አምላክ ኢየሱስ ከፍተኛ አደጋ ውስጥ ሲገባ ለምን ዝም አለው? አይጠብቀውም?

 


39. አምላክ ደጋፊዎቻቸውን ከአደጋ ለመጠበቅና የሚወዳቸውንም ሰዎች ለመከላከል የገባውን ቃል ኪዳን ኢየሱስ (ኢሳ) የአምላክ ጠላቶች ቀላል ሰለባ ሆነው እስኪወድቁ ድረስ ችላ ይላል ወይ? ይህ ደግሞ የገባውን ቃል የማስፈፀሚያ መንገድ ወይም የቃል ኪዳኑ ክቡርነት ቅድመ ሁኔታ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል ወይ?

ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር የሚወዳቸውን ሰዎች በመከራ ውስጥ እንዲያልፉ ፈፅሞ ሊፈቅድ አይችልም የሚል ከቅዱሳት መጻሕፍት ጋር የሚጣረስ ምልከታ ስላለው በእጅጉ የተሳሳተ ነው፡፡ ጠያቂው የነቢያትንና የቅዱሳን ሰዎችን ታሪክ ለማጥናት ጊዜ ቢወስዱ ኖሮ ይህንን ጥያቄ ባልጠየቁ ነበር፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም ሆነ በቁርኣን ውስጥ ብዙ ነቢያት በመከራ ውስጥ ማለፋቸውንና መገደላቸውን የሚናገሩ ታሪኮች አሉ፡፡ ለበለጠ ማብራርያ በዚሁ ምዕራፍ ቁጥር 13 እና 24 ‹ለ፣ሐ› ይመልከቱ፡፡