ኢየሱስ አምላክ ከሆነ «ቢቻልህ ትላለህን? ለሚያምን ሁሉ ነገር ይቻላል፡፡» ከማለት አምላክ ስለሆንኩ ምን ይሳነኛል ለምን አላለም?

26. በማርቆስ 9:21-23 ላይ “ኢየሱስ የልጁን አባት “ይህ በሽታ ከጀመረው ምን ያህል ጊዜ ነው? ሲል ጠየቀው፡፡ አባትየውም እንዲህ አለ «ከህጻንነቱ ጀምሮ ነው፡፡ ሊገድለውም እየፈለገ ብዙ ጊዜ በእሳትና በውሀ ውስጥ ይጥለው ነበር፤ ግንቢቻልህ እባክህእዘንልን እርዳንም፡፡» ኢየሱስ «ቢቻልህ ትላለህን? ለሚያምን ሁሉ ነገር ይቻላል፡፡» አለው፡፡ ይላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቲያኖች እንደሚያስቡት «አምላክ» ከሆነ ታዲያ በማን አምኖ ነው ተዓምር ማድረግ የቻለው? ለምን ቢሉ «ለሚያምን ሁሉ ነገር ይቻላል፡፡» በማለት «ቢቻልህ» ተብሎ የተጠየቀውን ጥያቄ መልሷል፡፡ አምላክ ስለሆንኩ ምን ይሳነኛል አለማለቱም አስተውሎት ሊቸረው ይገባል፡፡

ኢየሱስ ይህንን ያለው ሰውየው ስለ ተጠራጠረው “ብታምን ይሆንልሃል” ለማለት ፈልጎ እንጂ ስለ ገዛ እምነቱ ለመጥቀስ ፈልጎ አይደለም፡፡ አሕመዲን ቀጣዩን ቁጥር ቢያነቡ ኖሮ ይህ ሃቅ በተገለጠላቸው ነበር፡፡ ዳሩ ግን እንደ ግብር አባታቸው ጥቅሶችን መቆራረጣቸውና ከአውድ ገንጥለው ማውጣታቸው ተሳስተው ሌሎችንም ለስህተት እንዲዳርጉ አድርጓቸዋል፡፡ ቀጣዩ ቁጥር እንዲህ ይላል፡- “ወዲያውም የብላቴናው አባት ጮኾ፦ አምናለሁ፤ አለማመኔን እርዳው አለ” (ቁ. 24)፡፡ የብላቴናው አባት ኢየሱስ ስለ እርሱ እምነት መናገሩን አውቆ አለማመኑን እንዲረዳ ተማፅኖታል፡፡ ታዲያ አሕመዲን ምን ቤት ናቸው በመሰለኝ እና በደሳለኝ የሚተረጉሙት?

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