በድጋሚ ለእነሱ አሳልፎ እንደሚሰጠው ተረድቶ ሸሽቶ የባር ዳርቻ እስኪደርስ ድረስ ተጓዘ።

አቡ ጃንዳል ቢን ሱኸይል ካፊሮች ነፃ አወጡትና አቡ ባስርን ተቀላቀለ። ከዚያ ጊዜ በኋላ ከቁረይሽ ማንም ሰው እስልምናን ሲቀበል ሃይለኛ ቡድን እስኪመሠርቱ ድረስ አቡ ባስርን ይቀላቀል ነበር። ወላሂ የቁረይሽ የንግድ ተጓዥ ወደ ሻም በደረሰ ቁጥር ያጠቁና  ንብረታቸውን ይዘርፏቸው ነበር። ከዚህም የተነሳ ቁረይሾች ወደ ነቢዩም ለአላህ እና ለዘመዶቹ ብሎ ወደ ነቢዩ የሚመጣ ማንኛውም ሰው ጥበቃ እንደሚደረግለት ለእነ አቡ ባስር መልእክት እንዲልክ ለመኑት። ስለዚህም ነቢዩ ወደነ አቡ ባስር መልእክት ላከ አላህም የሚከተለውን መለኮታዊ አንቀጽ አወረደ፦

24  እርሱም ያ በመካ ውስጥ በእነርሱ ላይ ካስቻለችሁ በኋላ እጆቻቸውን ከእናንተ ላይ እጆቻችሁንም ከእነርሱ ላይ የከለከለ ነው፡፡ አላህም የምትሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡

25  እነርሱ እነዚያ የካዱ፣ ከተከበረው መስጊድም የከለከሏችሁ፣ መስዋእቱንም የታሰረ ሲኾን በስፍራው እንዳይደርስ (የከለከሉ) ናቸው፡፡ የማታውቋቸው የኾኑ ምእመናን ወንዶችና ምእምናት ሴቶች (ከከሓዲዎቹ ጋር) ባልነበሩ ያለ ዕውቀት እነርሱን መርገጣችሁና ከእነረሱ (በኩል) መከፋት የሚነካችሁ ባልኾነ ኖሮ (እጆቻችሁን ባላገድን ነበር) አላህ የሚሻውን ሰው በእዝነቱ ውስጥ ያገባ ዝንድ (እጆቻችሁን አገደ)፡፡ በተለዩ ኖሮ እነዚያን ከእነርሱ ውስጥ የካዱትን አሳማሚን ቅጣት በቀጣናቸው ነበር፡፡

26  እነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ አላህም በመልክተኛው ላይና በምእምናኖቹ ላይ እርጋታውን አወረደ፡፡ መጥጠበቂያይቱንም ቃል አስያዛቸው፡፡ በእርሷም ተገቢዎች ባለቤቶችዋም ነበሩ፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ዐዋቂ ነው፡፡

ትምክህታቸውና ትዕቢታቸው መሐመድ የአላህ ነብይ መሆኑን አለማመናቸውና በውል ስምምነቱ ውስጥ “በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በሆነው በጣም አዛኝ በሆነው” የሚለውን ለመጻፍ ፈቃደኛ አለመሆናቸው ነው። እነሱም (ጣዖት አምላኪያን) ሙስሊሞቹን ቤቱን (ካዕባን) እንዳይጎበኙ ከለከሏቸው።

باب الشُّرُوطِ فِي الْجِهَادِ وَالْمُصَالَحَةِ مَعَ أَهْلِ الْحَرْبِ وَكِتَابَةِ الشُّرُوطِ(15)

حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مُحَمَّدٍ، حَدَّثَنَا عَبْدُ الرَّزَّاقِ، أَخْبَرَنَا مَعْمَرٌ، قَالَ أَخْبَرَنِي الزُّهْرِيُّ، قَالَ أَخْبَرَنِي عُرْوَةُ بْنُ الزُّبَيْرِ، عَنِ الْمِسْوَرِ بْنِ مَخْرَمَةَ، وَمَرْوَانَ، يُصَدِّقُ كُلُّ وَاحِدٍ مِنْهُمَا حَدِيثَ صَاحِبِهِ قَالَ خَرَجَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم زَمَنَ الْحُدَيْبِيَةِ، حَتَّى كَانُوا بِبَعْضِ الطَّرِيقِ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّ خَالِدَ بْنَ الْوَلِيدِ بِالْغَمِيمِ فِي خَيْلٍ لِقُرَيْشٍ طَلِيعَةً فَخُذُوا ذَاتَ الْيَمِينِ ‏”‏‏.‏ فَوَاللَّهِ مَا شَعَرَ بِهِمْ خَالِدٌ حَتَّى إِذَا هُمْ بِقَتَرَةِ الْجَيْشِ، فَانْطَلَقَ يَرْكُضُ نَذِيرًا لِقُرَيْشٍ، وَسَارَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم حَتَّى إِذَا كَانَ بِالثَّنِيَّةِ الَّتِي يُهْبَطُ عَلَيْهِمْ مِنْهَا، بَرَكَتْ بِهِ رَاحِلَتُهُ‏.‏ فَقَالَ النَّاسُ حَلْ حَلْ‏.‏ فَأَلَحَّتْ، فَقَالُوا خَلأَتِ الْقَصْوَاءُ، خَلأَتِ الْقَصْوَاءُ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ مَا خَلأَتِ الْقَصْوَاءُ، وَمَا ذَاكَ لَهَا بِخُلُقٍ، وَلَكِنْ حَبَسَهَا حَابِسُ الْفِيلِ، ثُمَّ قَالَ وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لاَ يَسْأَلُونِي خُطَّةً يُعَظِّمُونَ فِيهَا حُرُمَاتِ اللَّهِ إِلاَّ أَعْطَيْتُهُمْ إِيَّاهَا ‏”‏‏.‏ ثُمَّ زَجَرَهَا فَوَثَبَتْ، قَالَ فَعَدَلَ عَنْهُمْ حَتَّى نَزَلَ بِأَقْصَى الْحُدَيْبِيَةِ، عَلَى ثَمَدٍ قَلِيلِ الْمَاءِ يَتَبَرَّضُهُ النَّاسُ تَبَرُّضًا، فَلَمْ يُلَبِّثْهُ النَّاسُ حَتَّى نَزَحُوهُ، وَشُكِيَ إِلَى رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم الْعَطَشُ، فَانْتَزَعَ سَهْمًا مِنْ كِنَانَتِهِ، ثُمَّ أَمَرَهُمْ أَنْ يَجْعَلُوهُ فِيهِ، فَوَاللَّهِ مَا زَالَ يَجِيشُ لَهُمْ بِالرِّيِّ حَتَّى صَدَرُوا عَنْهُ، فَبَيْنَمَا هُمْ كَذَلِكَ، إِذْ جَاءَ بُدَيْلُ بْنُ وَرْقَاءَ الْخُزَاعِيُّ فِي نَفَرٍ مِنْ قَوْمِهِ مِنْ خُزَاعَةَ، وَكَانُوا عَيْبَةَ نُصْحِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم مِنْ أَهْلِ تِهَامَةَ، فَقَالَ إِنِّي تَرَكْتُ كَعْبَ بْنَ لُؤَىٍّ وَعَامِرَ بْنَ لُؤَىٍّ نَزَلُوا أَعْدَادَ مِيَاهِ الْحُدَيْبِيَةِ، وَمَعَهُمُ الْعُوذُ الْمَطَافِيلُ، وَهُمْ مُقَاتِلُوكَ وَصَادُّوكَ عَنِ الْبَيْتِ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّا لَمْ نَجِئْ لِقِتَالِ أَحَدٍ، وَلَكِنَّا جِئْنَا مُعْتَمِرِينَ، وَإِنَّ قُرَيْشًا قَدْ نَهِكَتْهُمُ الْحَرْبُ، وَأَضَرَّتْ بِهِمْ، فَإِنْ شَاءُوا مَادَدْتُهُمْ مُدَّةً، وَيُخَلُّوا بَيْنِي وَبَيْنَ النَّاسِ، فَإِنْ أَظْهَرْ فَإِنْ شَاءُوا أَنْ يَدْخُلُوا فِيمَا دَخَلَ فِيهِ النَّاسُ فَعَلُوا، وَإِلاَّ فَقَدْ جَمُّوا، وَإِنْ هُمْ أَبَوْا فَوَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، لأُقَاتِلَنَّهُمْ عَلَى أَمْرِي هَذَا حَتَّى تَنْفَرِدَ سَالِفَتِي، وَلَيُنْفِذَنَّ اللَّهُ أَمْرَهُ ‏”‏‏.