ኢየሱስ “እኔ ብቻዬን ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም» ካለ እንዴት አምላክ ይሆናል?

 


38. ኢየሱስ በርካታ ነገሮችን ማድረግ ሲያቅተው ተስተውሏል፡፡ ምንም ከራሱ ማድረግ እንደማይችልም በዮሐንስ 5:30 (የ1879 አትም) “እኔ ብቻዬን ከራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፡» ሲል በግልጽ ተናግሯል፡፡ አምላክ ከራሱ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልምን? አምላክ ከሌላ አካል እገዛ ይሻልን? እንዲሁም ሆኖ ምንም ማድረግ የማይችል አምላክ ነበርን?

አሁንም የተከበሩት ጠያቂያችን ኢየሱስ ሰውም አምላክም መሆኑን ዘንግተዋል፡፡ በፍፁም ሰውነቱ ያንን መናገሩ ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን ይህ የኢየሱስ ንግግር ከዚህም የጠለቀ ትርጉም አለው፡፡ ክርስቲያኖች ሦስቱም የሥላሴ አካላት ተነጣጥለውና ተለያይተው ይሠራሉ የሚል እምነት የላቸውም፡፡ አብ የሚሠራው ዘለዓለማዊ ቃሉ በሆነው በወልድ እና የእርሱ መንፈስ በሆነው በመንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ ስለዚህ ሦስቱን የሥላሴ አካላት መነጣጠል ፈፅሞ የማይቻል ነው፡፡ አንዳቸው ከሌላቸው ተለይተው መስራት ከባሕርያቸው ጋር አይሄድም፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ይህንን መናገሩ ከአብ ጋር ያለውን የማይነጣጠል አንድነት የሚያሳይ እንጂ አምላክነቱን የሚቃወም አይደለም፡፡

 

 

ለአሕመዲን ጀበል 303 ጥያቄዎች የተሰጠ መልስ ማውጫ