የተባለው የኢየሱስ ስቅለት ሲፈጸም የተመለከቱት ደቀ መዛሙርት ቁጥር ስንት ነው? ያሳዩት መስተጋብርስ ምን ነበር?

 


  1. የተባለው የኢየሱስ ስቅለት ሲፈጸም የተመለከቱት ደቀ መዛሙርት ቁጥር ስንት ነው? ያሳዩት መስተጋብርስ ምን ነበር? ሐዋርያት በሙሉ ጥለውት ሸሹ የሚለው የማቴዎስ (26፡56) ቃል እውነት ሊሆን ይችላል ወይ? እነዚያ ታላላቅ ሐዋርያት ከታላቁ መምህር ጋር ያላቸው አንድነትና ባህሪ መለክያው ይህ ነው ወይ? ተወዳጁ ዮሐንስ ብቻ ነበር ይህ ሁኔታ ሲፈጸም በቦታው ተገኝቶ ነበር የሚባለው፡፡ ይሁንና ምን ያህል ግዜ ነበር በቦታው የቆየው?

በኢየሱስ ስቅለት ወቅት እናቱ ማርያም፣ አክስቱ፣ የሮማዊው ባለሥልጣን የቀለዮጳ ሚስት ማርያም፣ መግደላዊት ማርያም፣ ሰሎሜ፣ የዮሐንስና የያዕቆብ እናት እና ከገሊላ ጀምረው የተከተሉት ሌሎች ብዙ ሴቶች በቦታው ነበሩ (ዮሐንስ 19፡25-26፣ ማቴዎስ 27፡55-56፣ ማርቆስ 15፡40-41፣ ሉቃስ 23፡49)፡፡ ዮሐንስ እስከ መጨረሻው በቦታው ላይ በመሆን ሞቱን እንደተመለከተ ተጽፏል (ዮሐንስ 19፡35)፡፡ ሐዋርያት ሁሉ ጥለውት እንደሸሹ ማቴዎስ 26፡56 ላይ የተጻፈ ቢሆንም ወዲያው ግን ጴጥሮስ ተመልሶ መምጣቱን እና የፍርድ ሂደቱን መከታተሉን በቁጥር 58 ላይ እናነባለን፡-

ጴጥሮስ ግን እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ድረስ ሩቅ ሆኖ ተከተለው፥ የነገሩንም ፍጻሜ ያይ ዘንድ ወደ ውስጥ ገብቶ ከሎሌዎቹ ጋር ተቀመጠ፡፡” ጴጥሮስ በሊቀ ካህናቱ ዘንድ ከታወቀ ከሌላ ደቀ መዝሙር ጋር ተመልሶ እንደመጣና ደቀ መዝሙሩ አስፈቅዶ አብረው ኢየሱስ ለፍርድ ወደቀረበበት የሊቀ ካህናቱ ግቢ እንደገቡ ዮሐንስ ይነግረናል (ዮሐንስ 18፡15-16)፡፡ ሐዋርያቱ እንዳይገደሉ በመፍራት ራሳቸውን ባይገልጡም ነገር ግን ሁኔታውን በቅርብ ርቀት ይከታተሉ እደነበር እንገነዘባለን፡፡