‏ فَقَالَ بُدَيْلٌ سَأُبَلِّغُهُمْ مَا تَقُولُ‏.‏ قَالَ فَانْطَلَقَ حَتَّى أَتَى قُرَيْشًا قَالَ إِنَّا قَدْ جِئْنَاكُمْ مِنْ هَذَا الرَّجُلِ، وَسَمِعْنَاهُ يَقُولُ قَوْلاً، فَإِنْ شِئْتُمْ أَنْ نَعْرِضَهُ عَلَيْكُمْ فَعَلْنَا، فَقَالَ سُفَهَاؤُهُمْ لاَ حَاجَةَ لَنَا أَنْ تُخْبِرَنَا عَنْهُ بِشَىْءٍ‏.‏ وَقَالَ ذَوُو الرَّأْىِ مِنْهُمْ هَاتِ مَا سَمِعْتَهُ يَقُولُ‏.‏ قَالَ سَمِعْتُهُ يَقُولُ كَذَا وَكَذَا، فَحَدَّثَهُمْ بِمَا قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم‏.‏ فَقَامَ عُرْوَةُ بْنُ مَسْعُودٍ فَقَالَ أَىْ قَوْمِ أَلَسْتُمْ بِالْوَالِدِ قَالُوا بَلَى‏.‏ قَالَ أَوَلَسْتُ بِالْوَلَدِ قَالُوا بَلَى‏.‏ قَالَ فَهَلْ تَتَّهِمُونِي‏.‏ قَالُوا لاَ‏.‏ قَالَ أَلَسْتُمْ تَعْلَمُونَ أَنِّي اسْتَنْفَرْتُ أَهْلَ عُكَاظٍ، فَلَمَّا بَلَّحُوا عَلَىَّ جِئْتُكُمْ بِأَهْلِي وَوَلَدِي وَمَنْ أَطَاعَنِي قَالُوا بَلَى‏.‏ قَالَ فَإِنَّ هَذَا قَدْ عَرَضَ لَكُمْ خُطَّةَ رُشْدٍ، اقْبَلُوهَا وَدَعُونِي آتِهِ‏.‏ قَالُوا ائْتِهِ‏.‏ فَأَتَاهُ فَجَعَلَ يُكَلِّمُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم نَحْوًا مِنْ قَوْلِهِ لِبُدَيْلٍ، فَقَالَ عُرْوَةُ عِنْدَ ذَلِكَ أَىْ مُحَمَّدُ، أَرَأَيْتَ إِنِ اسْتَأْصَلْتَ أَمْرَ قَوْمِكَ هَلْ سَمِعْتَ بِأَحَدٍ مِنَ الْعَرَبِ اجْتَاحَ أَهْلَهُ قَبْلَكَ وَإِنْ تَكُنِ الأُخْرَى، فَإِنِّي وَاللَّهِ لأَرَى وُجُوهًا، وَإِنِّي لأَرَى أَوْشَابًا مِنَ النَّاسِ خَلِيقًا أَنْ يَفِرُّوا وَيَدَعُوكَ‏.‏ فَقَالَ لَهُ أَبُو بَكْرٍ امْصُصْ بَظْرَ اللاَّتِ، أَنَحْنُ نَفِرُّ عَنْهُ وَنَدَعُهُ فَقَالَ مَنْ ذَا قَالُوا أَبُو بَكْرٍ‏.‏ قَالَ أَمَا وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ لَوْلاَ يَدٌ كَانَتْ لَكَ عِنْدِي لَمْ أَجْزِكَ بِهَا لأَجَبْتُكَ‏.‏ قَالَ وَجَعَلَ يُكَلِّمُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم فَكُلَّمَا تَكَلَّمَ أَخَذَ بِلِحْيَتِهِ، وَالْمُغِيرَةُ بْنُ شُعْبَةَ قَائِمٌ عَلَى رَأْسِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم وَمَعَهُ السَّيْفُ وَعَلَيْهِ الْمِغْفَرُ، فَكُلَّمَا أَهْوَى عُرْوَةُ بِيَدِهِ إِلَى لِحْيَةِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم ضَرَبَ يَدَهُ بِنَعْلِ السَّيْفِ، وَقَالَ لَهُ أَخِّرْ يَدَكَ عَنْ لِحْيَةِ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم‏.‏ فَرَفَعَ عُرْوَةُ رَأْسَهُ فَقَالَ مَنْ هَذَا قَالُوا الْمُغِيرَةُ بْنُ شُعْبَةَ‏.‏ فَقَالَ أَىْ غُدَرُ، أَلَسْتُ أَسْعَى فِي غَدْرَتِكَ وَكَانَ الْمُغِيرَةُ صَحِبَ قَوْمًا فِي الْجَاهِلِيَّةِ، فَقَتَلَهُمْ، وَأَخَذَ أَمْوَالَهُمْ، ثُمَّ جَاءَ فَأَسْلَمَ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ أَمَّا الإِسْلاَمَ فَأَقْبَلُ، وَأَمَّا الْمَالَ فَلَسْتُ مِنْهُ فِي شَىْءٍ ‏”‏‏.‏ ثُمَّ إِنَّ عُرْوَةَ جَعَلَ يَرْمُقُ أَصْحَابَ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِعَيْنَيْهِ‏.‏ قَالَ فَوَاللَّهِ مَا تَنَخَّمَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم نُخَامَةً إِلاَّ وَقَعَتْ فِي كَفِّ رَجُلٍ مِنْهُمْ فَدَلَكَ بِهَا وَجْهَهُ وَجِلْدَهُ، وَإِذَا أَمَرَهُمُ ابْتَدَرُوا أَمْرَهُ، وَإِذَا تَوَضَّأَ كَادُوا يَقْتَتِلُونَ عَلَى وَضُوئِهِ، وَإِذَا تَكَلَّمَ خَفَضُوا أَصْوَاتَهُمْ عِنْدَهُ، وَمَا يُحِدُّونَ إِلَيْهِ النَّظَرَ تَعْظِيمًا لَهُ، فَرَجَعَ عُرْوَةُ إِلَى أَصْحَابِهِ، فَقَالَ أَىْ قَوْمِ، وَاللَّهِ لَقَدْ وَفَدْتُ عَلَى الْمُلُوكِ، وَوَفَدْتُ عَلَى قَيْصَرَ وَكِسْرَى وَالنَّجَاشِيِّ وَاللَّهِ إِنْ رَأَيْتُ مَلِكًا قَطُّ، يُعَظِّمُهُ أَصْحَابُهُ مَا يُعَظِّمُ أَصْحَابُ مُحَمَّدٍ صلى الله عليه وسلم مُحَمَّدًا، وَاللَّهِ إِنْ تَنَخَّمَ نُخَامَةً إِلاَّ وَقَعَتْ فِي كَفِّ رَجُلٍ مِنْهُمْ، فَدَلَكَ بِهَا وَجْهَهُ وَجِلْدَهُ، وَإِذَا أَمَرَهُمُ ابْتَدَرُوا أَمْرَهُ وَإِذَا تَوَضَّأَ كَادُوا يَقْتَتِلُونَ عَلَى وَضُوئِهِ، وَإِذَا تَكَلَّمَ خَفَضُوا أَصْوَاتَهُمْ عِنْدَهُ، وَمَا يُحِدُّونَ إِلَيْهِ النَّظَرَ تَعْظِيمًا لَهُ، وَإِنَّهُ قَدْ عَرَضَ عَلَيْكُمْ خُطَّةَ رُشْدٍ، فَاقْبَلُوهَا‏.‏ فَقَالَ رَجُلٌ مِنْ بَنِي كِنَانَةَ دَعُونِي آتِهِ‏.‏ فَقَالُوا ائْتِهِ‏.‏ فَلَمَّا أَشْرَفَ عَلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم وَأَصْحَابِهِ، قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ هَذَا فُلاَنٌ، وَهْوَ مِنْ قَوْمٍ يُعَظِّمُونَ الْبُدْنَ فَابْعَثُوهَا لَهُ ‏”‏‏.