በቁርኣን ወይም በኢስላም ስንት ፈጣሪ ነው ያለው?

በቁርኣን ወይም በኢስላም ስንት ፈጣሪ ነው ያለው?

ዘላለም መንግሥቱ


ሱራ 23 (ሱረቱ አል ሙእሚኑን) ቁጥር 14 እንዲህ ይላል፦

“ከዚያም ጠብታዋን (በአርባ ቀን) የረጋ ደም አድርገን ፈጠርን። የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ፈጠርን። ቁራጭዋንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ፈጠርን። አጥንቶቹንም ሥጋን አለበስናቸው። ከዚያም (ነፍስን በመዝራት) ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው። ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ።”

በዚህ ጥቅስ ውስጥ፥ ‘ፈጠርን’ የሚለው ቃል ሦስት ጊዜ ተደጋግሞ ተጽፎአል። ወደ አፈጣጠሩ ሂደት ውስጥ አልገባም። ያ በራሱ ጥያቄ የሚሆን ነገር ነው። በቅንፍ ውስጥ የሚገኙት ቃላት የተጨመሩ ናቸው። አርባ ቀን እና ነፍስ በመዝራት የሚሉት የሌሉና የተጨመሩ ናቸው። ይህንንም እንተወው። እዚህ ጥያቄ ወደሚሆነው አሳብ የሚወስደን፥ ‘ፈጠርን’ (ኸለቅና፥ እና ፈኸለቅና) የሚለው ቃል ነው። ቃሉ መፍጠር ነው።

ለንጽጽር እንዲረዳን ከብዙ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች አንዱን ብቻ ብናይ እንዲህ ይላል፤

Then We made the sperm-drop into a clinging clot, and We made the clot into a lump [of flesh], and We made [from] the lump, bones, and We covered the bones with flesh; then We developed him into another creation. So blessed is Allah , the best of creators.

የመጨረሻዎቹን ሐረጎች ነው እንድናስተያይ የፈለግሁትና ጥያቄዬም የሆነው። እንግሊዝኛው፥ So blessed is Allah , the best of creators. ይላል። አማርኛው፥ ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ። ይላል። ከእንግሊዝኛው ጋር ለማስታረቅ ወይም ለማጣላት ሳይሆን ከላይ ያየናቸው፥ ‘ፈጠርን’ ያለበት ቃል ነው በአማርኛው፥’ ከፈጣሪዎች ሁሉ በላጭ’ ሳይሆን፥ ‘ከሰዓሊዎች ሁሉ በላጭ’ ተብሎ የተተረጎመው። ‘አላሁ አህሰኑ አልኻሊቂን’ የሚለው ኸለቅና (ፈጠርን) የሚለው ግስ ምንጩ የሆነው የአድራጊነት ቃል ነው።

ከሰዓሊዎችም ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ?

ምንም የስዕል ውድድር የለምና አላህ ለምን ከሰዓሊዎች በለጠ? ከፈጣሪዎች ላለማለት ነው ከሰዓሊዎች የተደረገው? ወይም ከላይ ያሉትንም ሐረጎች፥ የረጋ ደም አድርገን ሳልን። የረጋውንም ደም ቁራጭ ሥጋ አድርገን ሳልን። ቁራጭዋንም ሥጋ አጥንቶች አድርገን ሳልን። ብሎ አላህ ከሰዓሊዎች ቢበልጥ አንድ ነገር ነው። ያም ሆኖ ሌሎች ሰዓሊዎችም አሉ ማለት ነው ወይ? የሚል ጥያቄ ያስከትላል። እዚህ ግን ቃሉ መፍጠር ነው። አላህም ከፈጣሪዎች በላጭ ነው።

ጥያቄው፥ ስንት ፈጣሪዎች ናቸው ያሉት? ዒሳ ፈጣሪ መሆኑ፥ ወይም መፍጠሩ በቁርኣን ውስጥ ተጽፎአል (3፥49) ያ በአላህ ፈቃድ ሊባል ይቻላል፤ ያም ሆኖ ፈጥሮአልና ከፈጣሪ ተርታ ይመደባል። አላህ ፈጣሪ ነው፤ ዒሳም ፈጥሮአል፤ ሌላስ ፈጣሪ አለ ወይ? አላህ ለምንና እንዴት ከፈጣሪዎች በላጭ ሆነ?

