ከሁሉም በላይ መሐሪ የሆነው አምላክ የመጀመሪያውን ኃጢአት ለአዳምና ለዝርዮቹ ይቅር ለማለት ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ ለምን ቆየ? 

 


  1. ከሁሉም በላይ መሐሪ የሆነው አምላክ የመጀመሪያውን ኃጢአት ለአዳምና ለዝርዮቹ ይቅር ማለት የማይችልና ነብዩ ኢየሱስ መጥተው በደማቸው እስኪቤዙ ድረስ በጥርጣሬና በውዥንብር ውስጥ የተዋቸው አድርጎ ማመኑን ምክንያታዊና አሳማኝ ማድረግ ይቻላል ወይ?

እግዚአብሔር ከክርስቶስ ዘመን በፊት የነበሩትን ሕዝቦች በጥርጣሬና በውዥንብር ውስጥ እንደተዋቸው ክርስቲያኖች አያምኑም፡፡ ይልቁኑ የመሲሁን መምጣት እና ቤዛነቱን ግልፅ በሆነ ሁኔታ በነቢያቱ በኩል አስቀድሞ አስታውቋል (ኢሳይያስ 53፣ ዳንኤል 9፡24-26)፡፡ እግዚአብሔር ኃጢአትን ያለ ቅጣት ዝም ብሎ ይቅር ማለት አለበት የሚለው አመለካከት የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት እና ምህረት እንጂ ፍትሃዊ ባሕርዩን እና ለኃጢአት ያለውን አመለካከት ያገናዘበ ባለመሆኑ ተቀባይነት የለውም፡፡