‏ فَبُعِثَتْ لَهُ وَاسْتَقْبَلَهُ النَّاسُ يُلَبُّونَ، فَلَمَّا رَأَى ذَلِكَ قَالَ سُبْحَانَ اللَّهِ مَا يَنْبَغِي لِهَؤُلاَءِ أَنْ يُصَدُّوا عَنِ الْبَيْتِ، فَلَمَّا رَجَعَ إِلَى أَصْحَابِهِ قَالَ رَأَيْتُ الْبُدْنَ قَدْ قُلِّدَتْ وَأُشْعِرَتْ، فَمَا أَرَى أَنْ يُصَدُّوا عَنِ الْبَيْتِ‏.‏ فَقَامَ رَجُلٌ مِنْهُمْ يُقَالُ لَهُ مِكْرَزُ بْنُ حَفْصٍ‏.‏ فَقَالَ دَعُونِي آتِهِ‏.‏ فَقَالُوا ائْتِهِ‏.‏ فَلَمَّا أَشْرَفَ عَلَيْهِمْ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ هَذَا مِكْرَزٌ وَهْوَ رَجُلٌ فَاجِرٌ ‏”‏‏.‏ فَجَعَلَ يُكَلِّمُ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم، فَبَيْنَمَا هُوَ يُكَلِّمُهُ إِذْ جَاءَ سُهَيْلُ بْنُ عَمْرٍو‏.‏ قَالَ مَعْمَرٌ فَأَخْبَرَنِي أَيُّوبُ عَنْ عِكْرِمَةَ، أَنَّهُ لَمَّا جَاءَ سُهَيْلُ بْنُ عَمْرٍو قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ لَقَدْ سَهُلَ لَكُمْ مِنْ أَمْرِكُمْ ‏”‏‏.‏ قَالَ مَعْمَرٌ قَالَ الزُّهْرِيُّ فِي حَدِيثِهِ فَجَاءَ سُهَيْلُ بْنُ عَمْرٍو فَقَالَ هَاتِ، اكْتُبْ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ كِتَابًا، فَدَعَا النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم الْكَاتِبَ، فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ ‏”‏‏.‏ قَالَ سُهَيْلٌ أَمَّا الرَّحْمَنُ فَوَاللَّهِ مَا أَدْرِي مَا هُوَ وَلَكِنِ اكْتُبْ بِاسْمِكَ اللَّهُمَّ‏.‏ كَمَا كُنْتَ تَكْتُبُ‏.‏ فَقَالَ الْمُسْلِمُونَ وَاللَّهِ لاَ نَكْتُبُهَا إِلاَّ بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ اكْتُبْ بِاسْمِكَ اللَّهُمَّ ‏”‏‏.‏ ثُمَّ قَالَ ‏”‏ هَذَا مَا قَاضَى عَلَيْهِ مُحَمَّدٌ رَسُولُ اللَّهِ ‏”‏‏.‏ فَقَالَ سُهَيْلٌ وَاللَّهِ لَوْ كُنَّا نَعْلَمُ أَنَّكَ رَسُولُ اللَّهِ مَا صَدَدْنَاكَ عَنِ الْبَيْتِ وَلاَ قَاتَلْنَاكَ، وَلَكِنِ اكْتُبْ مُحَمَّدُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ وَاللَّهِ إِنِّي لَرَسُولُ اللَّهِ وَإِنْ كَذَّبْتُمُونِي‏.‏ اكْتُبْ مُحَمَّدُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ ‏”‏‏.‏ قَالَ الزُّهْرِيُّ وَذَلِكَ لِقَوْلِهِ ‏”‏ لاَ يَسْأَلُونِي خُطَّةً يُعَظِّمُونَ فِيهَا حُرُمَاتِ اللَّهِ إِلاَّ أَعْطَيْتُهُمْ إِيَّاهَا ‏”‏‏.‏ فَقَالَ لَهُ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ عَلَى أَنْ تُخَلُّوا بَيْنَنَا وَبَيْنَ الْبَيْتِ فَنَطُوفَ بِهِ ‏”‏‏.‏ فَقَالَ سُهَيْلٌ وَاللَّهِ لاَ تَتَحَدَّثُ الْعَرَبُ أَنَّا أُخِذْنَا ضُغْطَةً وَلَكِنْ ذَلِكَ مِنَ الْعَامِ الْمُقْبِلِ فَكَتَبَ‏.‏ فَقَالَ سُهَيْلٌ وَعَلَى أَنَّهُ لاَ يَأْتِيكَ مِنَّا رَجُلٌ، وَإِنْ كَانَ عَلَى دِينِكَ، إِلاَّ رَدَدْتَهُ إِلَيْنَا‏.‏ قَالَ الْمُسْلِمُونَ سُبْحَانَ اللَّهِ كَيْفَ يُرَدُّ إِلَى الْمُشْرِكِينَ وَقَدْ جَاءَ مُسْلِمًا فَبَيْنَمَا هُمْ كَذَلِكَ إِذْ دَخَلَ أَبُو جَنْدَلِ بْنُ سُهَيْلِ بْنِ عَمْرٍو يَرْسُفُ فِي قُيُودِهِ، وَقَدْ خَرَجَ مِنْ أَسْفَلِ مَكَّةَ، حَتَّى رَمَى بِنَفْسِهِ بَيْنَ أَظْهُرِ الْمُسْلِمِينَ‏.‏ فَقَالَ سُهَيْلٌ هَذَا يَا مُحَمَّدُ أَوَّلُ مَا أُقَاضِيكَ عَلَيْهِ أَنْ تَرُدَّهُ إِلَىَّ‏.‏ فَقَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ إِنَّا لَمْ نَقْضِ الْكِتَابَ بَعْدُ ‏”‏‏.‏ قَالَ فَوَاللَّهِ إِذًا لَمْ أُصَالِحْكَ عَلَى شَىْءٍ أَبَدًا‏.‏ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ فَأَجِزْهُ لِي ‏”‏‏.‏ قَالَ مَا أَنَا بِمُجِيزِهِ لَكَ‏.‏ قَالَ ‏”‏ بَلَى، فَافْعَلْ ‏”‏‏.‏ قَالَ مَا أَنَا بِفَاعِلٍ‏.‏ قَالَ مِكْرَزٌ بَلْ قَدْ أَجَزْنَاهُ لَكَ‏.‏ قَالَ أَبُو جَنْدَلٍ أَىْ مَعْشَرَ الْمُسْلِمِينَ، أُرَدُّ إِلَى الْمُشْرِكِينَ وَقَدْ جِئْتُ مُسْلِمًا أَلاَ تَرَوْنَ مَا قَدْ لَقِيتُ وَكَانَ قَدْ عُذِّبَ عَذَابًا شَدِيدًا فِي اللَّهِ‏.‏ قَالَ فَقَالَ عُمَرُ بْنُ الْخَطَّابِ فَأَتَيْتُ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ أَلَسْتَ نَبِيَّ اللَّهِ حَقًّا قَالَ ‏”‏ بَلَى ‏”‏‏.‏ قُلْتُ أَلَسْنَا عَلَى الْحَقِّ وَعَدُوُّنَا عَلَى الْبَاطِلِ قَالَ ‏”‏ بَلَى ‏”‏‏.‏ قُلْتُ فَلِمَ نُعْطِي الدَّنِيَّةَ فِي دِينِنَا إِذًا قَالَ ‏”‏ إِنِّي رَسُولُ اللَّهِ، وَلَسْتُ أَعْصِيهِ وَهْوَ نَاصِرِي ‏”‏‏.‏ قُلْتُ أَوَلَيْسَ كُنْتَ تُحَدِّثُنَا أَنَّا سَنَأْتِي الْبَيْتَ فَنَطُوفُ بِهِ قَالَ ‏”‏ بَلَى، فَأَخْبَرْتُكَ أَنَّا نَأْتِيهِ الْعَامَ ‏”‏‏.‏ قَالَ قُلْتُ لاَ‏.‏ قَالَ ‏”‏ فَإِنَّكَ آتِيهِ وَمُطَّوِّفٌ بِهِ ‏”‏‏.‏ قَالَ فَأَتَيْتُ أَبَا بَكْرٍ فَقُلْتُ يَا أَبَا بَكْرٍ، أَلَيْسَ هَذَا نَبِيَّ اللَّهِ حَقًّا قَالَ بَلَى‏.