ይህንን ጥቅስ በተመለከተ ሙስሊሞች ከግንዛቤ ውስጥ ሊያስገቡት የሚገባው ሌላው ጉዳይ በእስላማዊ ምንጮች ውስጥ በግልጽ እንደተጻፈው የጥቅሱ መቋጫ የሆነው ይህ አባባል መጀመርያ አላህ ለሙሐመድ “ያወረደው ንግግር አካል እንዳልነበረ ነው። አባባሉ የሙሐመድ ሳይሆን የዑመር አል-ኸጧብ ቃል እንደሆነ የሚያሳዩ ማስረጃዎ አሉ። ሙሐመድ ጥቅሱን የጨረሰው “ሌላ ፍጥረት አድርገን አስገኘነው” በሚለው ላይ እንደነበርና ነገር ግን ዑመር “ከፈጣሪዎች ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ” ብሎ በመደነቅ ሲናግር ሰምቶ እንደጨመረው የጥቅሱ አስባብ እንዲህ ይነግረናል፦

(So blessed be Allah, the Best of creators!) [23:14]. Ahmad ibn Muhammad ibn ‘Abd Allah al-Hafiz informed us> ‘Abd Allah ibn Muhammad ibn Hayyan> Muhammad ibn Sulayman> Ahmad ibn ‘Abd Allah ibn Suwayd ibn Manjuf> Abu Dawud> Hammad ibn Salamah> ‘Ali ibn Zayd ibn Jud‘an> Anas ibn Malik who reported that ‘Umar ibn al-Khattab, may Allah be well pleased with him, said: “My words agreed with those of my Lord in four instances. I said: ‘O Messenger of Allah, why do we not pray behind the Maqam [were Abraham stood to pray]’, and Allah, exalted is He, revealed (… Take as your place of worship the place where Abraham stood (to pray)…) [2:125]. And I said: ‘O Messenger of Allah, why do you not put a curtain [to protect your wives from the gaze of men]?’ And so Allah, exalted is He, revealed: (And when ye ask of them (the wives of the Prophet) anything, ask it of them from behind a curtain…) [33:53]. I also said to the wives of the Prophet, Allah bless him and give him peace: ‘You had better take heed or Allah, glorious is He, will give the Prophet instead of you wives who are better than you’. And so Allah, exalted is He, revealed (It may happen that his Lord, if he divorce you, will give him in your stead wives better than you) [66:5]. And when the verse (Verily We created man from a product of wet earth) [23:12] up to His words (… and the produced it as another creation) [23:14] were revealed, I exclaimed: ‘So blessed be Allah, the Best of creators!’ and the end of the verse was revealed as: (So blessed be Allah, the Best of creators!)’ ”.

