ለምንድነው በዮሐንስ ራዕይ 1፡6 እና 3፡12 ላይ ኢየሱስ በሰማይ ሆኖ እያለ አብ አምላኩ እንደሆነ የተገለፀው?

 


62. እንደ ክርስቲያኖች አስተምሮት: “የዮሐንስ ራዕይ” የተባለው መጽሐፍ ሲጽፍ ኢየሱስ ወደ ሰማይ አርጎ ነበር፡፡ ታዲያ ለምንድነው በዮሐንስ ራዕይ 1፡6 እና 3፡12 ላይ በሰማይ ያለው አብ አምላኩ እንደሆነ የተገለፀው?

ኢየሱስ የትንሳኤ አካሉን ይዞ ወደ ሰማይ በማረጉ ምክንያት በሰማይም ቢሆን ሰውም አምላክም ነው፡፡ ስለዚህ ሰብዓዊ ባሕርዩን ስላልተወ አብ አምላኩ መሆኑ መነገሩ የክርስቲያኖችን እምነት የሚያረጋግጥ እንጂ የሚቃወም አይደለም፡፡ ጠያቂያችን ይህንን ጥያቄ ማቅረባቸው መሠረታዊ የክርስትና ትምህርት ዕውቀት የጎደላቸው መሆኑን ያሳያል፡፡