‏ قُلْتُ أَلَسْنَا عَلَى الْحَقِّ وَعَدُوُّنَا عَلَى الْبَاطِلِ قَالَ بَلَى‏.‏ قُلْتُ فَلِمَ نُعْطِي الدَّنِيَّةَ فِي دِينِنَا إِذًا قَالَ أَيُّهَا الرَّجُلُ، إِنَّهُ لَرَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم وَلَيْسَ يَعْصِي رَبَّهُ وَهْوَ نَاصِرُهُ، فَاسْتَمْسِكْ بِغَرْزِهِ، فَوَاللَّهِ إِنَّهُ عَلَى الْحَقِّ‏.‏ قُلْتُ أَلَيْسَ كَانَ يُحَدِّثُنَا أَنَّا سَنَأْتِي الْبَيْتَ وَنَطُوفُ بِهِ قَالَ بَلَى، أَفَأَخْبَرَكَ أَنَّكَ تَأْتِيهِ الْعَامَ قُلْتُ لاَ‏.‏ قَالَ فَإِنَّكَ آتِيهِ وَمُطَّوِّفٌ بِهِ‏.‏ قَالَ الزُّهْرِيِّ قَالَ عُمَرُ فَعَمِلْتُ لِذَلِكَ أَعْمَالاً‏.‏ قَالَ فَلَمَّا فَرَغَ مِنْ قَضِيَّةِ الْكِتَابِ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لأَصْحَابِهِ ‏”‏ قُومُوا فَانْحَرُوا، ثُمَّ احْلِقُوا ‏”‏‏.‏ قَالَ فَوَاللَّهِ مَا قَامَ مِنْهُمْ رَجُلٌ حَتَّى قَالَ ذَلِكَ ثَلاَثَ مَرَّاتٍ، فَلَمَّا لَمْ يَقُمْ مِنْهُمْ أَحَدٌ دَخَلَ عَلَى أُمِّ سَلَمَةَ، فَذَكَرَ لَهَا مَا لَقِيَ مِنَ النَّاسِ‏.‏ فَقَالَتْ أُمُّ سَلَمَةَ يَا نَبِيَّ اللَّهِ، أَتُحِبُّ ذَلِكَ اخْرُجْ ثُمَّ لاَ تُكَلِّمْ أَحَدًا مِنْهُمْ كَلِمَةً حَتَّى تَنْحَرَ بُدْنَكَ، وَتَدْعُوَ حَالِقَكَ فَيَحْلِقَكَ‏.‏ فَخَرَجَ فَلَمْ يُكَلِّمْ أَحَدًا مِنْهُمْ، حَتَّى فَعَلَ ذَلِكَ نَحَرَ بُدْنَهُ، وَدَعَا حَالِقَهُ فَحَلَقَهُ‏.‏ فَلَمَّا رَأَوْا ذَلِكَ، قَامُوا فَنَحَرُوا، وَجَعَلَ بَعْضُهُمْ يَحْلِقُ بَعْضًا، حَتَّى كَادَ بَعْضُهُمْ يَقْتُلُ بَعْضًا غَمًّا، ثُمَّ جَاءَهُ نِسْوَةٌ مُؤْمِنَاتٌ فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا إِذَا جَاءَكُمُ الْمُؤْمِنَاتُ مُهَاجِرَاتٍ فَامْتَحِنُوهُنَّ‏}‏ حَتَّى بَلَغَ ‏{‏بِعِصَمِ الْكَوَافِرِ‏}‏ فَطَلَّقَ عُمَرُ يَوْمَئِذٍ امْرَأَتَيْنِ كَانَتَا لَهُ فِي الشِّرْكِ، فَتَزَوَّجَ إِحْدَاهُمَا مُعَاوِيَةُ بْنُ أَبِي سُفْيَانَ، وَالأُخْرَى صَفْوَانُ بْنُ أُمَيَّةَ، ثُمَّ رَجَعَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَى الْمَدِينَةِ، فَجَاءَهُ أَبُو بَصِيرٍ ـ رَجُلٌ مِنْ قُرَيْشٍ ـ وَهْوَ مُسْلِمٌ فَأَرْسَلُوا فِي طَلَبِهِ رَجُلَيْنِ، فَقَالُوا الْعَهْدَ الَّذِي جَعَلْتَ لَنَا‏.‏ فَدَفَعَهُ إِلَى الرَّجُلَيْنِ، فَخَرَجَا بِهِ حَتَّى بَلَغَا ذَا الْحُلَيْفَةِ، فَنَزَلُوا يَأْكُلُونَ مِنْ تَمْرٍ لَهُمْ، فَقَالَ أَبُو بَصِيرٍ لأَحَدِ الرَّجُلَيْنِ وَاللَّهِ إِنِّي لأَرَى سَيْفَكَ هَذَا يَا فُلاَنُ جَيِّدًا‏.‏ فَاسْتَلَّهُ الآخَرُ فَقَالَ أَجَلْ، وَاللَّهِ إِنَّهُ لَجَيِّدٌ، لَقَدْ جَرَّبْتُ بِهِ ثُمَّ جَرَّبْتُ‏.‏ فَقَالَ أَبُو بَصِيرٍ أَرِنِي أَنْظُرْ إِلَيْهِ، فَأَمْكَنَهُ مِنْهُ، فَضَرَبَهُ حَتَّى بَرَدَ، وَفَرَّ الآخَرُ، حَتَّى أَتَى الْمَدِينَةَ، فَدَخَلَ الْمَسْجِدَ يَعْدُو‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم حِينَ رَآهُ ‏”‏ لَقَدْ رَأَى هَذَا ذُعْرًا ‏”‏‏.‏ فَلَمَّا انْتَهَى إِلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم قَالَ قُتِلَ وَاللَّهِ صَاحِبِي وَإِنِّي لَمَقْتُولٌ، فَجَاءَ أَبُو بَصِيرٍ فَقَالَ يَا نَبِيَّ اللَّهِ، قَدْ وَاللَّهِ أَوْفَى اللَّهُ ذِمَّتَكَ، قَدْ رَدَدْتَنِي إِلَيْهِمْ ثُمَّ أَنْجَانِي اللَّهُ مِنْهُمْ‏.‏ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏”‏ وَيْلُ أُمِّهِ مِسْعَرَ حَرْبٍ، لَوْ كَانَ لَهُ أَحَدٌ ‏”‏‏.‏ فَلَمَّا سَمِعَ ذَلِكَ عَرَفَ أَنَّهُ سَيَرُدُّهُ إِلَيْهِمْ، فَخَرَجَ حَتَّى أَتَى سِيفَ الْبَحْرِ‏.‏ قَالَ وَيَنْفَلِتُ مِنْهُمْ أَبُو جَنْدَلِ بْنُ سُهَيْلٍ، فَلَحِقَ بِأَبِي بَصِيرٍ، فَجَعَلَ لاَ يَخْرُجُ مِنْ قُرَيْشٍ رَجُلٌ قَدْ أَسْلَمَ إِلاَّ لَحِقَ بِأَبِي بَصِيرٍ، حَتَّى اجْتَمَعَتْ مِنْهُمْ عِصَابَةٌ، فَوَاللَّهِ مَا يَسْمَعُونَ بِعِيرٍ خَرَجَتْ لِقُرَيْشٍ إِلَى الشَّأْمِ إِلاَّ اعْتَرَضُوا لَهَا، فَقَتَلُوهُمْ، وَأَخَذُوا أَمْوَالَهُمْ، فَأَرْسَلَتْ قُرَيْشٌ إِلَى النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم تُنَاشِدُهُ بِاللَّهِ وَالرَّحِمِ لَمَّا أَرْسَلَ، فَمَنْ أَتَاهُ فَهْوَ آمِنٌ، فَأَرْسَلَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَيْهِمْ، فَأَنْزَلَ اللَّهُ تَعَالَى ‏{‏وَهُوَ الَّذِي كَفَّ أَيْدِيَهُمْ عَنْكُمْ وَأَيْدِيَكُمْ عَنْهُمْ بِبَطْنِ مَكَّةَ مِنْ بَعْدِ أَنْ أَظْفَرَكُمْ عَلَيْهِمْ‏}‏ حَتَّى بَلَغَ ‏{‏الْحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ‏}‏ وَكَانَتْ حَمِيَّتُهُمْ أَنَّهُمْ لَمْ يُقِرُّوا أَنَّهُ نَبِيُّ اللَّهِ، وَلَمْ يُقِرُّوا بِبِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ، وَحَالُوا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ الْبَيْتِ‏.