አሕመድ ኢብኑ ሙሐመድ ኢብኑ ዐብዱላህ አል-ሐፊዝ እንደነገሩን፤ አነስ ኢብኑ ማሊክ እንደዘገበው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ (ረዲአላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፡- “ቃሌ ከጌታዬ ጋር በአራት ጉዳዮች ተስማምቷል። እንዲህ ብዬ ነበር፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ ከመ ጀርባ ሆነን ለምን አንሰግድም? (አብረሃም ለመስገድ የቆመበት ስፍራ)። የተከበረው አላህ ይህንን አወረደ፦ (…ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ..) [2፡125]። እኔም እንዲህ ብዬ ነበር፡- የአላህ መልእክተኛ ሆይ (ሚስቶችህን ከሰዎች ዕይታ ለመጠበቅ) ለምን መጋረጃ አታደርግም?” ከዚያም የተከበረው አላህ እንዲህ የሚል አወረደ፦ (ዕቃንም (ለመዋስ) በጠየቃችኋቸው ጊዜ ከመጋረጃ ኋላ ኾናችሁ ጠይቋቸው…) [33:53]። እኔም ለነብዩ ሚስቶች እንዲህ አልኳቸው፡- “ብትጠነቀቁ ይሻላችኋል ወይም የተከበረው አላህ ከናንተ የሚበልጡ ሚስቶችን በምትኩ ለነቢዩን ይሰጠዋል።” ከዚያም የተከበረው አላህ ይህንን አወረደ፦ (ቢፈታችሁ ከእናንተ የበለጡ ሚስቶችን … ጌታው ሊለውጠው ይከጀላል( [66፡5]። (በእርግጥም ሰውን ከነጠረ ጭቃ ፈጠርነው) [23፡12] የሚለው አንቀጽ (ከዚያም ሌላ ፍጥረትን አድርገን አስገኘነው) [23፡14] እስከሚለው ድረስ በተገለጠ ጊዜ በመደነቅ እንዲህ አልኩ፦ “ከፈጣሪዎች ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ የተመሰገነ ይሁን!” ከዚያም የጥቅሱ መቋጫ የሆነው “ከፈጣሪዎች ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ የተመሰገነ ይሁን!” የሚለው ተገለጠ። (አል-ዋሂዲ፤ አስባብ አል-ኑዙል ሱራ 23፡14) https://quranx.com/Tafsir/Wahidi/23.14

ከዚህ እስላማዊ ምንጭ በግልጽ እንደሚታየው የጥቅሱ መጨረሻ የሆነው አባባል የሙሐመድ ጓደኛ ጭማሪ እንጂ ለሙሐመድ የተገለጠለት አይደለም። እንዲህ ያለ የቃል በቃል ግጥምጥሞሽ ሊፈጠር የሚችለው እንደ ሙሐመድ ሁሉ ዑመርም ነቢይ ከሆነ ብቻ ነው። ዑመር ነቢይ ካልሆነ ሙሐመድ ቁርኣኑን ሲያጽፍ ከራሱ እያመነጨ እንጂ ከፈጣሪ እየሰማ አልነበረም ማለት ነው፤ በሰው አስተያየት የሚሻሻል የፈጣሪ ቃል የለምና። ሙስሊሞች ቁርኣንን የሚመስል ነገር ማንም መፍጠር አይችልም የሚሉትም ብሂል ሐሰት ይሆናል። ሙስሊም ወገኖቻችን ዑመር ሰው አይደለም ካላሉን በስተቀር ቁርአንን ሰምቶ ከማስመሰል አልፎ ለቁርኣን ግብአት ሊሆን የቻለ ንግግር ተናግሯልና። በዚህ ሁኔታ ቁርአን ከዑመር ንግግር የተሻለ ሊሆን አይችልም።

ስናጠቃልል የአማርኛ ቁርኣን ተርጓሚዎች የአረብኛውን ትርጉም ለመለወጥ ቢሞክሩም የተጠቀሰው ቃል መፍጠርን እንጂ ስዕል መሳልን የሚያመለክት አይደለም። ቅድመ እስልምና በነበረው የአረብ አምልኮ ውስጥ ብዙ አማልክትና ፈጣሪዎች መኖራቸው ይታወቃል። በጥንቱ አረብኛ ውስጥ ባልተለመደ ሁኔታ በቁርኣን ውስጥ አምላክ በብዙ ቁጥር መገለጹ ቅድመ እስልምና የነበረው አምልኮተ ጣዖት በመጽሐፉ ውስጥ ለመገኘቱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። አምላክ ነጠላ አንድ ነው የሚለውም አባባል እንደ ሌሎቹ እስላማዊ አስተምህሮዎች ሁሉ በዝግመተ ለውጥ የመጣ ትምህርት ከመሆን ያለፈ አይደለም።  ባይሆን ኖሮ አንዱን ፈጣሪ ከብዙ ፈጣሪዎች ጋር ማነጻጸር ባላስፈለገ ነበር።


 

ሙሐመድ