እምነት ቢኖራችሁ ረግማችሁ ርግማናችሁ ይደርሳል?

 


  1. በማርቆስ 11፡20-23 ላይ “በማግስቱ ጠዋት በመንገድ ሲያልፉ፤ በለሊቱ ከነሥሯ ደርቃ አዩ፡፡ ጴጥሮስ ነገሩ ትዝ አለውና ኢየሱስን ፤ “መምህር ሆይ! እነሆ የረገምሃት በለስ ደርቃለች” አለው፡፡ ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላቸው፤ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ እውነት እለችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር” ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል፡፡” የሚል ጥቅስ ተገልጿል፡፡ ኢየሱስ ለምን እንዲህ አለ? ጴጥሮስ የኢየሱስ እርግማን መፈጸሙን በመገረም ሲነግረው፣ እንደይገረምና ኢርሱም እንዴት ሊፈጽምለት እንደቸለ አይደል ሊገልጽ የፈለገው? ኢየሱስ፡፡ “በእግዚአብሔር እመኑ፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ማንም ይህን ተራራ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር” ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ብያምን ይሆንለታል” ሲል ራሱ በማመኑ እርግማኑ መሳካቱን ገልጿል፡፡ ታድያ በእግዚአብሔር የሚያምነው ኢየሱስ ራሱ አምላክ ነው ሊባል ይችላልን?

ኢየሱስ ስለ ደቀ መዛሙርቱ እምነት እንጂ ስለ ራሱ እምነት እየተናገረ አይደለም፡፡ ኢየሱስ ስለ ራሱ እምነት እንኳ ቢናገር ይህ አምላክነቱን አጠራጣሪ አያደርግም፡፡ ፍፁም ሰው እንደ መሆኑ መጠን በምድር ላይ በነበረ ጊዜ የአብን ፈቃድ ብቻ በማድረግ እና በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በመታገዝ መሲሃዊ አገልግሎቱን ሲፈፅም ነበር፡፡ ስለዚህ በአብ በማመን ተዓምራትን እንደሚያደርግ ቢናገር እንኳ ምንም የሚያስከትለው ችግር የለም፡፡ እርሱ ብቸኛው የእግዚአብሔር አካል ነው ብንል እና ስለ ገዛ እምነቱ ቢናገር ራሱን ስለሚያምን አሁንም ችግር አይፈጥርም፡፡ ምናልባት የአሕመዲን አምላክ በራሱ አምላክነት እና የማዳን ችሎታ አያምን እንደሆን ግልፅ አይደለም፡፡