Narrated Al-Miswar bin Makhrama and Marwan:

(whose narrations attest each other) Allah’s Messenger (ﷺ) set out at the time of Al-Hudaibiya (treaty), and when they proceeded for a distance, he said, “Khalid bin Al-Walid leading the cavalry of Quraish constituting the front of the army, is at a place called Al-Ghamim, so take the way on the right.” By Allah, Khalid did not perceive the arrival of the Muslims till the dust arising from the march of the Muslim army reached him, and then he turned back hurriedly to inform Quraish. The Prophet (ﷺ) went on advancing till he reached the Thaniya (i.e. a mountainous way) through which one would go to them (i.e. people of Quraish). The she-camel of the Prophet (ﷺ) sat down. The people tried their best to cause the she-camel to get up but in vain, so they said, “Al-Qaswa’ (i.e. the she-camel’s name) has become stubborn! Al-Qaswa’ has become stubborn!” The Prophet (ﷺ) said, “Al-Qaswa’ has not become stubborn, for stubbornness is not her habit, but she was stopped by Him Who stopped the elephant.” Then he said, “By the Name of Him in Whose Hands my soul is, if they (i.e. the Quraish infidels) ask me anything which will respect the ordinances of Allah, I will grant it to them.” The Prophet (ﷺ) then rebuked the she-camel and she got up. The Prophet (ﷺ) changed his way till he dismounted at the farthest end of Al-Hudaibiya at a pit (i.e. well) containing a little water which the people used in small amounts, and in a short while the people used up all its water and complained to Allah’s Messenger (ﷺ); of thirst. The Prophet (ﷺ) took an arrow out of his arrow-case and ordered them to put the arrow in that pit. By Allah, the water started and continued sprouting out till all the people quenched their thirst and returned with satisfaction. While they were still in that state, Budail bin Warqa-al- Khuza`i came with some persons from his tribe Khuza`a and they were the advisers of Allah’s Messenger (ﷺ) who would keep no secret from him and were from the people of Tihama. Budail said, “I left Ka`b bin Luai and ‘Amir bin Luai residing at the profuse water of Al-Hudaibiya and they had milch camels (or their women and children) with them, and will wage war against you, and will prevent you from visiting the Ka`ba.” Allah’s Messenger (ﷺ) said, “We have not come to fight anyone, but to perform the `Umra. No doubt, the war has weakened Quraish and they have suffered great losses, so if they wish, I will conclude a truce with them, during which they should refrain from interfering between me and the people (i.e. the ‘Arab infidels other than Quraish), and if I have victory over those infidels, Quraish will have the option to embrace Islam as the other people do, if they wish; they will at least get strong enough to fight. But if they do not accept the truce, by Allah in Whose Hands my life is, I will fight with them defending my Cause till I get killed, but (I am sure) Allah will definitely make His Cause victorious.” Budail said, “I will inform them of what you have said.” So, he set off till he reached Quraish and said, “We have come from that man (i.e. Muhammad) whom we heard saying something which we will disclose to you if you should like.” Some of the fools among Quraish shouted that they were not in need of this information, but the wiser among them said, “Relate what you heard him saying.” Budail said, “I heard him saying so-and-so,” relating what the Prophet (ﷺ) had told him. `Urwa bin Mas`ud got up and said, “O people! Aren’t you the sons? They said, “Yes.” He added, “Am I not the father?” They said, “Yes.” He said, “Do you mistrust me?” They said, “No.” He said, “Don’t you know that I invited the people of `Ukaz for your help, and when they refused I brought my relatives and children and those who obeyed me (to help you)?” They said, “Yes.” He said, “Well, this man (i.e. the Prophet) has offered you a reasonable proposal, you’d better accept it and allow me to meet him.” They said, “You may meet him.” So, he went to the Prophet (ﷺ) and started talking to him. The Prophet (ﷺ) told him almost the same as he had told Budail. Then `Urwa said, “O Muhammad! Won’t you feel any scruple in extirpating your relations? Have you ever heard of anyone amongst the Arabs extirpating his relatives before you? On the other hand, if the reverse should happen, (nobody will aid you, for) by Allah, I do not see (with you) dignified people, but people from various tribes who would run away leaving you alone.” Hearing that, Abu Bakr abused him and said, “Do you say we would run and leave the Prophet (ﷺ) alone?” `Urwa said, “Who is that man?” They said, “He is Abu Bakr.” `Urwa said to Abu Bakr, “By Him in Whose Hands my life is, were it not for the favor which you did to me and which I did not compensate, I would retort on you.” `Urwa kept on talking to the Prophet (ﷺ) and seizing the Prophet’s beard as he was talking while Al-Mughira bin Shu`ba was standing near the head of the Prophet, holding a sword and wearing a helmet. Whenever `Urwa stretched his hand towards the beard of the Prophet, Al-Mughira would hit his hand with the handle of the sword and say (to `Urwa), “Remove your hand from the beard of Allah’s Messenger (ﷺ).” `Urwa raised his head and asked, “Who is that?” The people said, “He is Al-Mughira bin Shu`ba.” `Urwa said, “O treacherous! Am I not doing my best to prevent evil consequences of your treachery?” Before embracing Islam Al-Mughira was in the company of some people. He killed them and took their property and came (to Medina) to embrace Islam. The Prophet (ﷺ) said (to him, “As regards your Islam, I accept it, but as for the property I do not take anything of it. (As it was taken through treason). `Urwa then started looking at the Companions of the Prophet. By Allah, whenever Allah’s Messenger (ﷺ) spat, the spittle would fall in the hand of one of them (i.e. the Prophet’s companions) who would rub it on his face and skin; if he ordered them they would carry his orders immediately; if he performed ablution, they would struggle to take the remaining water; and when they spoke to him, they would lower their voices and would not look at his face constantly out of respect. `Urwa returned to his people and said, “O people! By Allah, I have been to the kings and to Caesar, Khosrau and An- Najashi, yet I have never seen any of them respected by his courtiers as much as Muhammad is respected by his companions. By Allah, if he spat, the spittle would fall in the hand of one of them (i.e. the Prophet’s companions) who would rub it on his face and skin; if he ordered them, they would carry out his order immediately; if he performed ablution, they would struggle to take the remaining water; and when they spoke, they would lower their voices and would not look at his face constantly out of respect.” `Urwa added, “No doubt, he has presented to you a good reasonable offer, so please accept it.” A man from the tribe of Bani Kinana said, “Allow me to go to him,” and they allowed him, and when he approached the Prophet and his companions, Allah’s Messenger (ﷺ) said, “He is so-and-so who belongs to the tribe that respects the Budn (i.e. camels of the sacrifice). So, bring the Budn in front of him.” So, the Budn were brought before him and the people received him while they were reciting Talbiya. When he saw that scene, he said, “Glorified be Allah! It is not fair to prevent these people from visiting the Ka`ba.” When he returned to his people, he said, ‘I saw the Budn garlanded (with colored knotted ropes) and marked (with stabs on their backs). I do not think it is advisable to prevent them from visiting the Ka`ba.” Another person called Mikraz bin Hafs got up and sought their permission to go to Muhammad, and they allowed him, too. When he approached the Muslims, the Prophet (ﷺ) said, “Here is Mikraz and he is a vicious man.” Mikraz started talking to the Prophet and as he was talking, Suhail bin `Amr came. When Suhail bin `Amr came, the Prophet (ﷺ) said, “Now the matter has become easy.” Suhail said to the Prophet “Please conclude a peace treaty with us.” So, the Prophet (ﷺ) called the clerk and said to him, “Write: By the Name of Allah, the most Beneficent, the most Merciful.” Suhail said, “As for ‘Beneficent,’ by Allah, I do not know what it means. So write: By Your Name O Allah, as you used to write previously.” The Muslims said, “By Allah, we will not write except: By the Name of Allah, the most Beneficent, the most Merciful.” The Prophet (ﷺ) said, “Write: By Your Name O Allah.” Then he dictated, “This is the peace treaty which Muhammad, Allah’s Messenger (ﷺ) has concluded.” Suhail said, “By Allah, if we knew that you are Allah’s Messenger (ﷺ) we would not prevent you from visiting the Ka`ba, and would not fight with you. So, write: “Muhammad bin `Abdullah.” The Prophet (ﷺ) said, “By Allah! I am Apostle of Allah even if you people do not believe me. Write: Muhammad bin `Abdullah.” (Az-Zuhri said, “The Prophet (ﷺ) accepted all those things, as he had already said that he would accept everything they would demand if it respects the ordinance of Allah, (i.e. by letting him and his companions perform `Umra.)” The Prophet (ﷺ) said to Suhail, “On the condition that you allow us to visit the House (i.e. Ka`ba) so that we may perform Tawaf around it.” Suhail said, “By Allah, we will not (allow you this year) so as not to give chance to the ‘Arabs to say that we have yielded to you, but we will allow you next year.” So, the Prophet (ﷺ) got that written. Then Suhail said, “We also stipulate that you should return to us whoever comes to you from us, even if he embraced your religion.” The Muslims said, “Glorified be Allah! How will such a person be returned to the pagans after he has become a Muslim? While they were in this state Abu- Jandal bin Suhail bin `Amr came from the valley of Mecca staggering with his fetters and fell down amongst the Muslims. Suhail said, “O Muhammad! This is the very first term with which we make peace with you, i.e. you shall return Abu Jandal to me.” The Prophet (ﷺ) said, “The peace treaty has not been written yet.” Suhail said, “I will never allow you to keep him.” The Prophet (ﷺ) said, “Yes, do.” He said, “I won’t do.: Mikraz said, “We allow you (to keep him).” Abu Jandal said, “O Muslims! Will I be returned to the pagans though I have come as a Muslim? Don’t you see how much I have suffered?” (continued…) (continuing… 1): -3.891:… … Abu Jandal had been tortured severely for the Cause of Allah. `Umar bin Al-Khattab said, “I went to the Prophet (ﷺ) and said, ‘Aren’t you truly the Messenger of Allah?’ The Prophet (ﷺ) said, ‘Yes, indeed.’ I said, ‘Isn’t our Cause just and the cause of the enemy unjust?’ He said, ‘Yes.’ I said, ‘Then why should we be humble in our religion?’ He said, ‘I am Allah’s Messenger (ﷺ) and I do not disobey Him, and He will make me victorious.’ I said, ‘Didn’t you tell us that we would go to the Ka`ba and perform Tawaf around it?’ He said, ‘Yes, but did I tell you that we would visit the Ka`ba this year?’ I said, ‘No.’ He said, ‘So you will visit it and perform Tawaf around it?’ ” `Umar further said, “I went to Abu Bakr and said, ‘O Abu Bakr! Isn’t he truly Allah’s Prophet?’ He replied, ‘Yes.’ I said, ‘Then why should we be humble in our religion?’ He said, ‘Indeed, he is Allah’s Messenger (ﷺ) and he does not disobey his Lord, and He will make him victorious. Adhere to him as, by Allah, he is on the right.’ I said, ‘Was he not telling us that we would go to the Ka`ba and perform Tawaf around it?’ He said, ‘Yes, but did he tell you that you would go to the Ka`ba this year?’ I said, ‘No.’ He said, “You will go to Ka`ba and perform Tawaf around it.” (Az-Zuhri said, ” `Umar said, ‘I performed many good deeds as expiation for the improper questions I asked them.’ “) When the writing of the peace treaty was concluded, Allah’s Messenger (ﷺ) said to his companions, “Get up and’ slaughter your sacrifices and get your head shaved.” By Allah none of them got up, and the Prophet repeated his order thrice. When none of them got up, he left them and went to Um Salama and told her of the people’s attitudes towards him. Um Salama said, “O the Prophet (ﷺ) of Allah! Do you want your order to be carried out? Go out and don’t say a word to anybody till you have slaughtered your sacrifice and call your barber to shave your head.” So, the Prophet (ﷺ) went out and did not talk to anyone of them till he did that, i.e. slaughtered the sacrifice and called his barber who shaved his head. Seeing that, the companions of the Prophet (ﷺ) got up, slaughtered their sacrifices, and started shaving the heads of one another, and there was so much rush that there was a danger of killing each other. Then some believing women came (to the Prophet (ﷺ) ); and Allah revealed the following Divine Verses:– “O you who believe, when the believing women come to you as emigrants examine them . . .” (60.10) `Umar then divorced two wives of his who were infidels. Later on Muawiya bin Abu Sufyan married one of them, and Safwan bin Umaiya married the other. When the Prophet (ﷺ) returned to Medina, Abu Basir, a new Muslim convert from Quraish came to him. The Infidels sent in his pursuit two men who said (to the Prophet (ﷺ) ), “Abide by the promise you gave us.” So, the Prophet (ﷺ) handed him over to them. They took him out (of the City) till they reached Dhul-Hulaifa where they dismounted to eat some dates they had with them. Abu Basir said to one of them, “By Allah, O so-and-so, I see you have a fine sword.” The other drew it out (of the scabbard) and said, “By Allah, it is very fine and I have tried it many times.” Abu Basir said, “Let me have a look at it.” When the other gave it to him, he hit him with it till he died, and his companion ran away till he came to Medina and entered the Mosque running. When Allah’s Messenger (ﷺ) saw him he said, “This man appears to have been frightened.” When he reached the Prophet (ﷺ) he said, “My companion has been murdered and I would have been murdered too.” Abu Basir came and said, “O Allah’s Messenger (ﷺ), by Allah, Allah has made you fulfill your obligations by your returning me to them (i.e. the Infidels), but Allah has saved me from them.” The Prophet (ﷺ) said, “Woe to his mother! what excellent war kindler he would be, should he only have supporters.” When Abu Basir heard that he understood that the Prophet (ﷺ) would return him to them again, so he set off till he reached the seashore. Abu Jandal bin Suhail got himself released from them (i.e. infidels) and joined Abu Basir. So, whenever a man from Quraish embraced Islam he would follow Abu Basir till they formed a strong group. By Allah, whenever they heard about a caravan of Quraish heading towards Sham, they stopped it and attacked and killed them (i.e. infidels) and took their properties. The people of Quraish sent a message to the Prophet (ﷺ) requesting him for the Sake of Allah and Kith and kin to send for (i.e. Abu Basir and his companions) promising that whoever (amongst them) came to the Prophet (ﷺ) would be secure. So the Prophet (ﷺ) sent for them (i.e. Abu Basir’s companions) and Allah I revealed the following Divine Verses: “And it is He Who Has withheld their hands from you and your hands From them in the midst of Mecca, After He made you the victorious over them. … the unbelievers had pride and haughtiness, in their hearts … the pride and haughtiness of the time of ignorance.” (48.24-26) And their pride and haughtiness was that they did not confess (write in the treaty) that he (i.e. Muhammad) was the Prophet of Allah and refused to write: “In the Name of Allah, the most Beneficent, the Most Merciful,” and they (the mushriks) prevented them (the Muslims) from visiting the House (the Ka`bah).

Reference: Sahih al-Bukhari 2731, 2732

In-book reference: Book 54, Hadith 19

USC-MSA web (English) reference : Vol. 3, Book 50, Hadith 891 (deprecated numbering scheme)

 

አስገራሚ እስላማዊ ሐዲሳት